የክርስቲያን አገልግሎት

128/246

የተረጋገጣ ጥሪ

ብዙዎች-ፍላጎቱ ላላቸው ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ጸሎት የማድረግ የቤት ለቤት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 172. ChSAmh 194.1

ሠራተኞች በቤት ለቤት አገልግሎት ለየቤተሰቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በማንበብ የድርሻቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 141. ChSAmh 194.2

ራሷን ለጌታ ቀድሳ የሰጠች ሴት በቤት ለቤት የመጽሐፍ ቅዱስ አገልግሎት ተሳታፊ መሆን ይጠበቅባታል፡፡--Testimonies, vol. 9, pp. 120, 121. ChSAmh 194.3

የክርስቶስን ዱካ የምንከተል ከሆነ አገልግሎታችንን ወደ ሚፈልጉ ወገኖች መቅረብ የግድ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመክፈት የእግዚአብሔር ሕግ ከእኛ የሚጠይቀውን፣ ለሚያመነቱት የተሰጠውን አምላካዊ ተስፋ፣ ግዴለሹን የሚያነሳሳውንና ደካማውን የሚያጠነክረውን አምላካዊ ተስፋ ያንብቡላቸው፡፡Gospel Workers, p. 336. ChSAmh 194.4

ጌታ ሕዝቡ እንዲሠሩ የሚያደርገው ጥሪ በፊልጶስና በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ተሞክሮ ተመልክቶአል፡፡ ለኢትዮጵያዊው የተሰጠው የወንጌል አገልግሎት የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምተው ወደ ሚልካቸው የሚሄዱ የፊልጶስ ዓይነት ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወንጌላውያንን ይወክላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እያነበቡ ነገር ግን ቃሉን ማስተዋል የማይችሉ ብዙዎች በዓለም አሉ፡፡ ቃሉን ለእነዚህ ነፍሶች መግለጥ የሚችሉ አምላካዊ ዕውቀት ያላቸው ወንዶችና ሴቶች ያስፈልጉናል፡፡--Testimonies, vol, 8, pp. 58, 59. ChSAmh 194.5

ከቤተክርስቲያን አባላቶቻችን መካከል በየቤቱ እየዞሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ የሚያቀርቡ አገልጋዮች ያስፈልጉናል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 127. ChSAmh 194.6

የወንጌል ሠራተኞች የቤት ለቤት አገልግሎት በመስጠት ለሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስ ይክፈቱ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 123. ChSAmh 194.7

ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት ያልሰሙ የግብርናም ሆነ የኢንዱስትሪው ዘርፍ ባለ ሐብቶች በየአገሩ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ነፍሳት ያማከለ አገልግሎት መስጠት ይኖርብናል፡፡ ፈቃደኛ ወንጌላውያኖቻችን aዚህ የአገልግሎት ዘርፍ ይሰማሩ፡፡ መጻሕፍት በማበደር ወይም በመሸጥ፣ ጽሑፎችን በማደል እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አገልግሎት በመስጠት በሚኖሩበት አካባቢ ታላቅ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ ለነፍሳት የተለየ ፍቅር በማጎልበት ብዙዎችን መለወጥ በሚችል ኃይል መልእክቱን ማወጅ ይችላሉ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 35. ChSAmh 195.1