የክርስቲያን አገልግሎት
የሕክምናን ሥራ የማስፋፋት ዕቅድ
ጌታ ከእርሱ ጋር በጥምረት ለሥራት የሚያስችል ዕድል የሚፈጥሩልንን ሆስፒታሎቻችን እየረዳ ለአዳዲስሶቹም ተቋሞች ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡ የሦስቱ መላእክት መልእክት በሚታወጅበት በዚህ ግዙፍ ሥራ እያንዳንዱ አዳዲስ ተቋም እንደ አጋዥ እህት ድርጅት ሊታይ ይገባል፡፡ ጌታ በማይታይ እጅ የሚያጎለብታቸውን፣ ሕይወት የማዳን የተለየ ተግባር የሚያከናውኑት ሆስፒታሎቻችን ወደ ሥራ የሚገቡበትን ዕድል ሰጥቶአል፡፡ ሥራው ለአፍታም ሳይስተጓጎል _ ይቀጥል፡፡ Testimonies, vol. 7, p. 59. ChSAmh 189.2
የተቋሞች የሥራ ኃላፊነት የጤና ምግብ የሚዘጋጅባቸው ምግብ ቤቶችና የሕhምና ጣቢያዎች ይከፈቱ፡፡ ይህ ዘርፍ በባሕር ዳርቻዎች የሚከፈቱ የመዝናኛ ስፍራዎችን ያካተተ ይሁን፡፡ “የጌታን መንገድ አዘጋጁ” የሚለው የመጥምቁ ዮሐንስ ድምጽ በምድረ በዳ እንደ ተሰማ—የጌታ መልእክተኞች ድምጽ ቱሪስቶች በሚገኙባቸው የባሕር _ ዳርቻ መዝናኛዎች ሊሰማ የግድ ነው:: Testimonies, vol. 7, pp. 55, 56. ChSAmh 189.3
በብዙ ከተሞች የሚከፈቱ የጤና ምግብ ቤቶች ከሕክምና ተቋም ጋር ተያያዘዥነት ያለው አገልግሎት ሊሰጡ እንደሚገባ ብርሃን ተሰጥቶኛል፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሚፈጥሩት ትብብር ትክክለኛው መርኅ እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጓዳኝ አንዳንድ ጊዜ ለህመምተኞች ማረፊያ ክፍሎች ማዘጋጀት ጠቀሜታ አለው፡፡ የጤና ምግብ ቤቶች በሆስፒታሎች ለተመጋቢው የምግብ አገልግሎት የመስጠት ሥራ ይሠራሉ፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 60. ChSAmh 189.4
እግዚአብሔር ለከተሞቻችን የሚሰጠው መልእክት አለው፡፡ ይህን መልእክት—በወንጌል ስብሰባዎች፣ ወደ ሕዝብ ለመድረስ በሚቻልባቸው መንገዶችና የሕትመት ውጤቶቻችን ተጠቅመን ማወጅ ይኖርብናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መሻትን የመግዛት መልእክት በጤና ምግብ ቤቶቻችን ሊንጸባረቅ ይገባል፡፡ ከጤና ምግብ ቤቶቻችን ጋር ትስስር ያላቸው የወንጌል ስብሰባ ቅድመ ዝግጅቶች ሊደረጉ ይገባል፡፡ የጤና ምግብ ደጋፊ የሆኑ የሥነ ምግብ ባለሙያዎች በጤና ሳይንስና በክርስቲያናዊ መሻትን መግዛት ዙሪያ ትምህርት የሚሰጡበት ክፍል ይዘጋጅ፡፡ በእንዲህ ያለው ስብሰባ ሰዎች ለጤና ተስማሚ የሆነውን ምግብ እንዴት በቀላሉ ማዘጋጀት እንደሚችሉና በሌሎች አስፈላz ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ትምህርት ይሰጣል፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 115. ChSAmh 190.1
ወደ ምግብ ቤቶቻችን የሚጡ ሁሉ የሚያነቧቸው መልእቶች እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የተመጋቢውን ትኩረት የመሳብ ኃይል ያላቸው መሻትን በመግዛትና የሥነ ምግብ ተሐድሶ በማድረግ ዙሪያ የሚቀርቡ ጽሑፎችን ጨምሮ ወደ hርስቶስ ትምህርቶች የሚጋብዙ በራሪ ጽሑፎች ደምበኞች ሊያገኙ ይገባል፡፡ በራሪ ጽሑፍ የማዘጋጀትና የማቅረብ ሸክም የመላው ሕዝባችን ሊሆን ይገባል፡፡ ወደ ጤና ምግብ ቤቶቻችንና መዝናኛዎቻችን የሚመጡ ሁሉ የሚያነቡት ነገር ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ምናልባት ብዙዎች የሚሰጣቸውን በራሪ ጽሑፍ ባያነቡም ነገር ግን ከመካከላቸው ጥቂቶች ሰማያዊውን ብርሃን ሊመረምሩበት ይችላሉ፡፡ ከእናንተ ያገኙትን ካነበቡና ካጠኑ በኋላ ወደ ሌሎች ያስተላልፋሉ፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 116. ChSAmh 190.2
ምግብ ቤቶቻችንና የጤና ተቋሞቻችን ከተሞችን ማዕከል አድርገው የመመሥረታቸው ተቀዳሚ ምክንያት ሰዎች ትኩረታቸውን በሦስቱመላእክት መልእክት ጥሪ ላይ እንዲያደርጉ ለማስቻል እንደሆነ ተነግሮኛል፡፡ ሰዎች ለጤና ጠቀሜታ ያላቸውን ንጹህ ምግቦች የሚያዘጋጁ ምግብ ቤቶቻችን ከሌሎቹ ተራ ምግብ ቤቶች የተለየ አወቃቀር የተከተሉበትን መንስኤ በመጠየቅ መርኅዎችን መመርመራቸው ለዚህ ዘመን የተሰጠው ወቅታዊ መልእክት ዕውቀት ባለቤት በሚያደርጋቸው ከፍ ባለው መንፈሳዊ ማዕድ የምናገለግላቸውን ተጨማሪ መንገድ ይከፍትልናል፡፡Testimonies, vol. 7, pp. 122, 123. ChSAmh 191.1
የምግብ ዝግጅት ትምህርት መስጫ ስፍራዎች ሕhምና ከወንጌል ጋር በጥምረት በሚሠራበት ስፍራ ሁሉ የምግብ ዝግጅት ትምህርቶች ሊደፋፈሩ እንደሚገባ ጌታ አስተምሮኛል፡፡ ሰዎች በምግብ ምርጫቸው ዙሪያ ተሐድሶ እንዲያደርጉ የሚራ ማንኛውም ማበረታታት ሊደረግ ይገባል፡፡ በተቻለ መጠን የብርሃን ጨረሮች እንዲፈነጥቁላቸው ይደረግ፡፡ ተገቢውን የምግብ አዘገጃጀት ሥልጠና እየወሰዱ የተማሩትን ለሌሎች እንዲያካፍሉ ያበረታቱአቸው፡፡ —Gospel Workers, pp. 362, 363. ChSAmh 191.2
የምግብ ዝግጅት ማስተማሪያ ክፍሎች ይዘጋጁ፡፡ ሰዎች እንዴት ጤነኛ ምግም እንደሚያዘጋጁ ትምህርት ሊሰጣቸው የሚገባ ቢሆንም ነገር ግን አካልን ለረሃብ የሚያጋልጥ ዘዴ እንዲከተሉ ፈጸሞ ማደፋፈር የለብንም፡፡ ሰዎች ጤነኛ ያልሆኑ ምግቦችን ከገበታቸው ማስወገድ እንዳለባቸው ማሳየት ተገቢ ነው፡፡ እንደ ሻይ፣ ቡና እና የሥጋ ምግብ ከማዕድ ላይ በማስወzድ ጤነኛና የተመጣጠነ ምግብ ማግኘት ይቻላል፡፡ ሰዎች ጤነኛውንና የምግብ ፍላጎት የሚከፍተውን ምግብ እንዴት እንደሚያዘጋጁ ትምህርት የሚሰጠው ሥራ እጅግ አስፈላጊና ብርቱ አጽንኦተ የሚሰጠው ነው፡፡Testimonies, vol. 9, p. 12. ChSAmh 191.3