የክርስቲያን አገልግሎት
የእንዳንዱ ቤተ hርhቲያን ሥራ
የጤና ተሐድሶ መልእክት በእያንዳንዱ ቤተ hርስቲያን መሰራጨት ይኖርበታል፡Testimonies, vol. 6, p. 370. ChSAmh 186.1
የወንጌላዊው ሕክምና ባለሙያ አገልግሎት በምድር የእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን ሥራ አካል ሊሆን ይገባል፡፡—Testimonies, vol. 6, p. 289. ChSAmh 186.2
እያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያን አባል እንደ ወንጌላዊነቱ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡-- Testimonies, vol. 7, p. 62. ChSAmh 186.3
የጤና ተሐድሶ ሥራ ጌታ በምድራችን የሚስተዋለው የሥቃይ መጠን እንዲቀንስ የሚደርግበትና ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠራበት መንገድ ነው፡፡ አካላዊውና መንፈሳዊው ጤንነት ወደ ቀድሞው ይመለስ ዘንድ ሰዎች ከጌታ ጋር ተባብረው የአምላካዊው የድጋፍ እጅ መሆን እንዲችሉ አስተምሯቸው፡፡ ይህ ሰማያዊውን አዎንታ የያዘ ሥራ ሌሎች ተጨማሪ የከበሩ እውነቶች ሊገቡ የሚችሉበትን በር ይከፍታል፡፡ ይህን አገልግሎት በብልሃት ለሚይዙ የሚበጅ ስፍራ አለ፡፡-Testimonies, vol. 9, pp. 12, 13. ChSAmh 186.4
ምንም እንኳ ከፊታችን ውሸንፍር የበዛባቸው ጊዜያቶች ቢኖሩም አለማመንን የሚገልጽ ወይም ተስፋ አስቆራጭ ቃል ከአንደበታችን አይውጣ፡፡ በኃጢአት የታመሙ ነፍሳት ለሞሉበት ዓለም ፍቱን የፈውስ መልእክት መያዛችንን እናስታውስ፡፡Special Testimonies, series B, no. 8, p. 24 ChSAmh 186.5
ይህ በአግባቡ የተቀናበረ ሥራ በቤተ hርስቲያን ችላ የተባሉ አያሌ ምስኪን ኃጢአተኛ ነፍሳትን ያድናል፡፡ ክርስቲያኖች የተሰለፉበት በጎ ተግባር ተቋዳሽ ለሆን የሚናፍቁ ከእኛ እምነት ያልሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከልብ የመነጨ ፍላጎት ለጎረቤቶቻቸው ቢያሳዩ ኖሮ ለዚህ ዘመን የተሰጡን የተለዩ እውነቶች ወደ ብዙዎች መድረስ በቻሉ ነበር፡፡ ሰዎች በሚገኙበት ሁናቴ ደርሶ እነርሱን የመርዳትን ያህል የሥራውን ጸባይ መግለጽ የሚችል ነገር የለም፡፡ እግዚአብሔርን እንደሚወዱና ትእዛዛቱን እንደሚጠብቁ በመናገር ክርስቶስ እንደ ሠራ የሚሠሩ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች ምናልባት ዛሬ በመልእክቱ ሐሴት ያደርጉ ይሆናል፡፡ ሕክምናን ከወንጌል ጋር አጣምሮ የያዘው ይህ አገልግሎት ወንዶችንና ሴቶችን በሚያድነው የክርስቶስ ዕውቀትና የእርሱ እውነት ሲያሸንፍ፤ ለዚv ዘላቂ ሥራ ገንዘብም ሆነ ቅን አገልግሎት በጥንቃቄ እንዲውል ይደረግ፡፡Testimonies, vol, 6, P 280. ChSAmh 186.6
ሕዝባችን ሕክምናን ከወጌል ጋር አጣምሮ ለያዘው ሥራ ሕያው ፍላጎት እንዳለው ያሳይ፡፡ በዚህ መስክ እንደ መመሪያ እንዲያıለግሉን የተጻፉ መልእክቶችን በማጥናት ጠቃሚ እንዲሆኑ ራሳቸውን ያዘጋጁ፡፡ እነዚv መጻሕፍት አሁን ከሚታየው የላቀ ትኩረትና አድናቆት ሊቸራቸው ይገባል፡፡ በብዙዎች ተስተውለው ብርቱ ጠቀሜታ እንዲገኝባቸው ታልመው የተጻፉ መልእክቶች የጤናን መርኅዎች የማስተማር የተለየ ዓላማ አላቸው፡፡ እነዚህን መርኅዎች የሚያጠኑና በሕይወታቸው የሚተገብሩ አካላዊም ሆነ መንፈሳዊ ማንነታቸው አብልጦ የተባረከ ይሆናል፡፡ የጤና ፍልስፍናን ማስተዋላችን ያለማቋረጥ እየተስፋፋ እየሄደ ከሚገኘው የክፉ አሠራር መከላከያና መጠበቂያ ይሆነናል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 63. ChSAmh 187.1
ሰዎች ራስን መቆጣጠር ለማይችል ወራዳ ልማድ ማንነታቸውን አሳልፈው ቢሰጡ እንኳ ለትክክለኛው ዓይነት አገልግሎት ምላሽ እንደሚሰጡ ተነግሮኛል፡፡ ይህ ወንጌልን ከሕክምና አጣምሮ አገልግሎት የሚሰጠው ወንጌላዊ በጉዞው የሚያጋጥመው ነው፡፡ ሆኖም ለእነዚህ ሰዎች ተገቢው እውቅናም ሆነ ማበረታታት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እነዚህን ወገኖች ቀና ለማድረግጽኑ፣ በትዕግሥት የተሞላና ቅን ጥረት ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡ ራሳቸውን ወደ ቀድሞው ንጽሕና መመለስ ስለሚቸገሩ ምናልባት የክርስቶስን ጥሪ ቢሰሙ እንኳ ትርጉም ያለው ለውጥ ለማድረግ ጆሮዎቻቸው ደንዝዘዋል፡፡ ዐይኖቻቸው ለእነርሱ የሚበጅ አንዳች በጎ ነገር ከአምላካዊው ግምጃ ቤት መመልከት እንዳይችሉ ሆነው ታውረዋል፡፡ በመተላለፋቸውና በኃጢአታቸው ሙታን ናቸው፡፡ ይህም ሆኖ—ከወንጌል ግብዣ ውጪ ሊደረጉ አይችሉም፡፡ “ኑ” የሚለውን አምላካዊ ግብዣ ሊቀበሉ ይገባል፡፡ ምንም እንኳ ግብዣው ለእነርሱ እንደማይገባ አድርገው ቢያስቡም ጌታ ግን “በግድ አምጥተv አስገባ” በማለት ይናገራል፡፡ ያለ አንዳች ሰበብ እርሱን በማድመጥ አምላካዊውን ተስፋ በፍቅርና በበጎነት አጥብቀን እንያዝ፡— Testimonies, vol. 6, pp. 279, 280. ChSAmh 187.2
መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማደል ላይ የተሰማሩወንጌልን ከሕከምና አጣምሮ በያዘው አገልግሎት የመግባት ዝግጅት ይኑራቸው፡፡ የታመሙና በሥቃይ ያሉ ርዳታ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ይህ የምህረት አገልግሎት ከሚሰጣቸው መሃል አብዛኞቹ የሕይወትን ቃል ሰምተው ይቀበላሉ፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 34. ChSAmh 188.1
ሕክምናን ከወንጌል ጋር አጣምሮ የያዘውን አገልግሎት በማስተዋል ወደ ሥራው ለመግባት የተዘጋጀ ማን ነው? እያንዳንዱ ሠራተኛ አገልግሎቱ የገባውና ብቃት ያለው ይሁን፡፡ እንዲህ ከሆነ እንደ የሱስ ከፍ ባለና ሰፊ በሆነ ማስተዋል ማቅረብ ይችላል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 70. ChSAmh 188.2
የጌታን አገልግሎት ወደፊት አስኪዱ፡፡ ሕክምናን ከወንጌል ጋር አጣምሮ የያዘውን አገልግሎትና የሥነ ትምህርቱን ዘርፍ ወደፊት እንዲራመድ አድርጉ፡፡ ታላቁ እጦታችንጽኑ፣ ራሱን ለአገልግሎት አሳልፎ የሰጠ፣ ብልvና ብቁ ሠራተኛ መሆኑን አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ፡፡ Testimonies, vol. 9, pp. 168, 169. ሕያው የሆነውን የጤና ተሐድሶ መርኅ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ማያስተውሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ውሰዷቸው፡፡Testimonies, vol. 9, p. 118. ChSAmh 188.3
የጤና ተሐድሶ መምህራን አገልግሎቱን ወደፊት ማራመድ እንዳለባቸው እንድነግር ታዝዣለሁ፡፡ እያንዳንዱን አነስተኛ ተጽእኖ በማሳደር ዛሬ እየታየ ያለውን የሞራል ውድቀትና ዋይታ ወደ ቀድሞው እንመልስ ዘንድ ዓለም ይፈልገናል፡፡ የሦስቱን መላእክት መልእክት የሚያስተምሩ ለቆሙበት ዓላማ ጸንተው ይቁሙ፡-- Testimonies, vol. 9, p. 113. ChSAmh 189.1