የክርስቲያን አገልግሎት
ከወንጌል አገልግሎት ጋር ጥምረት መፍጠር
የወንጌልና የሕክምና አገልግሎቶች እጅና ጓንት ሆነው መራመድ ይኖርባቸዋል፡፡ ወንጌል ከእውነተኛ የጤና ተሐድሶ መርኅ ጋር ሊጣመር ይገባል፡፡ የክርስትና ሕይወት በተጨባጭ እንዲታይ የሚያደርግ ጽኑ፣ ጥብቅና መሻሻል የሚያመጣ ሥራ መሠራት ይኖርበታል. . . ወንዶችና ሴቶች የጤና ተሐድሶ መርኅዎችን አስፈላጊነት ተመልክተው ይለማመዷቸው ዘንድ ለሕዝቡ ለማቅረብ አቅማችን የሚፈቅደውን ሁሉ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 379. ChSAmh 183.3
ደቀ መዛሙርቱ እንደሠሩ በተመሳሳይ እንሠራ ዘንድ መለኮታዊው እቅድ ነው፡፡ አካላዊ ፈውስ ከወንጌል ተልዕኮ ጋር የተጣመረ ነው፡፡ በወንጌል ሥራ ማስተማርና መፈወስ ፈጽሞ የማይለያዩ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው:፡The Ministry of Healing, p. 141. ChSAmh 183.4
የወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ አገልግሎትና የወንጌላዊው ሥራ እግዚአብሔር መልካምነቱን ያለማቋረጥ ለመለገስ የሚመኝባቸው መስመሮች ናቸው:፡ እነዚህ መስመሮች ወደ ቤተ ክርስቲያን ግድብ የሚፈሱ የሕይወት ወንዞች ሊሆኑ ይገባል፡፡Bible Echo, Aug, 12, 1901. ChSAmh 183.5
አምላዊውን ቃል በመስበኩ ረገድ በቂ ተሞክሮ ያካበቱ አገልጋዮቻችን ቀለል ያሉ የሕክምና ዘዴዎችን በመማር እንደ አንድ ወንጌላዊ የሕክምና ባለሙያ ብልህ አገልግሎት ይስጡ፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 172. ChSAmh 183.6
መንገድ ጠራጊው ከቦታ ወደ ቦታ ሲዘዋወር አያሌ በደዌ የተያዙ ወገኖችን ያገኛል፡፡ ስለ ተለያዩ በሽታዎች መንስኤ ተጨባጭ ዕውቀት እንዲኖረው የሚጠበቀው ይህ ወንጌላዊ የሕክምና ባለሙያ በሥቃይ ያለውን ግለሰብ ህመም ሊያስታግስ የሚችል ቀለል ያለ የህክምና እርዳታ እንዲሰጥ ይጠበቃል፡፡ ከዚህ በላቀ ለህምተኛው በእምነት መጸለይና ወደ ታላቁ ሐኪም ማመላከት ይኖርበታል፡፡ ወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ ከእግዚአብሔር ጋር ሲሠራና ሲራመድ ወደ ልቦች መድረስ እንዲችል የሚረዱ አገልጋይ መላእhት ከጎኑ ይሆናሉ፡፡ በታማኝና የተቀደሱ ወንጌላውያን የሕhምና ባለሙያዎች ፊት እንዴት ታላቅ የአገልግሎት በር ተከፍቶአል! ሥራውን በትጋት ለሚሠራው እንዴት ዓይነት በረከት ተዘጋጅቶለታል!—Southern Watchman, Nov, 20, 1902. ChSAmh 184.1
የጤናማ አኗኗርን መርኅዎች ማካፈል ለወንጌል ሠራተኛው የተመደበ አገልግሎት መሆኑን እያንዳንዱ የወንጌል ሠራተኛ ሊሰማው ይገባል፡፡ በዚህ አገልግሎት ዙሪያ ያለው ፍላጎት ከፍተኛ እንደመሆኑ ዓለም ሳታቅማማ ትቀበለዋለች፡:—The Ministry of Healing p. 47. ChSAmh 184.2