የክርስቲያን አገልግሎት

120/246

መለኮታዊው ምሳሌ

ታላቁ ሐኪምና አገልጋይ የሆነው ክርስቶስ ምሳሌያችን ነው… እርሱ በሽተኞችን ፈወሰ ወንጌልንም ሰበከ፡፡ ፈውስና ስብከት በቅርብ የተሳሰሩ የአገልግሎቱ ክፍሎች እንደነበሩ ሁሉ ዛሬም ሊነጣጠሉ አይገባም፡፡ Testimonies, vol. 9, pp. 170, 171. ChSAmh 182.4

የክርስቶስ አገልጋዮች እርሱ የተወላቸውን ምሳሌ መከተል ይኖርባቸዋል፡፡ ለአገልግሎት ከቦታ ቦታ ይዘዋወር በነበረበት ወቅት በሐዘን የነበረውን ካጽናና፣ በህመም የተያዘውን ደግሞ ከፈወሰ በኋላ ስለ ሰማያዊ መንግሥቱ እውነት ያካፍላቸው ነበር፡፡ የእርሱም ተከታዮች ሥራ ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም፡፡— Christ’s Object Lessons, pp. 233, 234. ChSAmh 182.5

የክርስቶስ ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ እርሱ የተወውን ምሳሌ መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ በቅድሚያ የባልንጀራችንን አካላዊ ችግር ማስታገስና መፍትሔ ማግኘት ስንችል ከልብ የመነጨው ምስጋናና አድናቆት የመለያያ ግድግዳውን ያፈርሰዋል፡፡ በዚህም በቀላሉ ወደ ልባቸው ለመድረስ እንችላለን፡፡ ይህን አካሄድ በቅን ልብ ያጢኑ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 127. ChSAmh 183.1

ወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ በመንፈስ፣ በቃልና በጸባይ የመለኮታዊው ሐኪምና የወንጌል አገልጋይ ግልባጭየየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆኑ በገሃድ የሚታይ ይሁን፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 127. ChSAmh 183.2