የክርስቲያን አገልግሎት

122/246

የመልእክቱ ቀኝ እጅ

የወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ አገልግሎት ከሦስቱ መላእክት መልእክት ጋር እጅና ጓንት መሆኑ በተደጋጋሚ ተነግሮኛል፡፡ ወንጌላዊውያን የሕክምና ባለሙያዎች መለኮታዊውን ትእዛዝ እየተቀበሉ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት መንገዱን የማዘጋጀት ሥራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ቅንጅት ፈጥረው መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ የሰብዓዊው ቀኝ እጅ የሆነው እውነት ያለማቋረጥ በንቃት ሲሠራ እግዚአብሔር ያበረታዋል፡፡ ሆኖም ቀኝ እጅ መላውን አካል መወከል እንደማይችል ሁሉ አካል “አታስፈልገኝም” ሊለው አይችልም፡፡ አካል የንቁና ብርቱ ሥራ ባለቤት እንዲሆን የሚሠራ እጅ ያስፈልገዋል፡፡ ሁለቱም ለየራሳቸው የተመደበ ሥራ ያላቸው እንደመሆኑ አንደኛው ከሌላው ተነጥሎ የሚሠራ ከሆነ ሁለቱም ብርቱ እጦትና ሥቃይ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡Testimonies, vol. 6, p. 288. ChSAmh 184.3

የሕክምና ባለሙያው የሚሰጠው የወንጌል ሥራ ሊኖር ይገባል. . . እጅ ለአካል እንደሚሠራ አገልግሎቱም ለእግዚአብሔር መዋል ይኖርበታል፡፡ Testimonies, vol. 8, p. 160. ChSAmh 185.1