የክርስቲያን አገልግሎት

119/246

ምዕራፍ 11—ሕክምናንና ወንጌልን በአንድ ያጣመረ ሥራ

ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሥራ

የሱስ በምድራዊ አገልግሎቱ አብዛኛውን ጊዜውን ያውል የነበረው ለስብከት ሳይሆን በሽተኞችን ለመፈወስ ነበር፡፡-The Ministry of Healing, p. 19. ChSAmh 181.1

ለእውነተኛው የተሐድሶ አራማጅ መንገዱን የሚጠርገው ወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ አያሌ በሮችን ይከፍታል፡፡Testimonies, vol 7, p. 62. ChSAmh 181.2

ወንጌልን በተጨባጭ የተለማመደ የሕክምና ባለሙያ የሚሰጠው አገልግሎት እውነተኛና የታመነ ነው፡፡ Testimonies, vol. 8, p. 168. ChSAmh 181.3

የወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ አገልግሎት ፋና ወጊ የወንጌል ሥራ ነው፡፡ ወንጌል ቃሉን የማካፈል _ አገልግሎት በሚሰጡና በህhምና ባለሙያዎች ሊሰበክና ሊተገበር ይገባል፡፡— The Ministry of Healing p. 144. ChSAmh 181.4

የዓለም አዳኝ አብዛኛውን ጊዜውንና ጉልበቱን ያውል የነበረው ለስብከት ሳይሆን ብርቱ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች በመፈወስ ነበር፡፡ በምድር የእርሱ ተወካዮች የሆኑት ደቀ መዛሙርት እጆቻቸውን በበሽተኞች ላይ ጭነው እንዲፈውሱ የሱስ ከዕርገቱ አስቀድሞ አዟቸው ነበር፡፡ ጌታ ዳግም ሲገለጥ በሽተኞችን የጎበኙትንና መከራ የደረሰባቸውን ወገኖች ያጽናኑትን ያመሰግናቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 4, p. 225. ChSAmh 181.5

ወንጌላዊው የሕክምና ባለሙያ የሦስቱ መላእክት መልእክት የሆነውን ወቅታዊውን እውነት ለሕዝቦች የማቅረብ-ጎዳና የመጥረግ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ይህን አወቃቀር ተከትለን ከተራመድን መልእክታችን ግርዶሽም ሆነ እንቅፋ1 አይገጥመውም:፡--Testimonies, vol, 6, p. 293. ChSAmh 182.1

በጊዜያዊ እጦት ውስጥ ለሚገኘው ምስኪን ቅድሚያ ሰጥተን ለአካላዊውና ሥቃይ ላስከተለው ችግር መፍትሔ ስንሰጥ መልካሙን ምግባርና የኃይማኖት ዘር የምንዘራበት ልብ ውስጥ ለመግባት የሚያስችለንን የተከፈተ በር እናገኛለን፡፡--Testimonies, vol. 4, p. 227. ChSAmh 182.2

በሽተኞችንና ተስፋ የቆረጡትን በመጎብኘትና በማገልገል የብርሐን ጮራ እንዲያዩና በየሱስ ላይ ያላቸውን እምነት ሲጠነክር የመመልከት ያህል የላቀ መንፈሳዊ ብርታትና ጥልቅ የቅንነት ስሜት ሊሰጥ የሚችል ነገር የለም፡፡-- Testimonies vol. 4, pp. 75, 76. ChSAmh 182.3