የክርስቲያን አገልግሎት
በብዕርና በአንደበት
የየሱስን ሕያው አማላጅነት በብዕርዎም ሆነ በአንደበትዎ ያውጁ፡፡ ከታላቁ ሠራተኛ ጌታ ጋር ሕብረት ይፍጠሩ፡፡ ራሱን ከዶ በምድር ላይ በፍቅር የተመላለሰውን አዳኝ ይከተሉ፡፡Review and Herald, Jan. 24, 1893. ChSAmh 179.3
ሥራው ፍጹምና የተሟላ ይሆን ዘንድ ሁላችንም ጌታ እንደሚጠራንና እንደሚራን--የተለያየ አገልግሎት እንሰጣለን፡፡ እነሆ እርሱን በብዕራችንናበአንደበታችን እንድናገለግል ተጠርተናል፡፡Testimonies, vol.9, P 26. ChSAmh 179.4
ስለ ተሰቀለው ክርስቶስ--መነጋገር፣ መጸለይና መዘመር የነፍሳትን ልብ ይከፍታል ያሸንፋልም፡ ፡-- Testimonies, vol, 6, p. 67. ChSAmh 180.1
ብዕር በልባቸው መሠዊያ ላይ የሚነደው እውነት በሚሰማቸው፣ ለእግዚአብሔር ብልv ቅንአት ባደረባቸውና ሚዛናዊ የፍርድ ስሜት ባላቸው ሰዎች እጅ የሚገኝ ኃይል ነው፡፡ ከንጹሑ እውነት የቀለም ምንጭ እያጠቀሰ የሚጽፈው ብዕር በጽልመት ወደ ተዋጡት የምድር ጥጋት ላይ አዲስ ኃይል እየጨመረ፣ በየቦታው የተበታተኑ ብርቱ የብርሃን ጉልበት እንዲያıኙ እያደረገ-መልሶ የሚያንጸባርቅ የብርሐን ጨረር ፍንጣቂ መላክ ይችላል፡፡Life Sketches, p. 214. ChSAmh 180.2
ሥራውን ወደ ፍጸሜ ማምጣት ይቻል ዘንድ አገልጋዮቻችን ጉልበታቸውን ሁሉ በስብከት ላይ ማፍሰስ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም መንፈሳዊ ጽሑፎችን የማደል ሥራ ከፈቃደኛ ወንጌላዊ አገልግሎት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ስኬታማ ውጤት እንዲያመጣ ለቤተ hርስቲያን አባላት ተıቢውን ሥልጠና ሊሰጡ ይገባል፡፡ መንፈሳዊ መልእክቶችን መላhና ጽሑፎችን የማደል ሥራ የመመስከር አገልግሎቱን ያግዛል ያጠናክራልም፡፡ የአንደኛው አገልግሎት ጤናማ መሆንና በልካም ሁናቴ ላይ መገኘት ለሌላኛው የአገልግሎት ዘርፍ ብርቱ ኃይል ይሆናል፡፡-Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 180.3
ንቃት በሚጠይቀው የወንጌል ሥራ ታካች አይሁኑ፡፡ በዚህ አገልግሎት ስኬታማ ሥራ መሥራት የሚችሉት ከእግዚአብሔር ጋ ሊፈጥሩ በሚችሉት ግንኙነት ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡ መንፈሳዊመልእክቶችን ወይም ደብዳቤዎችን ከመጻፍዎ አስቀድሞ ከእውነተኛው የወይን ግንድ ጋር ተባቅለው ለእግዚአብሔር ክብር ፍሬ የሚያፈሩ የዱር ቅርንጫፎች ያገኙ ዘንድ ሁል ጊዜ ይጸልዩ፡፡ ትሁት በሆነ ልብ የድርሻቸውን የሚሠሩ ሁሉ እንደ ወይኑ ዙሪያ ሠራተኝነታቸው ያለማቋረጥ ራሳቸውን ያስተምራሉ፡፡-Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 180.4