የክርስቲያን አገልግሎት

68/246

ምዕራፍ 7—የወንጌል ሠራተኞችና የምዕመናን ትብብር

በተባበረ አንድነት ወደ አገልግሎት መግባት

በወንጌል አገልግሎት በመደበኛ የተቀጠሩ ሠራተኞችም ሆኑ የቤተ ክርስቲያን አባላት እያሸተ ወዳለው መኸር ይሰማሩ፡፡ በሰዎች የተዘነጉትን የወንጌል እውነቶች በሰበኩ ቁጥር ከደረሰው መኸር ይሰበስባሉ፡፡ እውነትን ተቀብለው ነፍሳትን ለክርስቶስ ለማሸነፍ ቅንአት የሚያድርባቸውን ወገኖች ያገኛሉ፡፡-Australian Signs of the Times, Aug. 3, 1903. ChSAmh 93.1

የሥራው ታላቁ ክፍል የሆነው እውነትን የመዝራት ኃላፊነት ለወንጌል ሥራ ለተቀጠሩ አገልጋዮች ብቻ እንዲተው የጌታ ዓለማ አይደለም፡፡ በመደበኛ የወንጌል አገልግሎት ተቀጥረው ለመሥራት ያልተጠሩ ያላቸውን አያሌ ችሎታ ለጌታ እንዲያውሉ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡ አሁን ያለ ሥራ የተቀመጡ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች ተቀባይነት ያለው አገልግሎት ማበርከት--እውነትን ወደ ጓደኞቻቸውና ጎረቤቶቻቸው በማድረስ ለጌታ ታላቅ ሥራ መሥራት ይችላሉ፡፡Testimonies, vol. 7, p. 21. ChSAmh 93.2

አገልጋዮች የሚያውጁት የእውነት መልእክት በእግዚአብሔር የተሰጣቸው ሲሆን ይኸውም ቤተ hርስቲያናት መልዕክቱን ተቀበለውና የግንኙነት አድማሳቸውን አስፍተው አፍላዎቹን የብርሐን ጨረሮች ወደ ሌሎች እንዲያዳርሱና እንዲያሰራጩ ነው::--Testimonies, vol. 6, p. 425. ChSAmh 93.3

ምዕመኑ የአገልጋዩ ቀኝ እጅ በመሆን ለጥረቱ ድጋፍ ሲሰጥና ሸክሙን እንዲሸከም እገዛ ሲያደርግለት የሥራ ጫና አይበዛበትም፤ ተስፋ መቁረጥም አያገኘውም፡፡ ምዕመኑ ሥራውን ወደፊት ለማካሄድ ከሚያስችለው መርኅ ካላፈነገጠ በቀር በቤተ ክርስቲያን ለመሸከም አዳጋች ሆኖ የሚዘልቅ ተጸእኖ ሊኖር አይችልም፡፡-- Review and Herald, Aug. 23, 1881. ChSAmh 94.1