የክርስቲያን አገልግሎት
የመዝሙር አገልግሎት
ጣፋጭ የሆነውን የወንጌል የውዳሴ ቃና ከነልዩ ባህሪው የቀሰሙ ተማሪዎች በዘማሪ ወንጌላውያንነት የላቀ መልካም አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን በመዘምራን መካከል አምልኮ የማድረግ ዕድሉን ማግኘት ወዳልቻሉ አያሌ ብቸኛ ስፍራዎች እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁናቴና በሐዘን ወደ ተዋጡ ወገኖች በመጓዝ እግዚአብሔር በሰጣቸው መክሊት ዜማና የጸሐይ ጮራ ይፈንጥቁ፡፡ ተማሪዎች ወደ አውራ ጎዳናውም ሆነ ወደ የጥጋቱ ሂዱ፡፡ ጥረታችሁ ከፍ ያለውንም ሆነ በዝቅታ የሚኖረውን የኅብረተሰብ ክፍል ያካተተ ይሁን፡፡ የሐብታሞችንም ሆነ የድኾችን ደጃፍ አልፋችሁ የምትገቡበትን ዕድል ስታገኙ “ጥቂት የወንጌል መዝሙሮችን ብንዘምርላችሁ ደስተኞች ናችሁ?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ የልቦች መለሳለስ እግዚአብሔር በዚያ የሚገኝበትን ጥቂት የጸሎት ቃላት ለመሰንዘር የሚያስችል በር ሊከፍት ይችላል፡፡ ይv ልባዊ የወንጌላዊ አገልግሎት እንደመሆኑ ብዙዎች መዝሙር ለመስማት ተቃውሞ አይኖራቸውም፡፡--Counsels to Teachers, pp. 547, 548. ChSAmh 92.1