የክርስቲያን አገልግሎት
አሳማኙ ስብጥር
ለዓለም አሳማኝ መሆን የሚችለው ከቤተ ክርስቲያን ምስባክ የሚደመጠው አስተምህሮ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን የምትኖረው ሕይወት ነው፡፡ መደበኛው የወንጌል ሠራተኛ የወንጌልን ንድፈ ሐሳብ ሲያውጅ በቤተ hርስቲያን በተጨባጭ የሚታየው ቅድስና ደግሞ አምላካዊውን ኃይል ገልጦ ያሳያል፡፡— Testimonies, vol. 7, p. 16. ChSAmh 94.2
ወንዶችና ሴቶች የቤተ ክርስቲያን አባላት ኃይላቸውን አሳስበው ከአገልጋዩና ከቤተ hርስቲያን መሪዎች ጋር በአንድነት ወደ ሥራው እስከሚገቡ በዚህ ምድር የተጀመረው የእግዚአብሔር ሥራ ፍጻሜ ማግኘት አይችልም፡፡--Gospel Workers, p. 352. ለነፍሳት ደኅንነት መሠራት ከሚኖርበት ሥራ ውስጥ ስብከት አነስተኛውን ክፍል ይወስዳል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ኃጢአተኞችን ስለ እውነት እየወቀሰና በደለኝነታቸውን እንዲመለከቱ እያደረገ በቤተ ክርስቲያን እቅፍ ያኖራቸዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች የራሳቸውን የሥራ ድርሻ ይወጡ ይሆናል _ እንጂ ቤተ ክርስቲያን መሥራት የምትችለውን ሥራ ሊሠሩ አይችሉም፡፡ Testimonies, vol. 4, p. 69. ChSAmh 94.3
የእግዚአብሔርን እውነት የማሰራጨት ኃላፊነት ለጥቂት የተቀቡ አገልጋዮች ብቻ ተወስኖ የተቀመጠ አይደለም፡፡ ይልቁንም የእውነት ዘር የhርስቶስ ደቀ መዛሙርት ነን በሚሉ ሁሉ በውሃ ዳር ሊዘራ ይገባል፡፡ Review and Herald, Aug. 22, 1899. ChSAmh 94.4
የወንጌል ሠራተኞችና የምዕመናን ትብብር አገልጋዮች አስደሳችና አሳማኝ ሰፊ ንግግር ቢያደርጉ፣ ቤተ ክርስቲያንን የመገንባትና የማበልጸግ ሰፊ ሥራ ቢሠራአባላቶቿ እንደ የሱስ ክርስቶስ አገልጋይነታቸው የድርሻቸውን ካላበረከቱ በቀር ሁል ጊዜም አቅመ ቢስና በጨለማ የተዋጠች ሆና ትቀራለች፡፡ ዓለም ክፉና በጽልመት የወደቀች እንደመሆኗ ጽኑና ዘላቂው ተምሳሌነት የበጎው ብርቱ ኃይል ነው፡፡-Testimonies, vol. 4, pp. 285, 286. ChSAmh 95.1