የክርስቲያን አገልግሎት

63/246

ምዕራፍ 6—ተማሪዎች በሥልጠና ላይ እያሉ የሚሠሩት የወንጌል ሥራ

የትምህርት ዓላማ

እውነተኛ ትምህርት ወንጌላዊን የማሠልጠን ሥራ ነው:: እያንዳንዱ የእግዚእብሔር ልጅ የሆነ ወንድም ሆነ ሴት ለእግዚአብሔርና ለባልንጀራው አገልግሎት መስጠት በሚያስችለው በወንጌል አገልግሎት ተሳራፊ የሚሆንበት ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ እኛን ለዚህ አገልግሎት ብቁ አድርጎ መቅረጽ የትምህርታችን ተጨባጭ ዓላማ ሊሆን ይገባል፡፡--The Ministry of Healing, p. 395. ChSAmh 89.1

ትምህርት ቤቶቻችንን ያቋቋምነው ወጣቶችንን በምድራዊው ህይወትም ሆነ ለእግዚአብሔር በሚሰጡት አገልግሎት ለዘላለም ብቁና ጠቃሚ አድርገው እንዲቀርጹና ማንኛውንም የጠላት ፈተና ተቋቁመው ማለፍ እንዲችሉ ነው፡፡Counsels to Teachers, p. 495. ChSAmh 89.2

አምላካዊውን ፈቃድ ለማያውቁትና እየጠፉ ላሉት አገልግሎት ለመስጠት ሲል ዕውቀት ለማግኘት በጽኑ የሚታገለው ታማኝ እግዚአብሔር ለሰብዓዊ ፍጡር ያለውን ታላቁን ዓላማ ወደ ፍጻሜ በማምጣቱ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ይገኛል፡፡ ሌሎችን ለመባረh በሚያበረከተው ከራስ ወዳድነት የጸዳ አገልግሎት ከፍ ያለውንና ፍጹም የሆነውን hርስቲያናዊ ሥነ ትምህርት ይጋራል፡፡--Counsels to Teachers, p. 545. ChSAmh 89.3

በትምህርት ቤት ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ መልእክቱን ለዓለም ለመስጠት ለሚንቀሳቀሱ፣ ሥራውን ወደፊት ለሚገፉ፣ ጠንካራ፣ ቀናኢ፣ መሥዋዕትነት ለሚከፍሉ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ጌታ ጥሪውን ያቀርባል፡፡Counsels to Teachers, p. 549. ChSAmh 90.1