የክርስቲያን አገልግሎት

62/246

ሥዕላዊ ማሳያ

በሕልሜ አንድ ሰው ነጭ ሸማ አምጥቶ--እንደ ሰዉ የአካል መጠን ጸባይና የሕይወት ፈርጅ ለሁሉም በልክ እየቆረጥኩ፣ የማያስፈልገውን ክፍል እያወጣሁ ለሚፈለግበት ጊዜ ዝግጁ አድርጌ እየሰቀልኩ እንዳስቀምጥ ተነግሮኝ ነበር፡፡ እንድቆርጣቸው ከታዘዝኳቸው ውስጥ አብዛኞቹ ዋጋ ቢስና የማይገቡ እንደሆኑ ተሰምቶኝ ነበር፡፡ እጄ ላይ የነበረው ሸማ ለመጨረሻ ጊዜ የምቆርጠው እንደሆነ ብጠይቅ ገና እንደሚቀር ተነገረኝ፡፡ የያዝኩትን ስጨርስ ሌሎች የምቆርጣቸው እንዳሉ ተመለከትኩ፡፡ ከፊት ለፊቴ የተከመረው የሥራ ብዛት ተስፋ አስቆራጭ ስሜት ፈጠረብኝ፡፡ ለሌሎች ሸማ በመቁረጥ ሥራ ላይ ከተሰማራሁ ሃያ ዓመታት ቢያልፉኝም ሥራዬ ምስጋና፣ አድናቆት ወይም መልካም ፍጻሜ ሲያገኝ መመልከት አልቻልኩም፡፡ በተለይ አንዲት ሴት ለሸማው ተገቢውን ዋጋ እየሰጠች አለመሆኗንና እርሷ እንድትቆርጠው መስጠት የጊዜና የሸማ ብክነት እንደሚያስከትል ሸማውን አምጥቶ እንድቆርጥ ለነገረኝ ሰው አስታወቅኩት፡፡ ሴትየዋ እጅግ ደኻ፣ አነስተኛ ዕወቀትና ንጽህና የጎደለው ልማድ ስላላት ብዙም ሳትቆይ ማበላሸቷ አይቀርም፡፡ ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰልኝ “ሸማዎቹን በልክ ቁረጪ፡፡ ለአንቺ የተሰጠው ተግባር ይህን ማድረግ ነው፡፡ ኪሳራው የአንቺ ሳይሆን የእኔ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ ሰው አይመለከትም፡፡ የሚሠራውን ሥራ ንድፍ የሚያወጣ አምላክ እንደመሆኑ ይሄኛው ወይም ያንኛው--የቱ የከበረ እንደሚሆን አታውቂም፡፡ ሆኖም በስተመረሻ ብዙዎች እንዲህ ያሉ ነፍሳት ወደ መንግሥተ ሰማይ ሲገቡ ሌሎች በበረከት የተሞላ ምድራዊ ሕይወት የኖሩና ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያስችሏቸውን አያሌ መልካም ዕድሎች ያልተጠቀሙ ግን ይተዋሉ፡፡-Testimonies, vol. 2, pp. 10, 11. ChSAmh 87.4

ኮዳ ጀበርናቸውን በጀርባቸው ያነገቱ ወታደሮች ሸክማቸውን አውርደው ራሳቸውን ለሰዓታት እንዴት እንደሚያሳርፉም ሆነ ተመልሰው በፍጥነት ወደ ሰልፍ እንደሚገቡ የሚረዳቸውን ወታደራዊ ሥልጠና ይወስዳሉ፡፡ መሣሪያዎቻቸውን በፍጥነት ማንገትና መወደር፣ እንዴት በጠላት ላይ ውጊያ እንደሚከፍቱም ሆነ በዘዴ እንደሚንቀሳቀሱ ይለማመዳሉ፡፡ ሰዎች በማንኛውም ድንገተኛ ወቅት ብቃት እንዲኖራቸው የሚያዘጋጃቸው ሥልጠና እንደቀጠለ ነው፡፡ ታዲያ ለልዑል አማኑኤል እየተዋጉ የሚገኙ ወታደሮች መንፈሳዊ ተጋድሎበጽናትም ሆነ በጥንቃቄ ያነሰ ሊሆን ይገባል?--Gospel Workers, p. 75. ChSAmh 88.1