የክርስቲያን አገልግሎት

64/246

እየተማሩ በተግባር መግለጽ

ተማሪዎች በዙሪያቸው ያለው ማኅበረሰብ ከሚያሻው ቀዳሚ መንፈሳዊ ነገር ጋር መተዋወቅ እንዲችሉና የቀለም ትምህርታቸው የተሟላ እንዲሆን ተግባራዊ የወንጌል ሥራ የሚሠሩበት ጊዜ ሊመደብላቸው ይገባል፡፡ በትምህርት ቤት ያገኙትን ዕውቀት ጥቅም ላይ የሚያውሉበት የጊዜ እጥረት እንዳይገጥማቸው ጫና የበዛበት ትምህርት እንዳይሰጣቸው ጥንቃቄ ማድግ ተገቢ ነው፡፡ ጽኑ የወንጌላዊ ጥረት እንዲያበረክቱ ማበረታታትና በተሳተ አስተምህሮ ከሚገኙ ሰዎች ጋር ትውውቅ ፈጥረው ወደ እውነት ሊያመጧቸው የሚችሉበትን መንገድ መሻት ያስፈልጋል፡፡ ትሁት አገልግሎት ሲሰጡ፣ hርስቶስ ጥበብ እንዲሰጣቸው ከልባቸው ሲሹና በጸሎት ተግተው _ ሲጠባበቁ--የገዛ ሕይወታቸውን ያበለጸገውን ዕውቀት ለሌሎች ያካፍላሉ፡፡--Counsels to Teachers, pp. 545, 546. ChSAmh 90.2

የሚቻል ከሆነ ተማሪዎች በትምህርት ዓመቱ መሃል በከተማ የወንጌል አገልግሎት ተሳታፊ ይሆኑ፡፡ በሚገኙበት አቅራቢያ ወዳለ ከተማና መንደር ጎራ ብለው የወንጌል አገልግሎት ይስጡ፡፡ በቡድን በቡድን እየሆኑ ክርስቲያናዊ በጎ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ፡፡ ተማሪዎች ዛሬ ለእግዚአብሔር እያበረከቱት ያለውን የውዴታ ግዴታ እጅግ ግዙፍ ከሆነ ምልከታ አኳያ ሊያጤኑት ይገባል፡፡ ትምህርት ጨርሰው ለእግዚአብሔር ሰፊ ሥራ የሚሠሩበትን ጊዜ መመልከት ሳይሆን ነገር ግን በትምህርት ቤት ሕይወታቸው እንዴት የክርስቶስን ቀንበር ተሸክመው ራስ ወዳድ ያልሆነ አገልግሎት ለሌሎች እንደሚሰጡ ጥናት ያድርጉ፡፡ --Counsels to Teachers, p. 547. ChSAmh 90.3

የወጣቶችን አእምሮ እጅግ አስፈላጊ በሆኑ ትምህርቶች መሙላት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ _ እነርሱም የተቀበሉትን እንዴት ማካፈል እንደሚኖርባቸው የግድ መማር ይኖርባቸዋል፡፡-Counsels to Teachers, p. 545. ChSAmh 91.1

የኮሌጆቻችንና የማሰልጠኛ ተቋሞቻችን ምሩቃን ወንጌላውያን ለአገልግሎት ወደ ሩቅ ስፍራዎች እንላካቸው፡፡ ተማሪዎች በትምህርት ቤት እያሉ ለዚህ ሥራ ሊያዘጋጃቸው የሚችለውን እያንዳንዱን ዕድል ተጠቅመው ራሳቸውን ያሻሽሉ፡፡ ከሰማይ ጋር ያላቸው ቁርኝት ትክክለኛነት የሚታይበትና ራሳቸውን ከሥራው ጋር የማስማማታቸው ችሎታ የሚፈተሽበትፈተና የሚጋፈጡበትና የሚያልፉበት ጊዜ ይህ ነው፡፡ --Counsels to Teachers, p. 549. ChSAmh 91.2