የክርስቲያን አገልግሎት

61/246

መለኮታዊው መለኪያ

ዕውቀታችንን ለሌሎች የማካፈል ዓላማን መርኅ ያደረገ በቂ ትምህርት እንድናገኝ የጌታ ምኞት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው በየትኛው ስፍራ ወይም እንዴት ለእግዚአብሔር ለመሥራት ወይም ለመመስከር እንደሚጠራ ማንም ማወቅ አይችልም፡፡ በሰዎች ምን እንደሚሠራ የሚያውቀው ሰማያዊው አባታችን ብቻ ነው፡፡ ደካማው እምነታችን ለይቶ መመልከት ያልቻላቸው ከፊት ለፊታችን የተደቀኑ መልካም ዕድሎች አሉ፡፡ አምላካዊውን ስም ሊያወድስ የሚችለውን የቃሉን እውነት ከፍ ባለ ደረጃ ለተቀመጡ ምድራዊ ባለሥልጣናት ሳይቀር እንዳስፈላጊነቱ ማቅረብ እንድንችል አእምሮአችን ሥልጠና ሊወስድ ይገባል፡፡--Christ’s Object Lessons, pp. 333, 334. ChSAmh 87.2

በአምላካዊው የወይን ስፍራ ሄደው ለመሥራት ራሳቸውን ሲያዘጋጁ የነበሩ እነማን ይሆኑ? እግዚአብሔር መhሊታቸውን በማይጠቀሙ ደስተኛ አይደለም፡፡ ይልቁንም እርሱ የሰጠንን መhሊቶች እስከ ጥግ ተጠቅመን ምርጥ አገልግሎት እንድንሰጠው ይሻል፡፡--Review and Herald, April 2, 1889. ChSAmh 87.3