የክርስቲያን አገልግሎት

240/246

ምዕራፍ 27—አገልግሎታችን የሚያስገኝልን ሽልማት

በዋጋ ሊተመን የማይችል

እግዚአብሔርን ማገልገል ዋጋ የሌለው ከንቱ ሥራ አይደለም፡፡ vይወታቸውን ለእርሱ _ አገልግሎት ላዋሉ በዋጋ ሊተመን የማይችል ሽልማት ተዘጋጅቶአል፡፡—Testimonies, vol. 4, p. 107. ChSAmh 368.1

ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚውል ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕትነት “ወደር በሌለው የጸጋው ባለጠግነት” መጠን ይከፈለዋል፡፡ The Desire of Ages, p. 249. ChSAmh 368.2

በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር መሥራታችን ለሚመጣው ዓለም ታላቅ ኃይል በመሆን ልዩ መብትና ጥቅም ያስገኝልናል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 361. ChSAmh 368.3