የክርስቲያን አገልግሎት
ለሽልማት ብቁ የሚደርገው መስፈርት
ለእግዚአብሔር የሚውለው አገልግሎት ስፋትና መጠን የሚለካው ሥራው ላይ በጠፋው ጊዜ ሳይሆን ለአገልግሎቱ ምክንያት በሆነው መንፈስ ነው:: Testimonies, vol. 9, p. 74. ChSAmh 368.4
በመለኮት የሚመራው የህይወታቸው ግስጋሴ ስኬት መለካት የሚችለው ጥቅም ላይ ባዋሉት መክሊት መጠን ነው፡፡ ለጌታ የሚሰጡት ታማኝና ጽኑ አገልግሎት ወደፊት ከሚቀበሉት ሽልማት ጋር ተመጣጣኝ ነው፡Review and Herald, March 1, 1887. ChSAmh 368.5
ጌታ በዚህ ምድር የሚሠራ ታላቅ ሥራ አለው፡፡ ዛሬ እርሱን በማገልገል ኃላፊነታቸውን በታማኝነት ለወጣት ፈቃደኞች ለሆኑ የከበረ ዘላለማዊ ህይወት ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 330. ChSAmh 369.1
በአስራ አንደኛው ሰዓት ወደ ወይን ተhሉ መጥተው የሥራ ዕድል የተሰጣቸው ሰዎች አመስግነዋል፡፡ እነርሱን ተቀብሎ ሥራውን በሰጣቸው ኃላፊም ልባቸው ፍጹም ረhቶአል፡፡ በዕለቱ ፍጸሜ ላይ የቤቱ ባለቤት የሙሉ ቀን ሒሳብ ሲከፍላቸው ሲመለከቱ፤ ይህን የሚያህል ክፍያ እንደማይገባቸው ያውቁ ስለ ነበር እጅግ ተደነቁ፡፡ በቀጣሪያቸው የፊት ገጽታ ላይ የተመለከቱት ደግነት በደስታ እንዲሞሉ አደረጋቸው፡፡ እነዚህ የአሥራ አንደኛው ሰዓት ተቀጣሪዎች የቤቱን ባለቤት መልካምነት ወይም የተቀበሉትን ለጋስ ክፍያ ፈጽሞ ሊረሱ አልቻሉም፡፡ ChSAmh 369.2
ለአገልግሎት የማይገባ እንደነበር የሚያውቀው >ጢአተኛ በአሥራ አንደኛው ሰዓት ወደ ጌታ የወይን ተክል መግባቱ ተመሳሳይ ስሜት ይፈጥርበታል፡፡ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችልበት ጊዜ አጭር እንደመሆኑ በጌታ የተዘጋጀው ሽልማት ለእርሱ እንደማይገባ ሊሰማው ቢችልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንደተቀበለው ሲመለከት ልቡ በደስታ ይሞላል፡፡ ከhርስቶስ ጋር በተባባሪነት አገልግሎት የሚሰጥበት ልዩ መብትና ጥቅም በማግኘቱ እያመሰገነ በትህትናና በታማኝ መንፈስ ይሠራል፡፡ እግዚአብሔር እንዲv ያለውን መንፈስ በመሸለም ደስ ይሰኛል፡፡--Christ’s Object Lessons, pp. 397, 398. ChSAmh 369.3