የክርስቲያን አገልግሎት

239/246

ውጤቶቹን ለእግዚአብሔር መተው

መልካም የሆነው ዘር እምብዛም ትኩረት ሳይሰጠው--በቀዝቃዛ፣ ራስ ወዳድና ዓለማዊ ልብ ውስጥ ሥር ሊሰድ ይችላል፡፡ ውሎ አድሮ የእግዚአብሔር ንፈስ ለዚህ ነፍስ እስትንፋስ ሲሰጠው ተሸሽጎ የነበረው ዘር ቡቃያ ሆኖ ያብብና በስተ መጨረሻ ለእግዚአብሔር ክብር ፍሬ ያፈራል፡፡ በሕይወት ዘመን አገልግሎታችን ይህ ወይም ያ--የትኛው ብልጽግና እንደሚያገኝ አናውቅም፡፡ ይህ መፍትሔ እንድንፈልግለት ለእኛ የተተወ ጥያቄም አይደለም፡፡ የእኛ ኃላፊነት የተሰጠንን ተግባር በማከናወን ውጤቱን ለእግዚአብሔር መተው ብቻ ነው፡፡ “ጠዋት ላይ ዘርህን ዝራ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፡፡” ታላቁ አምላካዊ ኪዳን እንደሚነግረን “ምድር እስካለች ድረስ የዘር ወቅትና መከር... አይቋረጡም፡፡” ገበሬው በተሰጠው ተስፋ ላይ በመተማን ምድሪቱን አርሶ በዘር እንደሚሸፍን፤ እኛም በተሰጠን አምላካዊ ማረጋገጫ ላይ ተመስርተን ከገበሬው በተመሳሳይ መንፈሳዊውን ዘር እንዘራለን፡፡ “hአፌ የሚወጣው ቃሌ በከንቱ ወደ እኔ _ አይመለስም፤ _ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዓላማ ይፈጽማል፡፡” “ዘር ቋጥረው እያለቀሱ የተሰማሩ ነዶአቸውን ተሸክመው እልል እያሉ ይመለሳሉ፡”— Christ’s Object lessons, p. 65. ChSAmh 367.1