የክርስቲያን አገልግሎት
ድል ኢድራጊው ሕይወት
ለእግዚአብሔር ምስክር መሆን የምንችለው እውነትን በመስበክና መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማደል ብቻ አይደለም፡፡ ክርስቶስን የሚመስል ሕይወት--ለክርስትና ሕይወት ድጋፍ፣ እጅግ ብርቱ ተፋላሚና የግስጋሴ መንስኤ ሲሆን—ርካሽ የክርስትና ጸባይ ግን ይህን ዓለም ከመምሰል በላቀ በዓለም ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ እናስታውስ፡፡ —Testimonies, vol 9, ChSAmh 33.1
ሁሉም መጻሕፍት የተቀደሰ ሕይወት ባለቤት ሊያደርጉን አይችሉም፡፡ ሰዎች የሚያምኑት አገልጋዮች የሚሰብኩትን ሳይሆን ቤተ ክርስቲያን የምትኖረውን ሕይወት ነው፡፡ እጅግ በተደጋጋሚ እንደሚስተዋለው በመድረክ ላይ የሚሰበከው ስብከት ሊያሳድር የሚችለው ተጽእኖ የእውነት ጠበቆች ነን በሚሉ ሰዎች ሕይወት አጸፋዊ ጥቃት ይገጥመዋል፡፡ -- Testimonies, vol. 9, p. 21. ChSAmh 33.2
የክርስቶስ ሕይወት እጅግ ሰፊና ግዙፍ፣ ዳርቻ የሌለው፣ የተጽእኖው አድማስ ከእግዚአብሔር ጋር የተሳሰረና መላውን ሰብዓዊ ቤተሰብ ያካተተ ነበር፡፡ ሰው ለራሱ ሊኖር ያልቻለውን ሕይወት እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ተጽእኖ ፈጣሪ አደረገው፡፡ እኛ እያንዳንዳችን የግዙፉ አምላካዊ አካል እንደመሆናችን ከባልንጀራችን ጋር በግል የተሳሰርንና በጋራ ግዴታዎች ስር የቆምን ነን፡፡ የአንዱ ደኅንነት በሌላው ላይ ተጽእኖ ስላለው ማንም ሰውከሰው ተገንጥሎ መቆም አይችልም፡፡ አንዱ ለሌላው ደኅንነት አሰፈላጊ ሆኖ እንዲሰማው መሆኑና ደስታቸው የተሟላ እንዲሆን መጣሩ የእግዚአብሔር ዓላማ ነው:፡ --Christ’s Object Lessons, p. 339. ChSAmh 33.3
መጽሐፍ ቅዱሳዊው ኃይማኖት በመጽሐፍ ቅዱስ ሽፋን ውስጥ ወይም በቤተ ክርስቲያን ግድግዳዎችም ላይ ተወስኖ መቀመጥ የለበትም፡፡ አልፎ አልፎ ለተለየ ጉዳይ ስንፈልገው ብቻ ገለጥ አድርገን መልሰን በጥንቃቄ የምናስቀምጠው _ ሳይሆን፤ ይልቁንም በያንዳንዱ የንግድ ሥራችንና በሁሉም ማኅበራዊ ግንኙነት ሕይወታችን የሚታይና የየዕለት ሕይወታችንን የሚቀድስ ሊሆን ይገባል፡፡—The Desire of Ages, pp. 306, 307. ChSAmh 34.1
በዚህ ዓለም በሕዝቦቹ ውስጥ ከብሮ መታየት የእግዚአብሔር ዓላማ ነው፡፡ የክርስቶስን ስም የተሸከሙ በአስተሳሰብ፣ በቃልና በተግባር እርሱን እንዲወክሉ ይጠብቃል፡፡ አስተሳሰባቸው የጠራ፣ _ ከአንደበቶቻቸው የሚወጡ ቃላት የከበሩና የሚያንጹ፣ በዙሪያቸው ያሉተን ወደ አዳኙ የሚስቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የክርስቶስ ኃይማኖት ከሚያደርጓቸውና ከሚናገሯቸው ነገሮች ጋር ድርና ማግ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡ እያንዳንዱ የንግድ ሥራ ግብይታቸው በእግዚአብሔር መገኘት መልካም መአዛ የተሞላ ይሁን፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 21. ChSAmh 34.2
አማኙ የንግድ ሰው ስለ እምነቱ ሲል ለጌታው ክብር የሚሰጥ ሥራ ይሥራ፡፡ በሄደበት ሁሉ ኃይማኖቱ የክርስቶስን መንፈስ ገልጦ የሚያሳይ ይሁን፡፡ በመካኒክነት የተሰማራው ባለሙያ በይሁዳ ከተሞች ራሱን ዝቅ አድርጎ አድካሚ ሥራ ይሠራ የነበረውን ጌታ በትጋትና በታማኝነት ይወክለው፡፡ የክርስቶስ ተብሎ የተሰየመ ማንኛውም ሰው ሰዎች የእርሱን መልካም ሥራ ተመልክተው _ ለፈጣሪውና ለአዳኙ ክብር እንዲሰጡ የሚያደርግ ሥራ ይሥራ፡፡ --Bible Echo, June 10, 1901. ChSAmh 34.3