የክርስቲያን አገልግሎት

10/246

ሴቶች በወንጌል ሥራ

ሴቶችም ሆኑ ወንዶች የተደበቀውን እውነት ለሰዎች ይፋ በሚያደርግየሥራ መስክ መሰማራት ይችላሉ፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ተገቢውን የሥራ ድርሻቸውን ሲወስዱ ጌታ በእነርሱ ውስጥ ይሠራል፡፡ በኃላፊነት የሚሠሩት ሥራ እንዳላቸው የሚሰማቸው ከሆነና በእግዚአብሔር መንፈስ ተጽእኖ የሚያıለግሉ ከሆነ ለዚህ ዘመን የሚጠየቀው መተማመን አላቸው ማለት ነው፡፡ አዳኙ ለአገልግሎት ራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው በሚሰጡ ሴቶች ላይ ፊቱን ያበራል፡፡ ይህ ደግሞ ከወንዶች የላቀ ኃይል ስለሚሰጣቸው ወንዶች በቤተሰብ መሃል ሊሠሩት የማይችሉትን ወደ ውስጠኛው ሕይወት መድረስ የሚችል ብርቱ ሥራ መሥራት እንዲችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ከወዶች ይልቅ እነርሱ ይበልጥ ወደ ወገኖች ልብ መቅረብ ይችላሉ፡፡ የሴቶች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ይፈለጋሉ፡፡ ጥንቁቅና ትሑት ሴቶች በቤታቸው ላሉ ወገኖች እውነትን በማስረዳትና በመግለጥ መልካም አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ ይህ በሚገባ የተብራራ የእግዚአብሔር ቃል የእርሾ ሥራውን በመሥራት በሚያሳድረው ተጽእኖ መላው ቤተሰብ ይለወጣል፡፡-- Testimonies, vol. 9, pp. 128, 129. ChSAmh 35.1

ለእግዚአብሔር የሚሠሩ ሁሉ የማርታና የማርያም ቅይጥ መለያ ባህሪ የሆነው--ለአገልግሎት ፈቃደኛነትና ለእውነት ልባዊ ፍቅር ሊኖራቸው ይገባል፡፡ እኔነትና ራስ ወዳድነት ፍጹም መወገድ ይኖርባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ቅን፣ ጠንቃቃና አርቆ አሳቢ፣ ለሥራ የተነሳሳ ልብ፣ ርኅሩኅና ለመርኅ እውነተኞች ለሆኑ አገልጋይ ሴቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡ አእምሮአቸውን ከእኔነትና ግላዊ ምቾት ከሚሰጣቸው ነገር ላይ አንስተው ክርስቶስን ማዕከል ያደረጉ የእውነት ቃላቶችን የሚናገሩ፣ መድረስ ከሚችሏቸው ሰዎች ጋር የሚጸልዩና ለነፍሳት መለወጥ ለሚሠሩ ጽኑ ሴቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 118. ChSAmh 35.2

እህቶች የኅትመት ውጤቶቻችን ለሆኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች አንባቢ ደንበኞችን በማፈላለግ ሰማያዊውን ብርሃን ወደ ብዙዎች አእምሮ የማድረስ ሥራ መሥራት ይችላሉ፡፡--Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 35.3

ከእውነት ሚዛን አኳያ የሚበይኑ የተከበሩ የግብረገብ ጀግኖች ሴቶች አሉ፡፡ ሕሊናቸው እውነትን በመቀበሉ ብልሃታቸው፣ ጥንቃቄአቸውና የመገንዘብ ችሎታቸው ለጌታቸው ውጤታማ ሠራተኞች ያደርጋቸዋል፡፡ hርስቲያን ሴቶች ለአገልግሎተ ተጠርተዋል፡፡--Review and Herald, Dec. 19, 1878, ChSAmh 36.1

እህቶቻችን መንፈሳዊ ጽሑፎቻችንንና በራሪ መልእክቶቻችንን አግኝተው ባነበቡ ሰዎች እውነተኛ ስሜት ሪያ ንቁ የሥነ ጽሑፍ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ. . . በመርኅዎች ላይ ጽኑ አቋም ያላቸውና ውሳኔ ሰጪ ሴቶች ይፈለጋሉ፤ በመጨረሻው ዘመን የምንኖር ሕዝቦች ለመሆናችን ብርቱ አጽንኦት የሚሰጡና ለዓለም መሰጠት ያለበት የመጨረሻው የከበረ የማስጠንቀቂያ መልእክት ያለን ሕዝቦች መሆናችንን የሚያምኑ ሴቶች ይፈለጋሉ. . . መንፈሳዊ በራሪ ጽሑፎችን ለማደልና ለወንጌል ሥራ እግዚአብሔር ሊጠቀምባቸው የሚችል ወገኖች እነዚህ ናቸው. . . እነዚህ ወገኖች ጥንቃቄ በተሞላው ኃላፊነት በነፃ የሚታደሉ እንደ Signs of the Times ያሉ መጽሔቶችን በማሰራጨት በብዙ መልኩ ለእግዚአብሔር የከበረ ሥራ መሥራተ ይችላሉ፡፡--Review and Herald, Dec. 19, 1878. ChSAmh 36.2

እኔ በግሌ ሴቶች ለመንፈሳዊ ሥራ ተመርጠው ወይም በቢሮ ውስጥ ገብተው መሥራት አለባቸው ብዬ አልመክርም፡፡ ሆኖም በወንጌላዊነት፣ በርቀት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አስተማሪነት፣ በራሪ ጽሑፎችን በማደል፣ አንባቢያን ለዚህ ዘመን ገጣሚ የሆኑ የተከበሩ መልእክቶችን ያዘሉ መጽሔቶችንና ጋዜጦችን ለወር ወይም ለዓመት የደንበኝነት አባል እንዲሆኑ በመጠየቅና በማግባባት ታላቅ ሥራ መሥራት ይችላሉ፡፡-Review and Herald, Dec. 19, 1878. ChSAmh 36.3

ሃያ ሴቶች ቢኖሩና ይህን የተቀደሰ ተልዕኮ የራሷ አድርጋ ለሥራው ከፍተኛ ዋጋ የሰጠችው አንዷ ብትሆን ብዙዎች ተለውጠውና እውነትንአግኝተው መመልከት ይኖርብናል፡፡--Review and Herald, Jan, 2, 1879. ChSAmh 36.4

ከክርስቶስ የዋህ ልብ ጋር ሕብረት ፈጥረው ሳይመጻደቁ የሚሠሩ ታማኝና የዋህ፣ ባገኙት ቦታ ሁሉ ለነፍሳት ደኅንነት መሥራት የሚችሉ ሴቶች አሁን ይፈለጋሉ፡፡--Review and Herald, Jan. 2, 1879. ChSAmh 37.1

በመቶዎች የሚቆጠሩ እህቶቻችን ዛሬ የሥራው ተሳታፊ መሆን ይችሉ ነበር፡፡ ራሳቸውም ሆኑ ልጆቻቸው ረዘም ላለ ጊዜ ሊጠቀሙበት የሚችሉት ዓይነት ቀለል ያለና ንጹሕ ልብስ በመልበስና ከአጉል መሽቀርቀር በመቆጠብ ጊዜአቸውን ከታይታ ነፃ ለሆነ የወንጌል ሥራ ሊያውሉ ይገባል፡፡ ምናልባትም በርቀት ላሉ ወዳጆች ደብዳቤ መጻፍ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ እህቶች አንድ ላይ ተሰባስበው ስለ ተሻለ በሥርዓት የሚመራ አገልግሎት ሊመክሩ ይገባል፡፡ ለእግዚአብሔር በስጦታ ለማቅረብም ሆነ በራሪ ጽሑፎችን አዘጋጅቶ ለወዳጆች ለመላክ ገንዘብ መቆጠብ ይቻላል፡፡ አሁን ወደ አገልግሎት ያልገቡ ሁሉ ሥራውን ሊቀላቀሉ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነች የሚሰማት እያንዳንዷ እህት እርሷ ልትደርስባቸው የምትችላቸውን ሁሉ የመርዳት ኃላፊነት እንዳለባት ይታወቃት፡፡Review and Herald, Dec. 12, 1878. ChSAmh 37.2

እህቶች ጠለቅ ያለውን የሥራ ድርሻ ላለመሸከም አያሌ ምክንያቶችን ሲደረድሩ መኖራቸው ገሐድ ቢሆንም ነገር ግን አገልግሎት የክርስትናን ተሞክሮ ወደ ፍጽምና የሚያመጡበት አስፈላጊ ሥርዓትና መንገድ ነው፡፡ ሴቶች በሰበካ በመታቀፍም ሆነ በግላቸው እምነታችንን በትክክል የሚወክሉ በራሪ ጽሑፎችን በማደል ሥራ መሰማራት ይችላሉ፡፡Review and Herald, Dec. 12, 1878. ChSAmh 37.3

እህቶች ሆይ--ሁል ጊዜ ንቃት ለሚጠይቀው የወንጌል ሥራ የዛላችሁና የደከማችሁ አትሁኑ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለመመስረት ፈቃዳችሁ እስከሆነ ድረስ ሥራው ሁላችሁንም በሚገባ የሚያሳትፍ ነው፡፡ መልእክትከመጻፋችሁ አስቀድሞ የዱሩ ቅርንጫፍ በእውነተኛው የወይን ተhል ላይ ተጣብቆና ለእግዚአብሔር ክብር ፍሬ አፍርቶ ስኬታማ ሆን እንድትችሉ ሁል ጊዜ ልባችሁን በጸሎት ወደ እግዚአብሔር አቅኑ፡፡ ትሁት በሆነ ልብ የዚህ ሥራ ተካፋይ የሚሆኑ ሁሉ ራሳቸውን በጌታ የወይን ተክል ዙሪያ ያለማቋረጥ ያስተምራሉ፡፡Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 38.1