የክርስቲያን አገልግሎት

8/246

ከተራ ማንነት መጠራት

ሰዎች የተጠሩበትን የአገልግሎት ኃላፊነት ሊወስዱ ይገባል፡፡ አዳኙ የሰብዓዊውን ሐዘን እንደተጋራ እነርሱም ተመሳሳይ ርኅራኄ ሲያሳዩ በእምነት አብሮአቸው እየሠራ እንደሆነ ያያሉ፡፡ --Gospel Workers, p. 38. ChSAmh 30.3

በእርሻ ሥራም ሆነ በንግድ እንቅስቃሴ ወይም በየትኛውም መስክ የተሰማሩ በቅርብም ሆነ በሩቅ ያሉ ወገኖች በአገልግሎት ልምድ ካላቸው ተገቢውን ትምህርት እንዲቀስሙ ጥሪ ይቀርብላቸዋል፡፡ የውጤታማ አገልግሎት ሥልጠና እውነትን በኃይል እንዲያውጁ ያስችላቸዋል፡፡ እጅግ አስደናቂ በሆነ የመለኮት ጣልቃ ገብነት መሰናክል የሆነው ተራራ ተወግዶ ወደ ባሕር ይጣላል፡፡ ለምድር ነዋሪዎች አንገብጋቢ የሆነው መልእክት ይደመጣል፣ ይስተዋላልም፡፡ ሰዎች የእውነትን ምንነት ይረዳሉ፡፡ መላው ምድር የማስጠንቀቂያውን ድምጽ እስኪ ሰማ ድረስ ሥራው ያለማቋረጥ ወደፊት ይገሰግሳል፡፡ እነሆ በዚያን ጊዜ መጨረሻው ይመጣል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 96. ChSAmh 31.1

እግዚአብሔር በመደበኛ ትምህርት ቤቶች ገብተው ያልተማሩትን ሰዎች መጠቀም ይችላልይጠቀምባቸዋልም፡፡ ይህን የሚያደርገውን አምላካዊ ኃይል መጠራጠር አለማመንን ይገልጣል፤ ለእርሱ አንዳችም ነገር የማያዳግተውን ሁሉን ቻይ አምላh መወሰን ይሆናል፡፡ ተጠራጣሪነትን በማጎልበት አያሌ የቤተ ክርስቲያን ብርታትና ጉልበቶች ያለ ጥቅም እንዲቀመጡና መንፈስ ቅዱስ በሰዎች እንዳይሠራ መንገዱን ይዘጋል፡፡ ለክርስቶስ በየፈርጁ ለመሥራት ፈቃደኞች የሆኑትንና ለአገልግሎት ጉጉት ያደረባቸውን ወገኖች ሥራ ፈት አድርጎ ያስቀምጣል፤ ብዙዎች ይህ ቅን ዕድል ቢሰጣቸው ከእግዚአብሔር ጋር ውጤታማ ሥራ መሥራት ይችሉ የነበረ ቢሆንም ይህ ሁኔታ ወደ ሥራው እንዳይገቡ ተስፋ ያስቆርጣቸዋል፡፡ --Gospel Workers, pp. 488, 489. ChSAmh 31.2

ለወንጌል ግስጋሴ መሥራት ለእያንዳንዱ ነፍስ የተሰጠ መብትና ልዩ ጥቅም ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ ጸጋና ዕውቀት በሙላት ያድጋሉ፡፡ እውነትን እናምናለን የሚሉ ሁሉ ያለ ኃይላቸውን፣ ችሎታቸውንና የተሰጣቸውን መልካም ዕድል ተጠቅመው ለመማርና ያወቁትን በተግባር ለማሳየት ቢጠቀሙበት በክርስቶስ በጠነከሩና ብርቱ በሆኑ ነበር፡፡ ገበሬ፣ ነጋዴ፣ መምህር፣ መጋቢ፣ ወይም በየትኛውም የሥራ መስክ የተሰማራን ብንሆን ራሳችንን ለእግዚአብሔር ቀድሰን ከሰጠን ለሰማያዊው ጌታ ብቃት ያለን ሠራተኞች እንሆናለን፡፡-Testimonies, vol. 6, p. 423. ChSAmh 31.3

በመምህርነት፣ በኮንስትራክሽን፣ በማኑፋክቸሪንግ ወይም በግብርና ሙያ የተሰማሩ ባጠቃላይ በቂ መክሊት ያላቸው የቤተ ክርስቲያን አባላት በኮሚቴዎች ወይም በሰንበት ትምህርት አስጠኚነት ወይም ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች ጋር ትስስር ያላቸውን የተለያዩ የሥራ ክፍተቶች በመሙላት ቤተ ክርስቲያንን ለሚያንጽ የወንጌል ሥራ ሊዘጋጁና ተሳታፊ ሊሆኑ ይገባል፡፡Review and Herald, Feb. 15, 1887. ChSAmh 32.1

ክርስቶስ ለሥራው ግስጋሴ አንደበተ ርቱዕ የአይሁድ ሥነ መለኮት ትምህርት ቤት ምሩቃን ወይም የሮም ብርቱ ኃይል አላስፈለገውም፡፡ የሥራው ጌታ ተመጻዳቂዎቹን የአይሁድ መምህራን አልፎ ዓለምን ዳር እስከ ዳር ያነቃነቀውን እውነት ይሰብኩና ያውጁ ዘንድ ትሁቶቹንና ያልተማሩትን ወገኖች መረጠ፡፡ አነዚህ ወገኖች የቤተ ክርስቲያን መሪ ለመሆን የሚያስችላቸውን ሥልጠናና ትምህርት እንዲወስዱና እነርሱም በተራቸው ሌሎችን በማሠልጠን የወንጌልን መልእክት ይዘው የሚወጡበትን ተልዕኮ መስጠት ዓላማው ነበር፡፡ በሥራቸው ስኬት ማግኘት እንዲችሉ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሊሰጣቸው የተገባ ነበር፡፡ ወንጌል መሰበክ የሚኖርበት በሰው ብርታት ወይም ጥበብ ሳይሆን ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ነበር፡፡-The Acts of the Apostles, p. 17. ChSAmh 32.2

አዳኙ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” የሚለውን ተልዕኮ የሰጣቸው አብዛኞቹ ወገኖችበትvትና የተሞላ ማንነት የነበራቸው፣ ጌታቸውን እንዲወዱ የተማሩና ከራስ ወዳድነት የጸዳ ምሳሌውን ለመከተል ቁርጥ ሃሳብ ያደረጉ ወንዶችና ሴቶች ነበሩ፡፡ በየሱስ ምድራዊ አገልግሎት ወቅት ከእርሱ ጋር አብረው በነበሩ ራሳቸውን ባዋረዱ ትሑታንና በደቀ መዛሙርቱ ላይ የከበረ አመኔታ ተጥሎ ነበር፡፡ በክርስቶስ አማይነት የተገኘውን አስደሳቹን የደኅንነት የምስራች ለዓለም ማዳረስ ነበረባቸው፡፡--The Acts of the Apostles, pp. 105, 106, 26 ChSAmh 32.3