የክርስቲያን አገልግሎት

188/246

ልጆች መንፈሳዊና አካላዊ ሸክሞችን እንዲጋሩ መፍቀድ

ሁሉም የበኩሉን አንድ ነገር ማበርከት ይችላል፡፡ አንዳንዶች “የቤት ሥራው ፋታ አልሰጥ ብሎኝ፣ የልጆቼ ነገር ጊዜ አሳጥቶኝ” እያሉ ለራሳቸው .ምክኒያት ይሰጣሉ፡፡ ወላጆች ሆይ—ልጆቻችሁ ለጌታ እንድትሠሩ የበለጸገ ኃይልና ብርታት ሊሆኗችሁ ይገባል፡፡ ህጻናት በዕድሜ አነስተኞቹ የጌታ ቤተሰብ አባላት ናቸው፡፡ ራሳቸውን ለፈጠራቸውና ለዋጃቸው ጌታ ቀድሰው እንዲሰጡ ምሪት ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ አካላዊ ጉልበታቸው፣ አእምሮአቸውና ነፍሳቸው የእርሱ መሆኑን መማር ይኖርባቸዋል፡፡ በአያሌ ከራስ ወዳድነት መንፈስ በራቁ አገልግሎቶች ተሳታፊ በመሆን የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ የሚረዳ ሥልጠና ይሰጣቸው፡፡ ልጆችዎ መፍትሔ እንጂ እንቅፋት እንዲሆኑ አይፍቀዱ፡፡ ልጆች መንፈሳዊውንም ሆነ አካላዊውን ሸክም ከወላጆቻቸው ጋር መካፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሌሎችን በመርዳታቸው የገዛ ደስታቸውንና ጠቃሚነታቸውን ያበለጽጋሉ፡፡ Testimonies, vol. 7, p. 63. ChSAmh 286.3