የክርስቲያን አገልግሎት
ብርቱ አርአያነት ያለው የhርስቲያን ቤት ተጽእኖ
በሥነ ሥርዓት ታርሞና ተኮትኩቶ የተያዘ የክርስቲያን ቤተሰብ እምነተ ቢሶች እንኳን ሊያስተባብሉት የማይችሉትን እውነት ይዞአል፡፡ በቤተሰብ መሃል እውን እየሆነ ያለው--በልጆች ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ሊያመጣ የሚችለው ነገር፤ በእርግጥም የአብርሃም አምላክ አብሯቸው እንዳለ ሁሉም እንዲረዳ የሚያስችል እውነታ ነው፡፡ ክርስቲያን ነን የሚሉ-ትክክለኛው >ይማኖታዊ ምሳሌነት በቤታቸው ቢታይ-ለበጎው ነገር ግዙፍ ተጽእኖ ማሳደር በመቻል በእርግጥም ‹‹የዓለም ብርሃን›› ይሆናሉ፡፡ የኃይማኖት አባቶችና ነቢያት ገጽ 158-159፤ ChSAmh 287.1
የቤት ውስጥ ተልዕኮ ከቤተሰቡ አባላት ባሻገር አልፎ ይሄዳል፡፡ የክርስቲያን ቤት ምርጥ የሆነውን የሕይወት እውነተኛ መርኅ የሚያሳይ ተጨባጭ ትምህርት ቤት ሊሆን ይገባል፡፡ እንዲህ ያለው መገለጫ መልካም ለሆነው ነገር ኃይል ይሆናል፡፡ እውነተኛ ቤት በሰብዓዊው ልብና ሕይወት ላይ የሚኖረው ተጽእኖ ከማንኛውም ስብከት ይልቅ እጅግ የበረታ ነው፡፡ ከእንዲህ ዓይነቱ ቤተሰብ የሚወጡ ወጣቶች የተማሯቸውን ትምህርቶች ለሌሎች ያካፍላሉ፡፡ የተከበሩት የሕይወት መርኅዎች ለሌሎች የቤተሰብ አባላት ይተዋወቃሉ፣ አነቃቂ ተጽእኖዎችም በማኅበረሰቡ ላይ መሥራት ይጀምራሉ፡፡The Ministry of Healing, p. 352. ChSAmh 287.2
በሥርዓት የሚመራና በዲሲፕሊን የታነጻ ቤተሰብ ለዚህ ዓለም መቅረብ የሚችል የክርስትናን ኃይል የሚያሳይ ታላቅ ማስረጃ ነው፡፡አውነት በልብ ላይ ስለሚኖረው ተጨባጭ ኃይል ሕያው ምስክር በመሆን ከማንኛውም ነገር በላቀ እማኝነቱን ይገልጻል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 304. በምድር ያሉ ቤተሰቦች የሰማያዊው ተምሳሌት ይሆኑ ዘንድ የእግዚአብሔር እቅድ ነው፡፡ በአምላካዊው እቅድ መሰረት የተቋቋሙና የሚመሩ የክርስቲያን ቤተሰቦች የክርስትናን ጸባይ በመፍጠርና የጌታን ሥራ ወደ ፊት በማራመድ ረገድ እጅግ ውጤታማ ከሚባሉ ወኪሎቹ መሃል ዋንኞቹ ናቸው፡፡-- Testimonies, vol. 6, p. 430. ChSAmh 288.1
ምናልባት የተጽእኖአችን ስፋትና ጥልቀት ዝቅተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ችሎታችን አነስተኛ፣ ልንጠቀምባቸው የምንችላቸው ዕድሎች ጠባብ፣ የገንዘብ አቅማችን ውሱን ሊሆን ቢችል እንኳ ለቤተሰብ አባላቶቻችን እንድንራ የተሰጠንን ዕድል በታማኝነት ጥቅም ላይ ማዋል የሚያስችሉን አስገራሚ ተስፋዎች በእጆቻችን ናቸው፡፡ ልባችንንና ቤታችንን ለመለኮታዊ የህይወት መርኅዎች ክፍት ብናደርግ የሕይወት ሰጪው ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እንሆናለን፡፡ ጠፍ፣ ድርቅና ፍሬ አልባው ውጫዊ ማንነት ላይ ሕይወት ሰጭና ውብ የፈውስ ምንጭ ከቤታችን ይፈልቃል፡፡-The Ministry of Healing, p. 355. ChSAmh 288.2