የክርስቲያን አገልግሎት

187/246

ምዕራፍ 21—መኖሪያ ቤት የወንጌላዊ የማልጠኛ ማዕከል

ከሁሉም ቅድሚያ የሚሰጠው አሰፈላጊ ነገር

ቤት የህጻኑ የመጀመሪያ ትምህርት ቤት እንደመሆኑ የአገልግሎት ሕይወት መሰረት መጠንሰስ የሚኖርበት በዚህ ስፍራ ነው፡፡The Ministry of Healing, p. 400. በቤት ውስጥ የወንጌላዊ አገልግሎት መስጠት አንድ ሰው በቅድሚያ በህይወቱ ሊሠራው የሚገባ ታላቅ ሥራ ነው::- Testimonies, vol. 4, p. 138. ChSAmh 284.1

ሰብዓዊውን ፍጡር ወደ ቀድሞው ንጽህና የመመለስና የማነቃቃት ሥራ በቤት ይጀምራል፡፡ የወላጆች ተግባር በልጆቻቸው ውስጥ በየሰከንዱ መነሳሳት ይፈጥራል... የማህበረሰብ ደኅንነት፣ የቤተ ክርስቲያን ስኬት እንዲሁም የአንድ አገር ብልጽግና በቤት ውስጥ ተጽእኖ ይመሰረታል፡፡ The Ministry of Healing, p. 349. ChSAmh 284.2

የእውነተኛ አገልግሎት መንፈስ በቤት ውስጥ አብልጦ ሲሰፍን— በህጻናት ሕይወት ውስጥ በሙላት መጎልበት ይጀምራል፡፡ ህጻናት በሚሰጡት አገልግሎት ደስታን ማግኘትና ለሌሎች በጎነት መሥዋዕትነት መክፈልን ይማራሉ፡፡The Ministry of Healing p. 401. ChSAmh 284.3

ወላጆች ከፊት ለፊታቸው የተንጣለለውን ታላቁን የቤታቸውን የወንጌል አገልግሎት መስክ አይዘንጉ፡፡ እያንዳንዷ እናት በተሰጧት ልጆች ከእግዚአብሔር የተቀደሰ ኃላፊነት ተቀብላለች፡፡ “ልጆችሽ ለዘላለም በጌታ ቅጥር ሲያበራ የሚኖር፣ በግብረገብ የታነጸ፣ አንጸባራቂ—ቤተ መንግሥታዊ ጸባይ ይዘው ይወጡ ዘንድ እነሆ ይህን ልጅሽንያቺን ልጅሽን ለእኔ አሰልኚ፡፡” በማለት ጌታ ይናገራል፡፡ ታማኟ እናት ልጆቿ የክፉውን ተጽእኖ እንዲቋቋሙ ትምህርት በምትሰጥበት ወቅት ከእግዚአብሔር ዙፋን የሚፈነጥቀው የብርሐን ጸዳልና አምላካዊ ክብር በላይዋ ያበራል፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 37. ChSAmh 285.1

ለክርስቶስ የምንሠራው ሥራ በቤተሰባችን መሃል ይጀምራል፡፡ ከዚv ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ወንጌልን የምናደርስበት መስክ የለም፡፡ ወላጆች ለመርኅ ተገዢና መልካም ምሳሌ በመሆን ላልተለወጡት መሥራት እንደሚገባ ልጆቻቸውን ማስተማር ይኖርባቸዋል፡፡ ልጆች ለአረጋውያንና ጉዳት ለደረሰባቸው የድጋፍ ስሜት እንዲያሳዩ ትምህርት ሲሰጣቸው የድኾችንና የችግረኞችን ሥቃይ የመቀነስ መሻት ያድርባቸዋል፡፡ ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች መሆን ይችሉ ዘንድ ከልጅነታቸው አንስቶ ከራስ ወዳድ ስሜት በራቀ ስለ ሌሎች በጎ ሲሉ መሥዋዕትነት መክፈልንና ለወንጌል ሥራ ትጋት ኖሮአቸው የክርስቶስን ምጽአት ማፋጠንን ሊማሩ ይገባል፡፡ ህጻናት ለሌሎች ከልብ የመነጨ የወንጌል አገልግሎት እንዲሰጡ ከተፈለገ በቅድሚያ ይህን የፍቅር አገልግሎት ለቤተሰባቸው አባላት በማበርከት መማራቸው ተፈጥሮአዊ ይሆናል፡፡Testimonies, vol, 6, p. 429. ChSAmh 285.2

እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በወንጌል አገልግሎት ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆን የሚያነሳሳ ሥርዓትን የተከተለ ጽኑ ጥረት መደረጉ የግድ ነው፡፡ ልጆቻችን ክርስቶስን ወክለው በማንኛውም ጊዜና ቦታ ምርጥ ተግባር ማከናወን ይችሉ ዘንድ ላልዳኑት በሚሰጠው ያላሰለሰ አገልግሎት የእነርሱን ሐዘኔታና የድጋፍ ስሜት ለማግኘት መሞከር ይኖርብናል፡፡ Review and Herald, July 4, 1893. ChSAmh 285.3

የመልአኩ መዝገብ ChSAmh 286.1

ትዳር የያዙ ወንዶች ሚስቶቻቸው ለልጆቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እቤት ትተዋቸው ወደ ሥራ ሲሄዱ ሚስትና እናት የሆነችው እማወራ የምትሠራው ሥራ ባልና አባት የሆነው አባወራ ከሚሠራው በተመሳሳይ ታላቅና አስፈላጊ ነው፡፡ ምንም እንኳ አንዱ በውጪሌላዋ ደግሞ በቤት ውስጥ ሥራ የተጠመዱ ቢሆንም ነገር ግን በቤት ካለችው እናት በተደጋጋሚ የሚጠየቀው ጥንቃቄ፣ ሥጋትና ሸክም ባልና አባት ከሆነው አባወራ የሚልቅ ነው፡፡ በምድር ጠቃሚ፣ ለሰማይ ገጣሚ አድርጋ የልጆቿን አእምሮና ጸባይ በመቅረጽ የምትሠራው ሥራ የተከበረና አስፈላጊ ነው፡፡ ባል በውጪ ሥራው ከሰዎች አክብሮትና ተቀባይነት ሲያገኝ በቤት ውስጥ የምትባዝነው እናት ግን ለልፋቷ ምድራዊ እውቅና ላይቸራት ይችላል፡፡ ሆኖም ስለ ቤተሰቦቿ ምርጥ ጥቅም ስትል የልጆቿን ጸባይ በመለኮታዊው ምሳሌ ለመቅረጽ የምትጥር ከሆነ መዝገብ የያዘው መልአክ የእርሷን ስም ከታላላቆቹ ወንጌላውያን እንደ አንዷ ይመዘግበዋል፡፡ እግዚአብሔር ነገሮችን እንደ ሰብዓዊው ዕይታ ውስን አድርጎ አይመለከትም፡፡ Testimonies, vol. 5, p. 594. ChSAmh 286.2