የክርስቲያን አገልግሎት
ድጋፍ ሰጭ እጆች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረግ
ኃጢአት ከሁሉም የባሰ hፉ ተግባር እንደመሆኑ በኃጢአት ለተሰናከለው ነፍስ ሐዘኔታና እርዳታ ማድረግ የእኛ ተግባር ነው፡፡ ሆኖም ተመሳሳይ አካሄድ በመጠቀም ወደ ሁሉም መድረስ አንችልም፡፡ ነፍሳቸውን እየተሰማው ያለውን ረሃብ የሚደብቁ ብዙዎች አሉ፡፡ እንደነዚv ዓይነቶቹ በሩኅሩኅ ቃላት ወይም በጸሎት በማሰብ በተሻለ ሊረዱ ይችላሉ፡፡ በከፍተኛ እጦት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ነፍሳት ቢኖሩም ነገር ግን የሚገኙበትን ሁናቴ ያስተውሉም፡፡ ነፍሳቸው በእንዴት ያለ የከፋ እጦት ውስጥ እንዳለ አይገነዘቡም፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች በኃጢአት ውስጥ በመስመጣቸው በዘላለማዊው ተጨባጭ እውነት ዙሪያ ስሜት አልባ ሆነዋል፡፡ ክርስቶስን የሚመስሉበትን ኃይል በማጣታቸው የሚድን ነፍስ ይኑራቸው ወይም አይኑራቸው የሚያወቁት አንዳች ነገር የለም፡፡ በእግዚአብሔር ላይ እምነት የላቸውም፤ በሰውም አይተማመኑም፡፡ አብዛኞቹ እንደነዚv ያሉ ነፍሳት ጋር መድረስ የሚቻለው ቅን የሆነውን ሰዎችን የማይፈርጅ አካሄድ በመከተል ብቻ ነው፡፡ የሚመገቡት እንዲያገኙ በማድረግ፣ ንጽህናቸውን መጠበቅ እንዲችሉ በማገዝና የሚለብሱት ንጹህ ልብስ በማዘጋጀት ለአካላዊ ፍላጎታቸው ቅድሚያ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ እንዲህ ያለውን ራስ ወዳድ ያልሆነ ፍቅር በተጨባጭ መመልከት ሲችሉ በhርስቶስ ፍቅር ማመን ዳገት አይሆንባቸውም፡፡ ChSAmh 264.1
የሚሳሳቱ፣ የሚያጠፉስህተታቸው የእፍረትና የከንቱነት ስሜት የሚፈጥርባቸው ብዙዎች አሉ፡፡ የሠሩት ስህተት ወደ ተስፋ መቁረጥ እስኪያመራቸው ድረስ ጥፋታቸውን አጥብቀው ይመለከታሉ፡፡ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ነፍሳት ፈጽሞ ችላ ማለት የለብንም፡፡ አንድ ሰው ከሚወርደው ወንዝ በተቃራኒ ለመዋኘት ሲሞhር የስበት ኃይል ወደ ኋላ ይገፋዋል፡፡ በውሃ ውስጥ እየሰመጠ _ ለነበረው ጴጥሮስ የታላቅ ወንድሙ እጅእንደተዘረጋለት ሁሉ ለዚህም ወንድም የእርዳታ እጅ ይዘርጋለት፡፡ በውስጡ መተማመንና መነቃቃት ሊፈጥሩ የሚችሉ የተስፋ ቃላት ይነገረው:፡— Christ’s Object Lessons, p. 387. ChSAmh 264.2
የጢአት ሕይወት አዝሎት ወዴት ሄዶ ፍቱን መድኃኒት ማግኘት እንደሚችል ለማያውቀው ነፍስ በርኅራኄ የተሞላውን አዳኝ ያቅርቡለት፡፡ እጁን ይዘው፣ ካንገቱ ቀና አድርገው የማበረታቻና የተስፋ ቃላቶችን ይንገሩት፡፡ የአዳኙን እጅ ጨብጦ እንዲይዝ ያግዙት፡፡-The Ministry of Healing, p. 168. ChSAmh 265.1