የክርስቲያን አገልግሎት
እንግዶችን መቀበል—ክርስቲያናዊ ተግባር
በምድራዊው ሕይወታችን ለሌላው በጎ በመሆን እንድንኖር፣ ሌሎችን እንድንባርክና እንግዳ ተቀባዮች እንድንሆን ተጠርተናል፡፡ የእኛን ጥንቃቄ ለሚሹ፣ የማኅበረሰባችንን ጥቅም ለመጋራት ፈቃደኞች ለሆኑና በቤታችን ማረፍ ለሚፈልጉ ምላሽ ለመስጠት የምንደፍረው ውስጣችን ሳይፈቅድ የግዳችንን እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚስተዋል ሐቅ ነው፡፡ እንደውም አንዳንዶች ከነጭራሹ ይህን የወገኖችን ሸክም የመጋራት አስፈላጊ ላፊነት ከላያቸው ገሸሽ ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ሆኖም ለእነዚህ ነፍሳት ያለንን ተደራሽነት ማሳየት የግድ ነው፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ አንዳንድ ወንድሞች እንግዶችን ለመቀበል ብዙም ደስተኞች አለመሆናቸውና እነዚህን ክርስቲያናዊ ኃላፊነቶች በእኩል አለመጋራታቸው ፈቃደኛ ልቦች ባሏቸው ጥቂት ፍልቅልቅና ደስተኞች ልቦች ላይ ብርቱ ሸክም ያርፋል፡፡-Testimonies, vol. 2, p. 645. ChSAmh 265.2
“እንግዶችን መቀበል አትርሱ፤ አንዳንዶች ይህን ሲያደርጉ ሳያወቁ መላእክትን አስተናግደዋልና፡፡” ዘመናት ቢያልፉም ነገር ግን እነዚህ ቃላት ዛሬም ያንኑ ጥንካሬአቸውን እንደ ያዙ ይገኛሉ፡፡ ሰማያዊው አባታችን ልጆቹ በመንገዳቸው ላይ በረከት ሊያገኙባቸው የሚችሏቸውን እድሎች ሸፈንፈን አድርጎ ማኖሩን ቀጥሎአል፡፡ እነዚvን ልዩ እድሎች እየተጠቀሙ የሚያበለጽጓቸው የታላቅ ደስታ ባለቤት ይሆናሉ፡፡Prophets and Kings, p. 132. ChSAmh 265.3