የክርስቲያን አገልግሎት

170/246

ሊታወስ የሚገባ

በአንዳንዶች ሕይወት ውስጥ ሟች ከሆነው ፍጡር ዐይኖች ታትመው የተቀመጡ ምዕራፎች መኖራቸው ሊታወስ ይገባል፡፡ ጉጉ ከሆኑ ዐይኖች በቅድስና የተጠበቁ አሳዛኝ የትውስታ ገጾች አሉ፡፡ ምናልባትም በሕይወት ላይ የደረሱ ችግሮች--ወኔን፣ መተማመንንና እምነትን በየቀኑ የሚሰልቡ በፈታኝ ሁናቴዎች ውስጥ የተደረጉ ከባድ ፍልሚያዎች ረዘም ላለ ጊዜ እንደ ተመዘገቡ ይቀመጣሉ፡፡ ውጣ ውረድ ከበዛው አስከፊ የሕይወት ገጽታ ጋር እየታገሉ ያሉ hአንዳንዶች በቀላሉ ሊገለጽ በሚችል በፍቅር የተሞላ ትኩረት ወይም የማበረታቻ ቃላት ብቻ ሊበረታቱ ይችላሉ፡፡ ከእውነተኛ ወዳጅ የሚጠበቀው እንዲv ያለ ጠንካራና ለመርዳት ዝግጁ የሆነ እጅ ለእነርሱ ያለው ዋጋ ከወርቅና ከብር ይልቅ የከበረ ነው፡፡ በደግነት የተሞሉ ቃላት የመላእክት ፈገግታ ያህል ተቀባይነት አላቸው:፡ ChSAmh 262.4

ለኑሮ የሚያስፈልገውን ወጪ መሸፈን እንደ ሰማይ የራቃቸው በዝግተኛ ክፍያ አድካሚ ሥራ እንዲሠሩ እየተገደዱ ያሉ ከድኽነት ጋር የሚታገሉ አያሌ ሕዝቦች አሉ፡፡ አንዳችም የመሻሻል ጭላንጭል የማይታይበት ከእጅ ወደ አፍ የሆነው አድካሚ ሥራ ሕይወታቸውን የከፋ አድርጎታል፡፡ ህመምና በሽታ በዚህ ሁኔታ ላይ ሲታከል፤ ለመሸከም የማይቸሉት ይሆንባቸዋል፡፡ ድካም የተጫናቸውና የተጨቆኑት እንዴት ፋታ እንደሚያıኙ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ ልባቸው ለተሰበረና ተስፋ ለቆረጡየችግራቸው ተካፋዮች ሁኑ፡፡ እንዲህ ያለው ሁኔታ እርዳታ ልትሰጡ የምትችሉበትን መንገድ ይከፍታል፡፡ ስለ አምላካዊው ተስፋ ንገሯቸው፣ አብራችኋቸውም ሆነ በተለይ ለእነርሱ እየጸለያችሁ ልባቸውን በአምላካዊው ተስፋ ሙሉ፡፡The Ministry of Healing p. 158. ChSAmh 263.1

ሕይወት በሰቆቃ የተሞላ ፍልሚያ የሆነባቸው አያሌ ወገኖች አሉ፡፡ የከበባቸው እጦትና ችግር ደስታ የራቃቸውና የማያምኑ አድርጎአቸዋል፡፡ አመስጋኝ ሊያደርጋቸው የሚችል አንዳችም ምhንያት እንደሌለ ያስባሉ፡፡ ለእነዚህ ወገኖች ደግ ቃላቶችን መሰንዘር፣ የድጋፍ ስሜት ማሳየትና በአድናቆት የታጀቡ አገላለጾችን መጠቀም—ለተጠማው ነፍስ ቀዝቃዛ ውሃ የመስጠት ያህል የላቀ ዋጋ አላቸው፡፡ በርኅራኄ የተሞላ አነጋገርና ደግነት የሰፈነበት ተግባር ከዛለው ትከሻ ላይ ሸhም የማንሳት ያህል ፍቱን ነው፡፡ እያንዳንዱ ራስ ወዳድ ያልሆነ ቃል ወይም ድርጊት ለጠፋው ሰብዓዊ ዘር የhርስቶስን ፍቅር መግለጥ የሚችል መሣሪያ ነው፡፡— Thoughts From the Mount of Blessing, p. 23. ChSAmh 263.2