የክርስቲያን አገልግሎት
ሌሎችን የመደገፍ ሥራ
የhርስቶስ ተከታዮች እርሱ እንደሠራው መሥራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የተራቡትን መመገብ፣ የታረዙትን ማልበስ፣ የሚሠቃዩትንና የታመሙትን ማጽናናት አለብን፡፡ ተስፋ የቆረጡትን በመርዳት ማነቃቃት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ሲሆን “ጽድቅvም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ከብር በኋላv ይጠብቅሃል፡፡”- The Desire of Ages, p. 350. ChSAmh 259.1
hርስቲያናዊ ድጋፍ በመስጠቱ የአገልግሎት መስክ ተካፋይ የሆኑ ወገኖች ጌታ እንዲሠሩ የሚመኘውን ሥራ በመሥራታቸው--ሥራቸው በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው፡፡ እያንዳንዱ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ለዚህ ዘርፍ ከልብ የመነጨ የድጋፍ ስሜት በማሳየት አጽድቆ ሊቀበለው ይገባል፡፡ ሰዎች ሊሠሩት የሚችሉትን በዙሪያቸው ያለውን ይህን ሥራ ችላ ሲሉ፣ እነዚህን ሸክሞች ለመሸከም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ ቤተ hርስቲያን ታላቅ እጦት ላይ ትወድቃለች፡፡ ነገር ግን ቤተ hርስቲያን ይህን ሥራ ወስዳ ቢሆን ኖሮ አባላት አያሌ ነፍሳትን ማዳኛ መንገድ መሆን በቻሉ ነበር፡፡--Testimonies, vol. 6, p. 295. ChSAmh 259.2
ከእግዚአብሔር የሚሰጡ ስጦታዎች በሥቃይ ላለው ማሻያ፣ በእጦት ለሚገኘው መድረሻ በመሆን ሰብዓዊውን ፍጡር ለመባረክ ሊውሉ ይገባል፡፡ የተራበውን እንድንመግብ፣ የታዘረውን እንድናለብስ፣ መበለቲቱንና አባታቸውን በሞት የተነጠቁ ህጻናትን እንድንረዳ፣ ጉዳት የደረሰባቸውንና የተጨቆኑትን እንድናገለግል ተጠርተናል፡፡ በምድር ላይ ተስፋፍቶ የምንመለከተው ሥቃይና መከራ ይኖር ዘንድ አምላካዊው ፈቃድአልነበረም፡፡ አንዱ የተቀማጠለ ኑሮ ሲኖር የሌሎች ልጆች ግን ዳቦ አጥተው ያለቅሳሉ፡፡ ሰዎች ከመሰረታዊ ፍላጎታቸው ባሻገር ለሌሎች በጎ በማድረግ ለሰብዓዊው ፍጡር በረከት እንዲሆኑ ተጠርተዋል፡፡ ጌታ እንዲህ ይላል፡ “ያላችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ” “ቸሮችና ለማካፈል ፈቃደኞች ሁኑ” “ነገር ግን ግብዣ ባዘጋጀህ ጊዜ ድኾችን፣ አካለ ስንኩሎችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውሮችን ጥራ” “የጭቆና ሰንሰለት እንድትበጥሱ”፣ “የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ”፣ “የተጨቆኑትን ነጻ እንድታወጡ”፣ “ቀንበርን ሁሉ _ እንድትሰብሩ”፣ “ምግብህን ለተራበ እንድታካፍለው”፣ “ተንከራታቹን ድኻ ወደ ቤትህ እንድታስገባው”፣ “የተራቆተውን ስታይ እንድታለብሰው”፣ “የተገፉ እንዲጠግቡ ብታደርግ”፣ “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ”—እነዚህ ጌታ የሰጠን ትእዛዛት ናቸው፡፡ በእምነት የዳኑት የታላቁ ክርስትና እምነት አካል የሆኑ ወገኖች ይህን ሥራ እየሠሩ ነውን?— Christ’s Object Lessons, Pp. 370, 371. ChSAmh 259.3
መልካም ቃላት እየተናገርንና በጎ ተግራት እያከናወንንለምስኪኑ፣ ለደኻውና ጉዳት ለደረሰበት ደግነት እያሳየን የመልካም ሥራ ፍሬዎችን እንድናፈራ ክርስቶስ ይጠይቀናል፡፡ ልቦች በሐዘን ላሉና በተስፋ መቁረጥ ሸክም ለደቀቁ ልቦች የድጋፍ ስሜት ሲያሳዩእጆች ለተቸገሩ ሲዘረጉ፣ የተራቆቱ ሲለብሱ፣ መጻተኛው በእንግዳ መቀበያ ሲስተናገድና በልብ ውስጥ መኖሪያ ሲያገኝመላእክት እጅግ በቅርበት ይመላለሳሉ፣ ሰማይም ፈጣን ምላሽ ይሰጣል፡፡ እያንዳንዱ ፍትሐዊ፣ በምኅረት የተሞላና የደግነት ተግባር ጣፋጭ ቃና ያለው ዜማ በሰማይ እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ አብ በሰማይ ዙፋኑ ተቀምጦ ምኅረት የሚያደርጉትን ነፍሳት ይመለከታል፣ ከከበሩ ንብረቶቹ አንዱ አድርጎም ይቆጥራቸዋል፡፡ ” እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የገዛ ገንዘቤ ይሆናሉº ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት፡፡” በእጦትና በሥቃይ ለሚገኘው ወገን የምናደርገው እያንዳንዱ በምኅረት የተሞላ ድርጊት ለየሱስ እንደተደረı ይቆጠራል፡፡ ለድኻው እርዳታ ስናደርግ፣ ለተጎዱና ለተጨቆኑ የድጋፍ ስሜት ስናሳይና ወላጅ ለሌላቸው ተገን ስንሆን ከየሱስ ጋር የቀረበ ወዳጅነት እንመሰርታለን፡፡-- Testimonies, vol. 2, p. 25. ChSAmh 260.1
በችግር ላለው፣ ለተጨቆነው፣ ለሚሠቃየውና ለምስኪኑ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት የምትቀበል ቤተ hርስቲያን ልትሠራው የምትናፍቀው ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡ ሰብዓዊው ፍጡር በጥልቅ ከወደቀበት ሥቃይና መከራ መድረስ የሚችለውን ጸጋና ብርታት በየቀኑ ከእግዚአብሔር እየተቀበልን--ራሳቸውን በትክክል መርዳት የማይችሉትን እየረዳን፣ የተራቡትን እየመገብንና የተጣሉትን ድኾች ወደ ቤታችን እያመጣን እንደ ደጉ ሳምራዊ ያለ ልባዊ ርኅራኄ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ይህን ሥራ በመሥራት የተሰቀለውን ክርስቶስ ለሰዎች ማቅረብ የምንችልበት ምቹ ዕድል ተሰጥቶናል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 276. ብዙዎች እምነታቸው ደካማና ወላዋይየክርስትና ተሞክሮአቸው ጨለማና በጥርጣሬ የተሞላ፣ ጸሎታቸው አቅመ ቢስና ብርታት የሌለው የሆነበት ምክንያት ምን እንደሆነ ሲገረሙ ይታያሉ፡፡ ስለ ምን ብለን ጾምን? አንተ ከጉዳይ ካልቆጠርኸው ስለ ምን ራሳችንን አዋረድን? ይላሉ፡፡” እንደነዚህ ዓይነቶቹ ሁናቴዎች እንዴት መለወጥ እንደሚችሉ ክርስቶስ በኢሳ. 58፡6-7 አሳይቶአል፡፡ ይህ እንግዲህ ክርስቶስ ልባቸው ለሚዝል፣ ለሚጠራጠሩና በፍርሐት ለሚርዱ ወገኖች የሰጠው ቀመር ነው፡፡ ሐዘን የተሰማቸው፣ ልባቸው ተሰብሮ በጌታ ፊት የሚመላለሱ ወገኖች ከሚገኙበት ሁናቴ ወጥተው የእነርሱን እርዳታ ለሚሻው ነፍስ ያላቸውን ተደራሽነት ያሳዩ፡፡Testimonies, vol 6, p. 266. ChSAmh 261.1
የወደቁትን ማንሳትና ተስፋ የቆረጡትን ማጽናናት አስደናቂው ሰማያዊ ውበት ነው፡፡ ክርስቶስ በሰብዓዊው ልብ ውስጥ ሲኖር በተመሳሳይ መንገድ ይገለጣል፡፡ እነዚህ ድርጊቶች በተተገበሩ ቁጥር የክርስቶስ ኃይማኖት በረከት ያስገኛል፡፡ ይህ እንዲሠራ በሚደረግበት ስፍራ ሁሉ ደማቅ ብርሃን አለ፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 386. ChSAmh 262.1
የሰራፕታዪቱ መበለት የነበራትን ትንሽ ምግብ ለኤልያስ በማካፈሏ በምላሹ የእርሷና የልጇ ሕይወት መትረፍ ቻለ፡፡ ፈተናና ስደት በሚመጣበት ወቅት በእጅጉ እርዳታና ድጋፍ ለሚያሻቸው ነፍሳት ለሚደርሱላቸው ሁሉ እግዚአብሔር ታላቅ በረከት እንደሚያፈስ ቃል ገብቶአል፡፡ እርሱ _ ዛሬም _ አልተለወጠም፡፡ በኤልያስ ዘመን የነበረው አምላካዊ ኃይሉ እነሆ ዛሬም ያው ነው፡፡— Prophets and Kings, pp. 131, 132. ChSAmh 262.2
ከራስ ወዳድነት በራቀ አገልግሎት መገለጽ የቻለው የክርስቶስ ፍቅር በክፉ አድራጊው ላይ ከሠይፍ ወይም ከፍርድ ቤት የላቀ ውጤታማ ተሐድሶ ያመጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች በሕግ ተላላፊው ላይ ፍርሐት እንዲሰርጽ የሚያደርጉ እንደመሆናቸው በፍቅር የተሞላው ወንጌላዊ ግን ከዚህ የላቀ ማድረግ ይችላል፡፡ በተደጋጋሚ በግሳጼ የደነደነው ልብ— በክርስቶስ ፍቅር ይቀልጣል፡፡— The Ministry of Healing, p. 106. ChSAmh 262.3