የክርስቲያን አገልግሎት
ምዕራፍ 17—ለሌሎች እርዳታ የማድረግ ክርስቲያናዊ ተግባር
መለኮታዊውን ዱካ መከተል
ብዙ ሰዎች ከርስቶስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ጊዜውን ያሳለፈባቸውን ቦታዎች መጎብኘት ማለትም እርሱ በተራመደበት መንገድ ላይ መራመድ፣ ትምህርት ያካሄደባቸውን ሐይቆች ማየትና ዐይኑ ያርፍባቸው የነበሩትን ኮረብታዎችና ሸለቆዎች መመልከት እንደ ልዩ ዕድል ይቆጥሩታል፡፡ ክርስቶስ በሄደበት ለመሄድ ወደ ናዝሬት፣ ቅፍርናሆም ወይም ቢታንያ መሄድ አያስፈልገንም፡፡ የእርሱን ዱካ ህሙማን በተኙበት አልጋ አጠገብ፣ ድኽነት በሰፈነባቸው ጉስቋላ ጎጆዎች ውስጥና መጽናናት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ እናገኘዋለን፡፡ የሱስ በዚህ ዓለም ይመላለስ በነበረ ጊዜ ያደረገውን ካደረግን የእርሱን ዱካ ተከተልን ማለት ነው፡፡The Desire of Ages p. 640. ChSAmh 258.1
የሱስ ለተመለከተው ሥቃይ ሁሉ መፍትሔ ለማግኘት ጣረ፡፡ ሊሰጣቸው የሚችል የገንዘብ መጠን ባይኖረውም ነገር ግን ከእርሱ የባሱትን ለመርዳት ሲል ብዙውን ጊዜ የምግብ ሠዓቱን መሥዋዕት ያደርግ ነበር፡፡ ወንድሞቹ የእርሱ ዝና ከእነርሱ ጋር በጣም የሚቃረን ሆኑ ተሰማቸው፡፡ ከእነርሱ አንዳቸውም የሌላቸው ወይም ይኖረናል ብለው አስበው የማያውቁት ዘዴ፣ ብልሃትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ነበር፡፡ ድኾችንና ጎስቋሎችን በጭካኔ አነጋገር ሲያመናጭቋቸው፤ የሱስ ግን እንደዚህ ያሉትን ሌሎች እርዳታ የማድረግ ከርስቲያናዊ ተግባር ፈልጎ ያጽናናቸው ነበር፡፡ ለችግረኞች የሚጠጣ ውሃና የራሱንም ምግብ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ከሥቃያቸው ይገላግላቸው ነበር፡፡ ያስተማራቸውን እውነት ከበጎ አድራጎቱ ጋር በማዛመድ በሕሊናቸው እንደማይረሳ ሆኖ ተመዘገበ፡፡— The Desire of Ages, pp. 86, 87. ChSAmh 258.2