የክርስቲያን አገልግሎት
ውጤታማ ሥራ የሚጠበቅባቸው ማተሚያ ቤቶቻችን
ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ከዓለም የተለዩልዩ ጠባይ ያላቸው በእግዚአብሔር የተመረጡ ሕዝቦች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እጅግ የሰላውን እውነት ተጠቅሞ ከዓለም ፈልቅቆ በማውጣት ከራሱ ጋር ትስስር እንዲፈጥሩ አድርጎአቸዋል፡፡ እነዚህ ተወካዮቹ ያደረጋቸውን ሕዝቦቹን የመጨረሻው የደኅንነት ሥራ አምባሳደሮች አድርጎ ጠርቶአቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም ሟች ለሆነው ሰብዓዊ ፍጡር ፈጽሞ ያልተሰጠ ግዙፍ የእውነት ሐብት ባለቤት የሚያደርጋቸው እጅግ የተከበረና የሚያስፈራ ማስጠንቀቂያ ለዓለም ያበረክቱ ዘንድ በእግዚአብሔር ተሰጥቶአቸዋል፡፡ ይህን ሥራ በማሳካቱ ረገድ ማተሚያ ቤቶቻችን እጅግ ውጤታማ መሣሪያዎቻችን SFO::-- Testimonies, vol. 7, p. 138. ChSAmh 203.1
የሕትመት ሥራችን በአምላካዊው አመራር የተቋቋመና በእርሱ የቅርብ ቁጥጥር የሚመራ ነው፡፡— Testimonies, vol. 7, p. 138. ChSAmh 203.2
ከክብሩ ነጸብራቅ የተነሳ ምድር የበራችው--በታላቅ ሥልጣን ከሰማይ የወረደው ሌላ መልአክ መልእክት ዙሪያ ማተሚያ ቤቶቻችን ከፍ ያለ ሥራ መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 140. ChSAmh 203.3
ለማተሚያ ቤቶቻችን እንዲv ለማለት እወዳለሁ፡ “አምላካዊውን ሕግ ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ፡፡ የሦስቱን መላእክት መልእክት ለመላው ዓለም አውጁ፡፡ “የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ለየሱስም ታማኝ (ራእ. 14፡2) አገልጋይ መሆናችሁ ይታይ፡፡ የሕትመት ውጤቶቻችን ለዓለም ምስክር የሚያደርጋቸውን መልእክት ያበርክቱ”፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 61. ChSAmh 203.4
ለዚህ ወቅት የተሰጠውን እውነት የሚያምኑ እርስዎ ከእንቅልፍዎ ይንቁ!! እውነትን የሚያስተውሉእውነትን ያውጁ ዘንድ አቅም በፈቀደ መጠን አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ አሁን ከእርስዎ የሚጠበቅ ሥራ ነው፡፡ የሕትመት ውጤቶቻችንን በመሸጥ ከሚገኘው ገቢ ከፊሉ የታወሩትን ዐይኖች በመክፈት ጪንጫውን ልብ የሚያለሰልሰውን የጽሑፍ ዘርፍ አቅም ለማጎልበት ይዋል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 62. ChSAmh 204.1
የወቅታዊውን እውነት ብርሐን የያዙ የሕትመት ውጤቶች የሚዘጋጁባቸው ማተሚያ ቤቶች በአሜሪካ፣ በአውሮፓና በሌሎች የዓለም ክፍሎች እንዲገነቡ ጌታ ከዓመታት በፊት የተለየ መመሪያዎች ሰጥቶኝ ነበር፡፡ የማደሚያና የማስጠንቀቂያ መልእhቶች የያዙ የሕትመት ውጤቶች በዓለም የሚሰራጩበት ማንኛውም ጥረት እንዲደረግ መመሪያ ሰጥቶአል፡፡ በሌላ መንገድ ሊደረስ የማይቻልባቸው ጥቂቶች ዘንድ የሕትመት ውጤቶቻችንን ተጠቅመን መድረስ እንችላለን፡፡ ከመጻሕፍቶቻችንና ከሕትመት ውጤቶቻችን የሚያንጸባርቀው ወቅታዊ እውነት ቃሉን ለዓለም በመንገር የሚያበራ ይሁን፡፡Testimonies, vol, 8, p. 87. ChSAmh 204.2
የሕትመት ውጤቶቻችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ወደ እያንዳንዱ አገርና ዜጋ መሰራጨት እንዳለባቸው ተመልክቼአለሁ፡፡ ለመሆኑ ገንዘብ ከነፍሳት ዋጋ ጋር ሲነጻጸር የመግዛት ኃይሉ ምን ያህል ነው? እያንዳንዱ በኪሳችን የሚኝ ብር የእኛ ሳይሆን እግዚአብሔር በአደራ ያስቀመጠው-የጌታ መሆኑ ሊስተዋል ይገባል፡፡ ብራችን የአላስፈላጊ ፍላጎቶች ማርኪያ ሳይሆን ወንዶችንና ሴቶችን ከውድመት በመታደግ በጥንቃቄ ለአምላካዊው ሥራ የምናውለው ነው::--life Sketches, p. 214. የሕትመት ውጤት የሆነው እውነት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ እስከ ምድር ዳርቻ ሊሰራጭ ይገባል፡፡- Testimonies, vol. 9, p. 26. ChSAmh 204.3
እነዚህ ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎም የሚኖርባቸው የኅትመት ውጤቶችም ሆኑ ወንጌል ለመላው ዓለም ሊሰበክና ሊሰራጭ ይገባል፡፡ በዚህ ሥራ የሚሰማራ እያንዳንዱ ሰው የስኬት ባለቤት የሚያደርገው መለኮታዊ ችሎታና ብቃት እንደሚሰጠው ክርስቶስ ቃል ገብቶአል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 34. ChSAmh 205.1
የኅትመት ውጤቶቻችን በየትኛውም ስፍራ መድረስ ይኖርባቸዋል፡፡ የሦስቱ መላእክት መልእክት በዚህ አማካይና ሕያው በሆነ መምህር መሰጠት ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት የምታምኑ ሁሉ ::-- The Colporteur Evangelist, p. 101. ChSAmh 205.2
አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ሕዝቦች የኅትመት ውጤቶቻችንን ይዘው የሦስቱ መላእክት መልእክት ወዳልተሰማባቸው ስፍራዎች ይሂዱ፡፡ መጻሕፍቶቻችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተተርጉመው ይታተሙ፡፡ ትሑትና ታማኝ የወንጌል ሠራተኞች መጻሕፍት የመሸጥ አገልግሎት ውስጥ በመግባት እነዚህን መጻሕፍት ባያገኝ ኖሮ እውነትን ለማስተዋል ይቸገር ወደ ነበረው ነፍስ ያምሩ፡፡ --Testimonies, vol. 9, pp. 33, 34. ChSAmh 205.3
የአዳኙን በቅርብ መገለጥ ተስፋ የሚያበስሩ የኅትመት ውጤቶች ይዘው ከከተማ ወደ ከተማ፣ ከአገር ወደ አገር ይጓዙ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 34. ChSAmh 205.4
የኅትመት ውጤቶቻችን በሌሎች አገሮች የሚገኙ አንባቢያንን ጠባብ አስተሳሰብና የተሳሳተ እምነት ግድግዳ አፈራርሰው ለመውጣት እንደረዳቸው ተመልክቻለሁ፡፡ ወንዶችና ሴቶች ወቅታዊ እውነት የያዙትን በራሪ ጽሑፎች በጋለ ፍላጎት ሲያጠኑ ጌታ አሳይቶኛል፡፡ በተለይ ጥላ አጥልቶበት የነበረው አራተኛው ትእዛዝ—የሰንበት እረፍት ርዕሰ ጉዳይ ወለል ሲልላቸው አዳዲስ የሆኑባቸውን ድንቅ ማስረጃዎች በማንበብ መጽሐፍ ቅዱሶቻቸውን ጥልቅና ከዚያ በፊት ባልታየ አዲስ መነሳሳት ይከፍቱ ነበር፡፡ በኅትመት ውጤቶቹ ላይ ያነበቧቸው እውነቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተስማሙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ አምላካዊውን ቃል ሲፈትሹ የመላእክት በዙሪያቸው መገኘት ባገኙት ግንዛቤ ላይ አዲስ ብርሃን እንዲፈነጥቅላቸው ያደርግ ነበር፡፡ በሚያነቧቸው የኅትመት ውጤቶች ላይ ያገኙ የነበረው እውነት አእምሮአቸው በተለየ አድናቆት እንዲሞላ መንስኤ ሆኖ ነበር፡፡ ChSAmh 205.5
በአንድ እጃቸው ወረቀቶችና በራሪ ጽሑፎች በሌላኛው—መጽሐፍ ቅዱስ ይዘውና ጉንጮቻቸው በእንባ ርሰውእግዚአብሔር ወደ ተሟላ እውነት ይመራቸው ዘንድ በፊቱ አጎንብሰው ቅንና ትሑት ጸሎት ሲያቀርቡ ተመልክቻለሁ፡፡ እውነት በልባቸው ተቀባይነት አግኝቶ እንደ ሰንሰለት ኅብር የፈጠረውን ሐቅ ሲመለከቱ መጽሐፍ ቅዱስን ከቀድሞው አዲስ ሆኖ አገኙት፡፡ ገጽታቸው በፍስሐና በቅድስና ሲያበራ ይስተዋሉ የነበሩ እነዚህ ወገኖች ያገኙትን እውነት በከፍተኛ ደስታ ከልባቸው ጋር አቆራኝተውት ነበር፡፡ ChSAmh 206.1
ያገኙትን ብርሃን ለብቻቸው በማጣጣም ብቻ እርካታ ማግኘት ያልቻሉ ለሌሎች ሥራት ጀምረዋል፡፡ አንዳንዶች ስለ እውነት ሲሉ-እንዲሁም በጨለማ ያሉትን ወንድሞች ለመርዳት ባላቸው ቅንአት ታላቅ መሥዋዕትነት ከፍለዋል፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተረጎሙ በራሪ ጽሑፎችን ለማሰራጨት የሚያስችል በቂ ዝግጅት ማድረግ ወሳኝ ነው፡፡Life Sketches, pp. 214, 215. ChSAmh 206.2