የክርስቲያን አገልግሎት
ነጻ ስርጭት ለማድረግ የሚያስችሉ ዕድሎች
የኅትመት ውጤቶች በባቡር ጉዞ፣ በንገድ ላይ፣ በመርከብና በፖስታ አማካይነት በጥንቃቄ ወደ አንባቢው እንዲሰራጩ ይደረግ፡፡Gospel Workers, p. 353. ChSAmh 206.3
ዛሬ በእስራኤል ዘመን ከነበረው እጅግ በላቀ ሁኔታ በሁሉም የኑሮ ጀረጃ ላይ የሚገኙ የተለያዩ አገራት ዜጎችወንዶችና ሴቶች ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉ፡፡ አውራ ጎዳናዎች ከአንድ ሺ እጥፍ በላይ ጨምረዋል፡፡ እግዚአብሔር ወደ ነፍሳት የምንደርስባቸውን መንገዶች በአስደናቂ መልኩ አዘጋጅቶአል፡፡ ማተሚያ ቤቶቻችን የሚፈለገውን ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ናቸው፡፡ እውነትን በየስፍራው ለማድረስ የሚያስችሉን በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘጋጁ መጽሐፍ ቅዱሶች፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች የማዘጋጀት ኃላፊነት በእጃችን እንደመሆኑ እስከ ዓለም ዳርቻ በፍጥነት ልናሰራጫቸው ይገባል፡፡-Gospel Workers, p. 352. ChSAmh 206.4
በራሪ ጽሑፎቻችን፣ መጽሔቶቻችንና መጽሐፎቻችን በየአቅጣጫው ይሰራጩ፡፡ መልካም አጋጣሚ ባገኛችሁ ቁጥር ለሰዎች ልታድሏቸው የምትችሏቸው በራሪ ጽሑፎች በሄዳችሁበት ሁሉ ከእናንተ አይለዩ፡፡ መሸጥ የምትችሏቸውን መጽሐፍት እየሸጣችሁ እንደ ሁኔታው በውሰት መስጠት ካለባችሁ ያን ከማድረግ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡ በዚvም አመርቂ ውጤት ታገኛላችሁ፡፡--Review and Herald, June 10, 1880, ChSAmh 207.1
በነፃ የሚታደሉ አነስተኛ ጽሑፍ የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በማሰራጨቱ ረገድ ኃላፊነታችንን በሚገባ እየተወጣን አለመሆኑን ጌታ አሳይቶኛል፡፡ ይህን ዘዴ ብቻ ተጠቅመን ከሠራን እውነትን አጥብቀው መያዝ የሚችሉ አያሌ ታማኝ ነፍሳትን አሉ. . እነዚህ አነስተኛ ገጾች ያሏቸው በራሪ ጽሑፎች ተልዕኮው ልባቸውን ከሚነካ ሰዎች በሚሰባሰብ ገንዘብ በቀላሉ መዘጋጀት ይችላሉ፡፡ ለወዳጅዎ ደብዳቤ ሲልኩ ከእነዚህ በራሪ ጽሑፎች አንድ ወይም ሁለቱን በፖስታ ውስጥ ቢከቱ ለቴምብር የሚከፍሉት ተጨማሪ ገንዘብ አይኖርም፡፡ በትራንስፖርት ውስጥ፣ በመርከብ ወይም በግብዣ ቦታ ከሰዎች ጋር ሲገናኙ የሚሰማ ጆሮ ላለው ሁሉ እነዚህን ጽሑፎች ማደል ይችላሉ፡፡ Testimonies, vol. 1, pp. 551, 552. ChSAmh 207.2