የክርስቲያን አገልግሎት

133/246

ምዕራፍ 13—የኅትመት ውጤቶች አገልግሎት

ቅድሚያ የሚሰጠው ሥራ

የኅትመት ውጤቶቻችንን ለሕዝብ ለማድረስ አንባቢው መጽሐፍ ቅዱስን እንዲመረምር መምራት ከሁሉ የላቀ አስፈላጊ ሥራ ነው፡: የወንጌላዊ ተልዕኮ የሆነው መንፈሳዊ ጽሑፎቻችንን ለቤተሰቦች ማስተዋወቅ፣ ስለ መልእክቶቹ መነጋገርና መጸለይ መልካም ሥራ ነው፡፡The Colporteur Evangelist, p. 80. ChSAmh 199.1

“የሦስቱን መላእክት መልእክት ለማወጅ ምን ማድረግ እችላለሁ?” በማለት እያንዳንዱ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ራሱን ይጠይቅ፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር የመጣው ይህን መልእክት ለአገልጋዩ ብሎም ለቤተ ክርስቲያን ለመስጠት ነው፡፡ መልእክቱ ለእያንዳንዱ አገር፣ ቤተሰብ፣ ቋንቋና ሕዝብ ሊታወጅ ይገባል፡፡ ለመሆኑ መልእክቱን የምናቀርበው እንዴት ነው? በራሪ ጽሑፎችን ማደል አንዱ መልእክቱ የሚደርስበት መንገድ ነው፡፡ እያንዳንዱ አማኝ ለዚህ ዘመን ተገቢ የሆኑ መልእክቶች የያዙ በራሪ ጽሑፎችን፣ መጽሔቶችንና መጻሕፍትን ያድል፡፡ መጻሕፍቶቻችንን በየትኛውም ስፍራ የሚያደርሱ መጽሐፍ በመሸጥ የሚተዳደሩ አገልጋዮች ያስፈልጉናል፡፡Southern Watchman, Jan. 5, 1904. ChSAmh 199.2

ጽሑፎቻችንና መጻሕፍቶቻችን ጌታ ለዚህ ዘመን የሰጠውን መልእክት ያለማcለስ ወደ ሕዝቡ የሚያደርስባቸው መንገዶች ናቸው፡፡ እውነትን ለነፍሳት በማስተማሩና በማረጋገጡ ረገድ የሕትመት ሥራዎች በቃል ብቻክንውን ማግኘት ከሚችለው አገልግሎት እጅግ የላቀ ውጤት ያስገኛሉ፡፡ የቤት ለቤት አገልግሎት በሚሰጠው ሠራተኛ አማካኝነት በየሰዉ ቤት መጽሐፍ መደርደሪያ ላይ የሚገኙት ድምጽ ዐልባዎቹ መልእክተኞች ሁለ ገብ የወንጌል አገልግሎት የማጠናከር ሥራ ይሠራሉ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ መንፈስ ቅዱስ የሰዎችን አእምሮ እንደሚነካ ሁሉ በተመሳሳይ መጻሕፍቱን የሚያነቡ አእምሮዎችን ይዳስሳል፡፡ እንዲሁም መላእክት የአገልጋዩን አገልግሎት እንደሚደግፉ ሁሉ እውነትን የያዙትን መጻሕፍት ከሚያነቡ ጎን ይሆናሉ፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 35, 316. ChSAmh 200.1

ከቦታ ቦታ በመዘዋወር የሚሰጥ አገልግሎት እንዲጠወልግ ሊተው አይገባም፡፡ በወቅታዊው እውነት ላይ የብርሃን ጮራ የፈነጠቁ መጻሕፍት በተቻለ ከፊት ሊደረጉ ይገባል፡፡ የኮንፈረንስ ፕሬዚደንቶችም ሆኑ ሌሎች የሥራ መሪዎች በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ብርቱ ኃላፊነት አለባቸው፡፡-Southern Watchman, April 25, 1905. ChSAmh 200.2

ዓለምን በመጻሕፍቶቻችንና በመጽሔቶቻችን አማካይነት መስበክና ለዚህች ምድር የእውነትን ብርሃን የመፈንጠቅ ኃላፊነት አለብን፡፡ የሁሉም ነገር መጨረሻ እየተቃረበ መሆኑን የሕትመት ውጤቶቻችን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡The Colporteur Evangelist, p. 100. ሕዝቦቹ ስንፍናን፣ ቀርፋፋነትንና ምላሽ አለመስጠትን አስወግደው ሕያው እንቅስቃሴ ያደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪውን ያቀርባል፡፡ የሕትመት ውጤቶቻችንን ወደ ሕዝቡ ወስደን እንዲቀበሉ ማነሳሳት ይኖርብናል፡፡- Southern Watchman, April 25, 1905. ChSAmh 200.3

አሁን የሕትመት ውጤቶቻችን የወንጌልን ዘር እየዘሩና እንደ iብከት-አያሌ ነፍሳት ወደ ክርስቶስ ማምጫ መሣሪያ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ መላው ቤተ ክርስቲያናት እነዚህን ጽሑፎች የማሰራጨት ሥራ መሥራታቸውን ተከትሎ ማንሰራራት ችለዋል፡፡ እያንዳንዱ የክርስቶስ ደቀ መዝሙር በዚህ ሥራ የራሱን ድርሻ ማበርከት ይችላል፡፡-Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 200.4

የሰማይ መልእክተኛ በመካከላችን ቆሞ በሚያስጠነቅቁ ቃላቶችና መመሪያዎች ተናግሮናል፡፡ የመንግሥት ወንጌል እየጠፋ ለሚገኘው ዓለም የተሰጠ መልእክት መሆኑን በግልጽ እንድናስተውል በማድረግ--በሕትመት ውጤቶቻችን ውስጥ የሚገኙትም ሆኑ ገና ያልታተሙት እነዚህ መልእክቶች በቅርብም ሆነ በሩቅ ወዳሉ መድረስ ይኖርባቸዋል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 67. ChSAmh 201.1

በሕትመት ውጤቶቻችን ላይ የምንሠራው ሥራ የተቀደሰውን ወቅታዊ ብርሃን በፍጥነት ለዓለም የምናዳርስበት መንገድ ሊሆን ይገባል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 69. ChSAmh 201.2

ሰይጣን የወጣቶችን ሞራል የሚያረክሱ መርዝነት ያላቸውን የሥነ ጽሑፍ ውጤቶች በማስፋፋት ሥራ ተጠምዶአል፡፡ ዓለማዊ የሕትመት ውጤቶች በመላው ምድር ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡ እያንዳንዱ የቤተ hርስቲያን አባል የሰዎችን አእምሮ ማጎልበት የሚችል የሕትመት ውጤት በማሰራጨት እውነት በቀጥታ ወደ እነርሱ የሚደርስበት ጥልቅ ፍላጎት የማያድርበት ለምን ይሆን? እነዚህ ለዓለም ብርሃን መሆን የሚችሉ መጽሔቶችና በራሪ ጽሑፎች ነፍሳትን የመለወጥ አቅም ያላቸው መሣሪያዎች መሆናቸው በተደጋጋሚ ተስተውሎአል፡፡Review and Herald, June 10, 1880. ChSAmh 201.3

ሥራው በሚገባ የተዘጋጀውን የሕትመት ውጤት በማሰራጨት ክንውን ሊያገኝ ሲገባው እኛ ግን አንቀላፍተናል፡፡ አሁን መጽሔቶችንና መጻሕፍትን በጥበብ እየተጠቀምን ክርስቶስ በፍጥሞስ ለነበረው ዮሐንስ የሰጠውን መልእክት ዓለም እንዲያስተውል ቁርጠኝነት በታከለበት ኃይል ቃሉን እንስበክ፡፡--The Colporteur Evangelist, p. 101. ChSAmh 201.4

የቤተ ክርስቲያን አባላት የሕትመት ውጤቶቻችንን ለሌሎች የማዳረሱን ሥራ ጠቃሚነት በማስተዋልና ለአገልግሎቱ በቂ ጊዜ በመመደብ ከእንቅልፋቸው ነቅተው ወደ ሥራ ይግቡ፡፡ በአያሌ አካሄዶችበራሳቸው ሊሰብኩ የሚችሉ መጽሔቶችን፣ በራሪ ጽሑፎችንና መጻሕፍትን በሰዎች ቤት ያኑሩ፡፡ አንዳችም ሊባhን የሚችል ጊዜ የለም፡፡ አባላት ምንም ሳይሰስቱ ቤት ለቤትም ሆነ ለጎዳና አገልግሎት ራሳቸውን በፈቃደኝነት በመስጠት ምላሽ ለሚሻው _ ብርቱው ማስጠንቀቂያ የበኩላቸውን ያበርክቱ፡፡ ቤተ hርስቲያን የተመደበችበትን ሥራ ስትሠራ “እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሐይ ያበራች፣ ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ” በመሆን ወደ ፊት ትገሰግሳለች፡፡ Southern Watchman, Nov. 20, 1902. ChSAmh 202.1

የእውነት ብርሃን--በወንጌል ተልዕኮ ጥረት አማካይነት አንጸባራቂ ጨረሮችን እየለቀቀ ይገኛል፡፡ የሕትመት ውጤት በአገልግሎት መድረስ ወደ ማይቻልባቸው አያሌ ስፍራዎች መድረስ የሚችል ብርቱ መሣሪያ ነው፡፡--Testimonies, vol. 5, p. 388. ChSAmh 202.2

ጨለማው የፈተና ወቅት ሊደርስ ተቃርቦአል፡፡ የቀረው ጊዜ አጭር መሆኑን ጠንቅቆ ሚያውቀው ሰይጣን ረቂቅ የማታለያ ኃይሉን በአንድ እያሰባሰበ ይገኛል፡፡ በዐለቶች መሃል ተሸሽገው የሚገኙ እውነትን የሚያውቁ ወገኖች በሙሉ እግዚአብሔር ዓለምን ሲቀጣ አምላካዊውን ክብር እንዲመለከቱ ጥሪ ይቀርብላቸዋል፡፡ አሁን እውነት ሳይነገር ታፍኖ መቀመጥ የለበትም፡፡ _ ግልጽ _ መግለጫዎች ሊወጡ የግድ ነው:፡ በነፋሻማው የአየር ጸባይ ወቅት ንፋስ ምድሪቱን በቅጠሎች ርጋፊ እንደሚሸፍን ወቅታዊውን እውነት የያዙ በራሪ ጽሑፎች በየቦታው መበተናቸውና እውነት ያለ አንዳች ማባበል እንደ ወረደ መነገሩ የግድ ይሆናል፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 231. ChSAmh 202.3

ድምጽ ዐልባዎቹን የእውነት መልእክተኞች ወደ ሕዝቡ የሚያደርሱ የነፍሳት ሸክም የሚሰማቸውና ብርሃን ለሚሹ ወቅታዊ ቃላት መሰንዘር የሚችሉ መንገድ ጠራጊ ሠራተኞች ያስፈልጋሉ፡፡ ምናልባት አንዳንዶች “እኔ የወንጌል ሠራተኛ ባለመሆኔ በሕዝብ ፊት መስበክ አልችልም ይሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እርስዎ ሰባኪ ባይሆኑም የተገናኙአቸውን በሚያስፈልጋቸው የሚያገለግሉ ወንጌላዊ መሆን ይችላሉ፡፡ የሚያገኟቸው ሰዎች የሱስን ይወዱ እንደሆነ በመጠየቅ—ደቀ መዛሙርት እንደ ሠሩ የሚሠራ አምላካዊ የእርዳታ እጅ መሆን ይችላሉ፡፡Southern Watchman, Nov. 20, 1902. ChSAmh 202.4