የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

124/349

የሰይጣን ጥላዎች

[Appeared In Notebook Leaflets, The Church, No. 3.]

ለእምነታችን እንቅፋት ለመሆንና ከጽድቅ ፀሐይ የሚመጣውን ብርሃን ለመጋረድ የሰይጣን ጥላ በመንገዳችን ላይ የማያርፍበት ጊዜ በፍጹም እንደማይመጣ ልብ እንበል፡፡ እምነታችን መንገዳገድ የለበትም፣ ነገር ግን በጥላው ውስጥ ጸንቶ ማለፍ አለበት፡፡ በጥርጣሬ ጨለማ ውስጥ መቀበር የሌለበት ልምምድ አለን፡፡ እምነታችን በስሜት ላይ ሳይሆን በእውነት ላይ ነው፡፡ ዓለም በክፋት ወደ ፊት እየገሰገሰ ሳለ ምንም ችግር አይገጥመንም በማለት ማናችንም ብንሆን ራሳችንን ማታለል የለብንም፡፡ {2SM 157.2} Amh2SM 157.2

እነዚህ ችግሮች ዘላለማዊ ጥበብ ካለው ምክር ለመፈለግ ወደ ልኡል ሕዝብ መሰብሰቢያ ክፍል የሚያመጡን ናቸው፡፡ እንድንፈልገው ይወዳል፤ እንድንታመንበትና ቃሉን እንድናምን ይወዳል፡፡ ግራ መጋባቶችና ፈተናዎች ባይኖሩን ኖሮ በራሳችን የምንተማመንና በራሳችን የተኮፈስን እንሆን ነበር፡፡ እውነተኛ ቅዱሳን የነጹ፣ የነጡ እና የተፈተኑ ይሆናሉ፡፡ --Letter 58, 1909. {2SM 157.3} Amh2SM 157.3