የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

125/349

ምዕራፍ 17—አንድነትና ታማኝነት

[Appeared In Notebook Leaflets, Christian Experience, No. 7.]

ጌታ ለእነዚህ የመጨረሻ ቀናት የሚሆነውን የእውነት እውቀት ለማስፋፋት ሥራው በሚስዮናዊ መስመር ወደ ፊት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡ በዘጸአት 31፡12-18 ላይ እንደተመለከተው የእግዚአብሔር ማህተም በላያቸው ያላቸው ሰዎች የሚሰሩትን ታላቅ፣ የተከበራ ሥራ ለማየት ዓይኖቻቸው በሰፊው መገለጥ ባለባቸው ሰዎች ላይ በእርግጠኝነት ማታለያ አለባቸው፡፡ {2SM 158.1} Amh2SM 158.1

ጌታ ታማኝ መጋቢዎች ወደ ሥራ መስክ እንዲላኩና በእነዚህ መስኮች ሥራውን ለማስፋፋት የእርሱን የገንዘብ ምንጮች በጥበብ እንዲጠቀሙ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የሚተባበር ሕዝብና አገልግሎት አለው፡፡. . . {2SM 158.2} Amh2SM 158.2

ሕዝቡ መንፈስ ቅዱስን ለመጠቀም ሳያስቡ መንፈስ ቅዱስ ሥራ እንዲሰራባቸው ራሳቸውን የሚሰጡ ከሆነ እግዚአብሔር ለእነርሱ ይሰራል፡፡ «እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው?” (ዘዳ. 10፡12፣13)፡፡ . . . {2SM 158.3} Amh2SM 158.3

በዓለማችን ላይ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሚሰሩት እጅግ የከበረ ቅዱስ ሥራ አለ፡፡ ፍጻሜው ቅርብ ነው፡፡ የእውነት መልእክት መሄድ አለበት፡፡ እንደ መንጋው ታማኝ እረኞች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ግልጽና የሰላ ምስክርነት ሊሸከሙ ነው፡፡ እውነት መጣመም የለበትም፡፡ መለኮታዊ ጸጋ ከምህረትና ከእግዚአብሔር ፍቅር በፍጹም አያርቅም፡፡ ይህን የሚያደርግ የሰይጣን ኃይል ነው፡፡ ክርስቶስ በሰበከ ጊዜ መልእክቱ በሁለት ወገን እንደተሳለ ስለታም ሰይፍ የሰዎችን ህሊና የሚወጋና የውስጣቸውን ሀሳብ የሚገልጽ ነበር፡፡ ክርስቶስ የሰራውን ሥራ የእርሱ ታማኝ መልእክተኞችም መስራት አለባቸው፡፡ በትህትና፣ በንጽህና እና እጅግ ጥብቅ በሆነ ሀቀኝነት ቃሉን ይሰብካሉ፡፡ በቃል ወይም በአስተምህሮ የሚሰሩ ለሀላፊነታቸው ታማኝ መሆን አለባቸው፡፡ ተጠያቂነት እንዳለባቸው ሰዎች ነፍሳትን መጠበቅ አለባቸው፡፡ «እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣» የሚለውን ዓረፍተ ነገር በሚያጠምዱ የሰው የጥበብ ቃላት በፍጹም አያለብሱአቸውም፡፡ ካደረጉ ግን ቃሉ ኃጢአትን ማሳመን እንዳይችል ደካማና ኃይል የለሽ በማድረግ ሕያው ጉልበቱን ያጠፋሉ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት የተነገረ እያንዳንዱ ቃል ለነፍሳት ድነት እጅግ ጥልቅ በሆነ ጭንቀት የተሞላ ይሆናል፡፡ {2SM 158.4} Amh2SM 158.4

የአገልጋይ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት የሚወሰነው በውጫዊ ታይታ ሳይሆን ተግባሩን በታማኝነት በመፈጸሙ ነው፡፡ ወደ ከፍታ የሚመራው የክርስቶስ መንገድ የሚገኘው እጅግ በጣም ጥልቅ በሆነ ራስን ዝቅ በማድረግ ውስጥ ነው፡፡ ከክርስቶስ ጋር በመከራው ተካፋዮች የሆኑ፣ በደስታ ዱካውን የሚከተሉ፣ በክብሩ ከእርሱ ጋር ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡ {2SM 159.1} Amh2SM 159.1

በአብዛኛው እውነት ከሆነ ነገር ጋር የሚስማሙ፣ ነገር ግን ያልተለወጡ ሰዎችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማስገባት ሰይጣን ያለማቋረጥ ጥረት ያደርግበት የነበረ ነገር ነበር፡፡ ለተሰጣቸው ኃላፊነት እውነተኛ ያልሆኑ ክርስቲያን ነን ባዮች ሰይጣን የሚሰራባቸው መስመሮች ናቸው፡፡ ያልተለወጡ የቤተ ክርስቲያን አባላትን የራሱን ሀሳቦች ለማስፋፋትና የእግዚአብሔርን ሥራ ወደ ኋላ ለማስቀረት ሊጠቀምባቸው ይችላል፡፡ ተጽእኖአቸው ሁል ጊዜ በስህተት አቅጣጫ ነው፡፡ በተሃድሶ መንገድ ላይ ትችትንና ጥርጣሬን እንደ ማሰናከያ አለቶች ያስቀምጣሉ፡፡ ለክርስቶስ ጽድቅ ዓይኖቻቸውን ስለጨፈኑ እና የእግዚአብሔርን ክብር እንደ ሽልማት አድርገው ስላልያዙ አለማመንን ያስገባሉ፡፡ {2SM 159.2} Amh2SM 159.2

አንድነት የቤተ ክርስቲያን ብርታት ነው፡፡ ሰይጣን ይህንን ስለሚያውቅ ጠብ ለማምጣት መላ ኃይሉን በሥራ ላይ ያሰማራል፡፡ በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አባላት መካከል መስማማት ጠፍቶ ማየት ይፈልጋል፡፡ ለአንድነት ጉዳይ ታላቅ ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡ የጠብና የጥላቻ ለምጽን ለመፈወስ የአሰራር መመሪያው ምንድን ነው? የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መታዘዝ ነው፡፡ {2SM 159.3} Amh2SM 159.3

ቤተ ክርስቲያንን የሚያዳክሙ ልዩነቶችን እያጎላን ማውራት እንደሌለብን እግዚአብሔር ሲያስተምረኝ ነበር፡፡ ጥላቻን የሚፈውስ መድሃኒት ያዛል፡፡ ሰንበትን በቅድስና በመጠበቅ ሕዝቡ መሆናችንን ማሳየት አለብን፡፡ ሰንበት ትዕዛዛትን የሚጠብቁ ሰዎችን ከሌሎች የሚለይ ምልክት እንደሆነ ቃሉ ይናገራል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ እርሱ ፈጣሪያቸው የመሆኑን እውቀት በመካከላቸው ጠብቀው ማቆየት አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚጠብቁ ሰዎች በሰማይ በሰይጣንና በእግዚአብሔር መካከል በተጀመረው ታላቁ ተጋድሎ ከእርሱ ጋር አንድ ይሆናሉ፡፡ ለእግዚአብሔር ታማኝ አለመሆን ማለት በእግዚአብሔር ሕግ መርሆዎች ላይ ጠብና ጥላቻ ማንሳት ነው፡፡ {2SM 160.1} Amh2SM 160.1

ከእግዚአብሔር ጉዳይ ጋር የተገናኘ እያንዳንዱ ነገር ቅዱስ ስለሆነ በሕዝቡ መከበር አለበት፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ የሚጠቅሱ ምክሮች ቅዱስ ናቸው፡፡ ክርስቶስ ሕይወቱን የሰጠው ኃጢአተኛ ዓለምን ወደ ንስሃ ለማምጣት ነው፡፡ በክርስቶስ ባደረ መንፈስ የተሞሉ ሰዎች ለእርሱ የወይን ቦታ በመጠንቀቅ እንደ እግዚአብሔር ገበሬዎች ይሰራሉ፡፡ ዝም ብለው ራሳቸው በመረጡት ቦታ አይሰሩም፡፡ ክርስቶስ የሰጣቸውን ታላቅ ሥራ መፈጸምን እጅግ ከፍተኛ ዓላማቸው አድርገው ጠቢብ ሥራ መሪዎችና ሰራተኞች መሆን አለባቸው፡፡ አዳኛችን ወደ ሰማይ ከማረጉ በፊት ለደቀ መዛሙርቱ በኢየሩሰሌም በመጀመር ወደ ሕዝብ፣ ነገድ፣ ቋንቋ፣ ወገን ሁሉ መሄድ እንዳለባቸው ነገራቸው፤ አክሎም እንዲህ አለ፣ «እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ» (ማቴ 28፡20)፡፡ --Manuscript 14, 1901. {2SM 160.2} Amh2SM 160.2