የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

300/349

አንድ ላይ ሆናችሁ ወደ ፊት ግፉ፣ በአንድነት ወደ ፊት ግፉ

በየቀኑ ልቦቻችን በክርስቶስ የፍቅር ሰንሰለት እንዲያያዙ እንደምንሞክር አድርጋችሁ ገምቱ፡፡ እውነተኛው ምስክር «የምነቅፍብህ ነገር አለ፣ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና” ይላል (ራዕይ 2፡ 4)፡፡ አክሎም «ንስሃ ካልገባህ በስተቀር ፈጥኜ እመጣለሁ፣ መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ” ይላል (ራዕይ 2፡ 5)፡፡ ለምን ? ይህ የሚሆንበት ምክንያት ከእርስ በርሳችን ስንለያይ ከክርስቶስም ስለተለየን ነው፡፡ አብረን ወደ ፊት መግፋት አለብን፡፡ በእግዚአብሔርና በቅዱሳን መላእክት ፊት የሆንኩ ይመስለኝ በነበሩ ጊዜያቶች የመልአክ ድምጽ «አብራችሁ ወደ ፊት ግፉ፣ አብራችሁ ወደ ፊት ግፉ፣ አብራችሁ ወደ ፊት ግፉ፣ ሰይጣን ገሃነማዊውን ጥላ በወንድሞች መካከል እንዲያጠላ አትፍቀዱለት፡፡ አብራችሁ ወደ ፊት ግፉ፤ በአንድነት ብርታት አለ» ሲል የሰማኋቸው ጊዜያቶች ምንኛ ብዙዎች ናቸው፡፡ Amh2SM 374.2

መልእክቱን እደግምላችኋለሁ፡፡ ወደየቤታችሁ ስትሄዱ አብራችሁ ወደ ፊት እንደምትገፉ ወስኑ፤ እግዚአብሔርን በሙሉ ልብ ፈልጉት፣ ታገኙትማላችሁ፤ ከማስተዋል በላይ የሆነው የክርስቶስ ፍቅር ወደ ልባችሁና ወደ ሕይወታችሁ ይመጣል፡፡ General Conference Daily Bulletin, April 13, 1891. Amh2SM 374.3