የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
የሀኪሞችን ደሞዝ በተመለከተ የተደረገ ጠቃሚ ቃለ መጠየቅ
{በሕዳር 4 ቀን 1913 ዓ.ም የፓስፊክ ዩኒየን ኮንፍራንስ መሪ ወንድሞች በጤና ማሰልጠኛ ተቋማችን ውስጥ የሚሰሩ ሀኪሞችን ደሞዝ በተመለከተ ለመወያየት ከሚስስ ኋይት ጋር በኤልምሻቬን ባለው ቤቷ ውስጥ ተሰበሰቡ፡፡ ቃለ መጠይቁ በአጭር የተወሰደ ዘገባ የተዘጋጀለት ሲሆን የመጀመሪያው ቅጂ ሚስስ ኋይት በሚከተሉት ቃላት ማረጋገጫ የሰጠችውን በእጅ የተጻፈ ማስታወሻ ይዟል፡- «ይህ በትክክል የተጻፈ ስለሆነ ለሌሎች ጥቅም ስል እደግመዋለሁ፡፡ በሚያጋጥሙን ችግሮቻችን ጌታ ይርዳን፣ ያስተምረን፣ ይምራንም፡፡” የዚህ ቃለ መጠይቅ ዘገባ ጠቃሚ የሆኑ ክፍሎች ቀጥሎ ቀርበዋል፡፡ …አሰባሳቢዎች፡፡--} Amh2SM 202.2
በስብሰባው ላይ የነበሩ አባላት፡- ኤለን ጂ ኋይት፣ ኤፍ ኤም በርግ፣ ጂ ደብልዩ ሪዘር፣ ደብልዩ ኤም አዳምስ፣ ጄ ኤች ቤህሬንስ፣ ሲ ኤል ታጋርት፣ ኤ ጂ ክርስቲያንሰን፣ ደብልዩ ሲ ኋይት የሚባሉ ሽማግሌዎችና ሲ ሲ ክሪስለር ናቸው፡፡ Amh2SM 202.3
ትውውቅና ሰላምታ ከቀረበ በኋላ ሽማግሌው ደብልዩ ሲ ኋይት በከፊል እንዲህ አለ፡- Amh2SM 202.4
ትናንት ቀኑን በሙሉ የተለያዩ ትምህርት ቤቶቻችንን እና የፓስፊክ ዩኒየን ኮንፍራንስን ፍላጎቶች እየተመለከትን ነበር፡፡ በአንግዊን፣ ሎዲ፣ ፌርናንዶ፣ አርሞና እና ሎማ ሊንዳ ባሉት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመሰልጠን ላይ ያሉ ከስድስት መቶ እስከ ሰባት መቶ የሚሆኑ ተማሪዎች አሉ፡፡ Amh2SM 202.5
ዛሬ የምንመለከተው የጤና ማሰልጠኛ ተቋምን ችግሮች፣ በተለይም ለሀኪሞችና ለቀዶ ጥገና እስፔሻሊስቶች መክፈል ስላለብን የደሞዝ ጥያቄ ይሆናል፡፡ በ---ባለው የጤና ማሰልጠኛ ተቋማችን ውስጥ ከእርሱ ጋር አብረው የሚሰሩትን ሰዎች ሁሉ እምነት ያተረፈ፣ ለበሽተኞች በሚሰጠው አገልግሎት እግዚአብሔር አብዝቶ የባረከው ሀኪም አለ፡፡ እርሱ ራሱ መቆየት የሚፈልግ ሲሆን ሁሉም ሰው እርሱ እንዲቆይ ይፈልጋል፤ ወንድሞች ለአማካይ ሰራተኞች የሚሰጡትን ደሞዝ እጥፍ ከከፈሉት በጤና ተቋሙ ውስጥ መቆየት ተገቢ እንደሆነ ይሰማዋል፡፡ በነጻ መስጠት ስለሚወድ ለዚህ ዓለማና ለኑሮ በቂ የሆነ ገንዘብ እንዲኖረው ይሻል፡፡ ይህ ጉዳይ እጅግ ግራ ስላጋበን በዚህ ጉዳይ ላይ ብርሃን ካለሽ ብናውቅ ደስ ይለናል፡፡ Amh2SM 202.6
እህት ኋጥት፡- ለእርሱ ከሌሎች ሀኪሞች ከሚከፈል የበለጠ ደሞዝ ከተከፈለው ሌሎቹም እንደ እርሱ ካልተከፈላቸው በቀር በትክክል እንዳልተያዙ ያምናሉ፡፡ በጥንቃቄና በማስተዋል መንቀሳቀስ አለብን፣ ብዙዎች እስከሚፈተኑ ድረስ ደሞዝ ወደ ላይ እንዲነሳ መፍቀድ የለብንም፡፡ መሰራት ያለበት ትልቅ ስራ ስላለ የሀኪሞችን ደሞዝ በተመለከተ ወደ ላይ መጨመር ሳይሆን ወደ ታች ማውረድ ሊኖር ይችላል፡፡ የሆነ ግልጽ ብርሃን ከጌታ ካልተሰጣችሁ በቀር ለአንድ ሰው ተመሳሳይ ሥራ ከሚሰሩት ሰዎች ይልቅ የጎላ ልዩነት ያለው ከፍተኛ ደሞዝ መክፈል አይመከርም፡፡ እንደዚህ ካደረጋችሁ ሌሎችም ተመሳሳይ የሆነ ከፍተኛ ደሞዝ ማግኘት እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡ ነገሮችን ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ መመልከት አለብን፣ አንድ የተዋጣለት ሰራተኛ ከፍተኛ ደሞዝ ስለጠየቀ ብቻ መስጠት እንችላለን ብለን ማሰብ ጥቅም የለውም፡፡ ነገር ግን እስካሁን ወጪ ካደረግነው የበለጠ ወጪ የሚጠይቁ የሥራ መስኮች እየተከፈቱ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ምን ያህል መክፈል እንደምንችል ማሰብ አለብን፡፡ Amh2SM 203.1
ደብልዩ ሲ ኋይት፡- እናት ሆይ፣ በተለይ የሰራተኞች ቡድን አንድን ሰው እስከሚወዱትና እስከሚያደንቁት ድረስ አብረውት ከሰሩ እና ያ ሰው ከማንም ይልቅ የተሻለ ሥራ እንደሚሰራ እስካመኑ ድረስ እምነታችንን ይፈትናሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ ለጠቃሚ ነገር ሊጠቀምበት የሚችለውን ነገር ወንድሞች የሚከለክሉ ከሆነ ስህተት ነው ብለው ማሰባቸው የማይቀር ነው፡፡ እንዲህ ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፣ « ሕይወትን በሚመለከት ጉዳይ ላይ አንድ ሺህ ዶላር ወይም አንድ ሺህ አምስት መቶ ዶላር ተጨማሪ መክፈል ምን አለው?» እንዲህ ይላሉ፣ «እሱ መፍትሄ ያስገኘላቸው እንዲህ እና እንዲህ ያሉ ጉዳዮች ያሉ ሲሆን እርሱ ሕይወቱን ያዳነው ሌላ ሰው አለ»፤ እንዲህ ዓይነት ሰው የሚፈልገውን ነገር አለማድረግ አስገራሚ የሆነ ስስታምነት ነው ብለው ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ እንዲህ ይላሉ፣ «እንደ ቀዶ ጥገና ሀኪም የሚሰራና የሚሰቃይ ማንም የለም፡፡ ክቡር የሆነች ነፍስ ቀጭን በሆነ ክር ላይ ተንጠልጥላ ሳለች ይህ ሀኪም ተግቶ የሚሰራቸውን ሰዓቶች፣ ስጋትና የአእምሮ ጭንቀት አስቡ፡፡» Amh2SM 203.2
ነገር ግን ይህን ጉዳይ ከግምት ውስጥ ስናስገባ ሳለ በሌላ ወገን ደግሞ በድርጊታችን ሌሎች ተቋሞች ተጽእኖ እንደሚደርስባቸው ማሰብ አለብን፡፡ ችሎታ ያለው ሀኪም ካገኘ ገንዘብ ለማግኘትና ከፍተኛ የሆነ ንግድ ለማድረግ በሚመች ቆንጆ በሆነ ቦታ ተቀምጦ ሳለ ለመኖር እየታገለ ያለን ደካማ የሆነ የጤና ማሰልጠኛ ተቋም እንመለከታለን፤ ጥሩ ሀኪም ማግኘት የሚችሉት ከተወሰነው የደሞዝ መጠን ሶስት መቶ ወይም አምስት መቶ ዶላር አስበልጠው መክፈል እንደሚችሉ ቢደፋፈሩ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፣ «እንድንከፍል ከተወሰነው በላይ ጥቂት መቶ ዶላሮችን ብቻ ጨምረን እንድንከፍል ከፈቀዳችሁልን ይህን ለደሞዝ ወጪ የሆነውን ለመሸፈን አምስት ሺህ ዶላሮችን ማግኘት እንችላለን፡፡» ከንግድ አንጻር ስንመለከት እንደዚህ ይመስላል፡፡ Amh2SM 204.1
እህት ኋይት፡- በዚያ ነገር ሥር እግዚአብሔር ያልተደሰተበት ራስ ወዳድነት አለ፡፡ በመስማማት መስራት አለብን፡፡ ሥራችን ወደ ፊት መቀጠል ያለበት ስምምነት ባለበት ተግባር ሲሆን አንዳንዶች በጣም ይከብዳቸዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ይቀላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ነገሮች ሁሉ እንደ አመጣጣቸው መወሰድ ያለባቸው ሲሆን ሰራተኞች ኢየሱስ ወደ እኛ ዓለም በመምጣት የሰጠውን ነገር ማሰብ አለባቸው፡፡ ስለዚህ ነገር ደግሜ ደጋግሜ አስባለሁ፣ ትክክለኛ የሆነ ምሳሌ መሆን ከቻልን እጅግ በጣም ጥሩ ሥራ የምንሰራ ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ወንድሞቻችን የማያገኙትን ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ ከተመኘን፣ ይህ ድርጊት የምናሳድረውን ተጽእኖ ይጎዳል፡፡ ወንድማችን «እገሌና እገሌ የሚባሉ ወንድሞች ይህን ያህል ደሞዝ ስላላቸው እኔም የእነርሱን ያህል ማግኘት አለብኝ፡፡» እንዲህ ሲሆን ደሞዝ ወደ ላይ የሚያሻቅብ ይሆንና ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ላይ ማሻቀቡን ይቀጥላል፡፡ እውነታው ግን ዓለምን ለማስጠንቀቅ ከፊታችን የተቀመጠው ሥራ ከሚጠይቀው ሰፊ ወጪ አንጻር የአንዳንዶች ደሞዝ ዝቅ እያለ መሄድ ይኖርበታል፡፡ . . . Amh2SM 204.2
ባለፈው ዓመት፣ ይህ የደሞዝ ጉዳይ ይታይ በነበረበት ጊዜ፣ እርምጃ እንድንወስድ ስለመራን መንፈስ ጌታ ሙሉ በሙሉ እንደሚያውቅና እኛ ባልጠበቅን ጊዜ እርሱ ነገሮችን ወደ መልካም እንደሚለውጥ ነግሬያቸው ነበር፡፡ ትክክለኛ የሆነ ምሳሌነትን እያስቀመጥን ስንሄድ የጌታ በረከት በላያችን ያርፋል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በትክክለኛ ብርሃን የሚመለከቱትንና ራስን መስዋዕት የማድረግ ምሳሌ የሚያሳዩ ሰዎችን ለመርዳት ጌታ በብዙ መንገድ እና በብዙ ቦታዎች ሲሰራ አይቻለሁ፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ በጸሎት፣ ራሳችሁን ዝቅ በማድረግ፣ በክርስቶስ መንፈስ ተግታችሁ እየሰራችሁ ሳለ ጌታ በፊታችሁ ደጆችን ይከፍትላችኋል፡፡ ሕዝብ ራሳችሁን መካዳችሁን ይመለከታል፡፡ Amh2SM 204.3
ወንድሞቼ ብዙ ደሞዝ መጠየቅ እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው ለማወቅ ምክር ፈልገው ወደ እኔ በመጡ ጊዜ ከፍተኛ ደሞዝ ጠይቀው ጥቂት ገንዘብ ሊያገኙ እንደሚችሉ ነግሬያቸው ነበር፣ ነገር ግን የተለየ መንገድ የሚከተሉትን የእግዚአብሔር በረከት ይከተላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር የሚመለከተው ራስን መካድን ነው፤ የእሥራኤል ጌታ እግዚአብሔር አንድን ነገር ለማድረግ ያነሳሳውን እያንዳንዱን ውስጣዊ ምክንያት ይመለከታል፤ ከባድ ወደሆኑ ቦታዎች ስትመጡ ሊረዱአችሁና በድል ላይ ድልን ሊያቀዳጇችሁ የእግዚአብሔር መላእክት በዚያ ቦታ ናቸው፡፡ Amh2SM 205.1
ነፍስን በማዳን ሥራ ውስጥ ጉልበታችንን ወደማባከን የሚመራን አስገዳጅ ምክንያት እንዳልሆነ ወንድሞችን በማያሻማ ሁኔታ መክሬያቸዋለሁ፡፡ Amh2SM 205.2
አገልግሎታችን በሚፈለግበት ቦታ ሁሉ ለተጠራንበት ተግባር ምላሽ እንዳንሰጥ የደሞዝ ጥያቄ መንገድ መዝጋት የለበትም፡፡ እግዚአብሔር ከምንቀበለው ወይም ከማንቀበለው ካሣ እጅግ የበለጠ በረከት ስራችንን እንዲከተል ነገሮችን ያስተካክላል፤ ባሪያዎቹ እየጠፉ ላሉ ነፍሳት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ውጤት ያለውን ነገር እንዲናገሩ ቃላት ይሰጣቸዋል፡፡ Amh2SM 205.3
ሰዎች ከሰማይ የሆነውን እርዳታ እየተራቡና እየተጠሙ ናቸው፡፡ እነዚህን ራስን መስዋዕት የማድረግን መርሆዎች ለመተግበር ስለሞከርኩ የተጠራህበትን ተግባር ስታስቀድም የእግዚአብሔር በረከት በላይህ ያርፋል ስል ምን እየተናገርኩ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ጌታ ከምንጠይቀው በላይ አብልጦ ሊሰጠን በተደጋጋሚ ነገሮችን እንደለወጠ በዚህ ጧት በፊታችሁ ለመመስከር በመታደሌ ደስ ይለኛል፡፡ Amh2SM 205.4
ጌታ አገልጋዮቹን ይፈትናል፤ ለእርሱ ታማኝ ከሆኑ እና ጉዳዮቻቸውን ለእርሱ ከተዉ ችግር በሚገጥማቸው በማንኛውም ጊዜ ይረዳቸዋል፡፡ Amh2SM 205.5
ከእግዚአብሔር ጋር አብረን ሰራተኞች የሆንነው በአገልግሎቱ ውስጥ ስለምናገኘው ደሞዝ አይደለም፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ ቤተሰቦቻችሁን ለማስተዳደር የሚያስችል ደሞዝ ማግኘት እንዳለባችሁ እሙን ነው፤ ነገር ግን ምን ያህል እንደምታገኙ ማስላት ከጀመራችሁ ምናልባት ለጋስ መሆን እንዳለባችሁ የማሰብ ዝንባሌ ለሌለው ለሆነ ሰው የመሰናከያ አለት ልትሆኑ ትችላላችሁ፤ ውጤቱም ግራ መጋባት ይሆናል፡፡ ሌሎች ደግሞ ሁሉም በእኩልነት እንዳልታዩ ያስባሉ፡፡ ብዙም ሳትቆዩ የእግዚአብሔር ሥራ እጅግ አንሶ ታገኙታላችሁ፤ ይህ ለማየት የማትፈልጉት ውጤት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ ከፍ ባለ ቦታ ተቀምጦ ለማየት ትሻላችሁ፡፡ በምሳሌነታችሁና በቃላቶቻችሁ በልብ ውስጥ ተቀባይነት ያገኘው እውነት ራስን የመካድ መንፈስ መውለዱን ሰዎች ሕያው የሆነ መተማመኛ ማግኘት አለባቸው፡፡ በዚህ መንፈስ ወደ ፊት ስትጓዙ የሚከተሉአችሁ ብዙዎች አሉ፡፡ Amh2SM 205.6
ጌታ ሥራው መሰራት ያለበት ስለሆነ በደንብ በመስራታችን ለራሳችን እርካታ ሊያመጣልን በሚችል መንገድ ራስን በመካድና መስዋዕት በማድረግ ልጆቹ መስራት ያለባቸውን ስራ እንዲሰሩ ይሻል፡፡ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ አሰቃቂ ለሆነ የመስቀል ሞት ራሱን ከሰጠ እኛ እንድንከፍል ለተጠራነው መስዋዕትነት ማጉረምረም አለብን ወይ? Amh2SM 206.1
ሌሊት እንቅልፍ ባልወሰደኝ ሰዓታት ወንድሞቻችን ትንሽ ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ የሚያገኙበትን ሁኔታ በማስላት እዚህ ወይም እዚያ ለመሄድ ቃል ከመግባት ዝንባሌ ጌታ እንዲጠብቃቸው እየተማጸንኩት ነበር፡፡ እርሱን በመታመን ራስን መስዋዕት በማድረግ መንፈስ ከሄዱ ጌታ አእምሮንና ባሕርይን ጠብቆ የሚያቆይ ኃይል ይሰጣቸውና ውጤቱ ስኬት ይሆናል፡፡ Amh2SM 206.2
ባለፉት ጊዜያቶች ካየነው በበለጠ ሁኔታ ራስን በመካድና መስዋዕት በማድረግ ሥራችን ወደ ፊት መቀጠል አለበት፡፡ እግዚአብሔር በብዙ መንገዶች በእኛ አማካይነት መስራት እንዲችል ነፍሳችንን ለእርሱ አሳልፈን እንድንሰጥ ይፈልጋል፡፡ ወንድሞች ሆይ፣ በየዋህነትና ዝቅ ባለ አእምሮ እንራመድ፣ ከእኛ ጋር ግንኙነት ላላቸው ሰዎችም ራስን መስዋዕት የማድረግን ምሳሌ እናሳያቸው፡፡ ድርሻችንን በእምነት ከሰራን እግዚአብሔር እኛ አልመን የማናውቃቸውን መንገዶች በፊታችን ይከፍትልናል፡፡ . . . Amh2SM 206.3
ሥራችን ከተመሰረተባቸው ራስን መስዋዕት ከማድረግ መርሆዎች ጋር የማይጣጣም ነገርን የሆነ ሰው ቢያቀርብላችሁ ያ ነገር ለስሙ ክብር የማያመጣ ስለሆነ አንድ የእግዚአብሔር እጅ ንካት ጥቅም መስሎ የታየውን ነገር ሁሉ ጠራርጎ እንደሚወስደው እናስታውስ፡፡--Manuscript 12, 1913. Amh2SM 206.4