የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)
አባካኝነት እና ተጽእኖ
በአገልጋዮቻችን፣ በመምህራኖቻችን እና የጽሁፍ ወንጌላዊያኖቻችን መካከል አእምሮን፣ ልብን እና ነፍስን ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር አሳልፎ የመስጠት አስፈላጊነት አለ፡፡ …ልብስ ወይም ውድ የሆኑ ቤቶች ወይም ቄንጠኛ አኗኗር ለሥራው ተገቢ የሆነ ባሕርይ አይሰጥም፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ትልቅ ዋጋ ያለው የዋህና ጸጥ ያለ መንፈስ ነው፡፡ ኃይማኖት ሰውን ሸካራና ያልተገራ አያደርግም፡፡ እውነተኛ አማኝ የራሱን ድክመት በመረዳት በእያንዳንዱ ነጥብ ራሱን እየጠበቀ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ይታመናል፡፡ እውነተኛ የሆነ ክርስቲያናዊ እግዚአብሔርን መምሰል በግዴታ ሊሆን አይችልም፤ ታማኝ ከሆነ ልብ የሚፈልቅ ነገር ነው፡፡.... Amh2SM 201.5
እግዚአብሔር ጥንቁቅ፣ የሚጸልዩና ተግባር ያላቸውን ሰዎች ይፈልጋል፡፡ ውድ የሆነ ውጫዊ ታይታ ነገሮችን በትክክል በሚያገናዝቡ ሰዎች ዘንድ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ክብር አይጨምርላቸውም፡፡ ለታይታ ሲባል ብክነት ያለበትን ወጪ ማድረግና ቀላል ቀዶ ጥገናን ስላደረገ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ መጠየቅ ለሐኪም ተገቢ አይደለም፡፡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር በትክክለኛ ብርሃን ይመለከታቸዋል፡፡-- Manuscript 34, 1904. Amh2SM 202.1