የተመረጡ መልእክቶች (ሁለተኛው መጽሐፍ)

168/349

አንገብጋቢ ሁኔታን መጋፈጥ

የገንዘብ እጥረት ሲገጥማችሁ፣ ብቁ የሆኑ ሰራተኞቻችሁ የራሳቸውን ሥራ ለመጀመር እንዲሄዱ ከተዋችኋቸው፣ ከአጭር ጊዜ በኋላ መልሳችሁ ለማምጣት ትመኛላችሁ፡፡ የገንዘብ ጥያቄ በጥሩ ሁኔታ ሊያዝ የሚችለው የገቢ እጥረት ጫና ሲኖር ሰራተኞች በሙሉ አነስተኛ የሆነ ደሞዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ሲሆኑ ነው፡፡ ይህ ወደ ማተሚያ ቤቶቻችን እንዲመጣ ጌታ ያሳየኝ መርህ ነበር፡፡ ብዙ የሚሰራ ነገር ይኖርና ሥራው እነዚህኑ ሰዎች ይፈልጋል፡፡ የገንዘብ እጥረት በሚያጋጥምበት ጊዜ ፍላጎቶቻችንን ለመገደብ ፈቃደኛ መሆን የለብንምን? Amh2SM 207.1

እኔና ባለቤቴ በዚህ መርህ ሰርተናል፡፡ እንዲህ አልን፣ «ማተሚያ ቤት የጌታ ተቋም ስለሆነ በተቻለን መጠን ወጪዎቻችንን በመቀነስ እንቆጥባለን፡፡” የጌታ ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥልና እንዲሳካ ሁሉም አገልጋዮቹ ራሳቸውን መስዋዕት እንዲያደርጉ እርሱ ይፈልጋል፡፡ በ---ያለውን የማተሚያ ቤት ለማስቀጠልና ለመጠበቅ እያንዳንዱ ሰራተኛ የሚቻለውን ሁሉ ያድርግ፡፡ ጌታ በተቋሞቻችን ሁሉ ውስጥ ይህንን በመንፈስ ቁጥጥር ሥር መሆንን በማየት የማይደሰት ይመስላችኋልን? መርህን ወደ ሥራ ማምጣት አለብን፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ «ማንም እኔን መከተል ቢወድ ራሱን ይካድ፣ መስቀሉንም በየዕለቱ ተሸክሞ ይከተለኝ” (ሉቃስ 9፡ 23)፡፡ ክርስቶስን ለመከተል ዝግጁ ነን ወይ?--Letter 25, 1896. Amh2SM 207.2

ተቋሞቻችን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር መሆን አለባቸው፡፡ በመስዋዕትነት የተቋቋሙ ሲሆን ሥራው በተሳካ ሁኔታ ወደ ፊት መቀጠል የሚችለው በመስዋዕትነት ብቻ ነው፡፡-- Letter 129, 1903. Amh2SM 207.3

ሰብአዊ ጥበብ ራስን ከመካድና ከቅድስና በማራቅ የእግዚአብሔር መልእክቶች ምንም ውጤት እንዳይኖራቸው የሚያደርጉ ብዙ ነገሮችን ይቀይሳል፡፡--The Review and Herald, Dec. 13, 1892. Amh2SM 207.4