የልጅ አመራር

31/85

ምዕራፍ 29—ታማኝነት እና ሐቀኝነት

ታማኝነት መተግበር እና መስተማር አለበት— የታማኝነት በሁሉም የእናቶች ሕይወት ውስጥ መተግበር በጣም አስፈላጊ ነው፣ በወጣቶችም ስልጠና ውስጥ ሴቶች እንዲሁም ወንዶች ቅንጣትም ያህል ቢሆን እንዳይዋሹ ወይም እንዳያታልሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ 268 CGAmh 144.1

እግዚአብሔር የሚጠይቀው መስፈርት—እግዚአብሔር በአገልግሎቱ ውስጥ ያሉት፣ በሰንደቅ ዓላማው ሥር ያሉት ሰዎች፣ ምላሶቻቸው ሐሰት የሚመስል አንዳች ነገር እንዳይናገር በጥብቅ ሐቀኛ፣ በባህሪያቸው የማይነቀፉ፣ እንዲሆኑ ይፍልጋል፡፡ አንደበት ታማኝ መሆን አለበት፣ ዐይኖች ታማኝ መሆን አለባቸው፣ ተግባራትም ሙሉ በሙሉ ልክ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚመሰገን መሆን አለበት፡፡ የምንኖረው “ሥራህን አውቃለሁ” ሲል በተናገረው ቅዱስ አምላክ ፊት ነው፡፡ መለኮታዊ ዐይን ሁልጊዜ በእኛ ላይ ነው፡፡ አንዳችም ኢፍትሐዊ የሆነ ድርጊት ከእግዚአብሔር ልንደብቅ አንችልም፡፡ እያንዳንዱን ተግባራችንን እግዚአብሔር መመልከቱ ጥቂቶች የሚገነዘቡት ሐቅ ነው፡፡269 CGAmh 144.2

በእግዚአብሔር ላይ መደገፋቸውን የተገነዘቡ ሰዎች ለወንድሞቻቸው ታማኝ መሆን እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ የህይወት በረከቶች ሁሉ ከእርሱ ለሆነው ታማኞች መሆን አለባቸው፡፡ አሥራትን እና መባዎችን አስመልክቶ የእግዚአብሔር መልካም ትዕዛዛትን ማድበስበስ በመንግሥተ ሰማይ መዝገብ ላይ በእርሱ ላይ እንደ ተፈጸመ ዝርፊያ ይመዘገባል፡፡ 270 CGAmh 144.3

ታማኝ ሚዛን እና ልኬቶች—በክርስቶስ ልኬት መሠረት ታማኝ የሆነ ሰው የማይለወጥ ታማኝነቱን የሚያሳይ ሰው ነው። ብዙዎች ትርፋቸውን በዓለም ውስጥ ከፍ ለማድረግ ሲሹ የሚጠቀሙት አታላይ ሚዛኖች እና የሀሰት ልኬቶች በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ናቸው…፡፡ ጽኑ ታማኝነት ልክ በዓለም ዋጋ ቢስ ነገር እና ቆሻሻ መካከል እንዳለ ወርቅ ይደምቃል፡፡ ማታለያ፣ ውሸት እና ታማኝ አለመሆን ተሸፋፍነው ከሰው ዓይኖች ሊሰወሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዓይኖች ሊሰወሩ አይችሉም፡፡ የባህሪይ እድገትን የሚመለከቱ እና ግብረ-ገባዊ ዋጋን የሚመዝኑ የእግዚአብሔር መላእክቶች እነዚህን ባህሪይን የሚያሳዩ ጥቃቅን ግብይቶችን በሰማይ ቤት መዝገብ ላይ ያሰፍራሉ፡፡ 271 CGAmh 144.4

በጊዜ እና በገንዘብ ታማኝ መሆን—የፍትሃዊነት ስሜታቸው በጥቃቅን ጉዳዮችም እንኳ የማይረቡ እና ልክ ያልሆኑ ነገሮች በጊዜያቸው ውስጥ ስፍራ እንዲያገኝ የማይፈቅዱላቸው ሰዎች ይፈለጋሉ— የእግዚአብሔር የሆነውን ገንዘብ እያስተዳደሩ እንደሆነ የሚገነዘቡ ሰዎች፣ አንድም ሳንቲም ያለአግባብ ለራሳቸው ጥቅም የማያውሉ ሰዎች፤ በቃጣሪዎቻቸው መገኘት እንደሚሆነው ሁሉ ባለመገኘታቸውም በሥራቸው ታማኞች እና ልክ፣ ጠንቃቆችና ትጉህ፣ በታማኝነታቸው ሰዎችን ለማስደስት ብቻ፣ የታይታ አገልጋዮች ሳይሆኑ፣ ነገር ግን ሕሊና ያላቸው፣ ታማኞች፣ እውነተኛ ሰራተኞች፣ ትክክለኛው ነገር የሚሰሩ፣ ለሰው ምስጋና ሳይሆን፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ካላቸው ከፍ ያለ የመታዘዝ ስሜት የተነሳ ትክክለኛ የሆነውን የሚወዱና የሚመርጡ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ 272 CGAmh 145.1

እርሱ ማን እንደሆነ ሌሎች እንዲያስቡ የሚፈልገው ነገር—በእያንዳንዱ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ አንድ ክርስቲያን ወንድሞቹ እርሱ ማን እንደሆነ እንዲያስቡ እንደሚፈልገው እንዲያው ነው፡፡ እርምጃው በመሠረታዊ መርሆዎች ይመራል። እርሱ ሴራ አያሴርም፤ ስለዚህ የሚደብቀው ምንም ነገር የለውም፣ የሚሸፍነውም ምንም ነገር የለውም፡፡ ትችት ሊሰነዘርበት ይችል ይሆናል፣ ሊፈተን ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን የማይናወጥ ታማኝነቱ እንደ ንጹህ ወርቅ ይደምቃል፡፡ ቃሉ የታመነ ስለሆነ ከእርሱ ጋር ለሚገናኙት ሁሉ እርሱ በረከት ነው፡፡ አጋጣሚ በመፈለግ ጎረቤቱን የሚጎዳ ሰው አይደለም፡፡ እርሱ ለሁሉም ጓደኛ እና ደጋፊ ነው፣ ባልደረቦቹም በእርሱ ምክር ይተማመናሉ…፡፡ እውነተኛ ሐቀኛ ሰው የራሱን ቦርሳ ለመሙላት ሲል ድክመትን እና የብቃት መጓደልን እንደ መልካም አጋጣሚ በፍጹም አይጠቀምም።6 CGAmh 145.2

ከጽኑ ታማኝነት ማፈንገጥን አይፍቀዱ—በእያንዳንዱ የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ጽኑ ታማኝ ይሁኑ። ቢፈተኑም እንኳ፣ በጥቃቅን ጉዳዮች እንኳ በፍጹም አያታልሉ ወይም አይዋሹ፡፡ በወቅቱ ተፈጥሯዊ ግፊት ቀጥተኛ ከሆነው የታማኝነት መንገድ ዘወር እንዲሉ ፈተናዎችን ሊያመጣ ይችል ይሆናል፣ ነገር ግን አንድ የፀጉር መስመር ልዩነት ያህል ዘወር አይበሉ። በየትኛውም ጉዳይ ላይ ምን ለማደረግ እንዳሰቡ ከተናገሩ እና ከዚያ በኋላ በራስዎ ኪሳራ ለሌሎች ማድላትዎን ቢገነዘቡ፣ ከመሠረታዊ መርህ የፀጉር መስመር ልዩነት ያህል ዘወር አይበሉ፡፡ ስምምነትዎን ይፈፅሙ፡፡ ዕቅድዎን ለመቀየር በመፈለግዎ ሊታመኑ እንደማይችሉ ያሳያሉ። በትናንሽ ጉዳዮች ወደ ኋላ የሚመለሱ እንደሆነ፣ በትላልቅ ጉዳዮችም ወደ ኋላ ይመለሳሉ። አንዳንዶች በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ ሰዎች አልተረዱኝም በማለት ለማታለል ይፈተናሉ፡፡ ቃላቶቼ ካለምኩት በላይ የሆነ ፍች እንዳላቸው ተወስደዋል፡፡ እውነታው ግን ለማለት የፈለጉት የተናገሩትን ብቻ ነው፣ ነገር ግን ትክክለኛውን ስሜት አጥተዋል፣ ከዚያም በእነርሱ ላይ ኪሳራ እንዳያስከትልባቸው ስምምነታቸውን ማፍረስ ይፈልጋሉ፡፡ ጌታ ፍርድን እንድናደርግ፣ ምህረትን እና እውነትንና ጽድቅን እንድንወድ ይፈልጋል፡፡ 273 CGAmh 146.1

ጽኑ መርሆዎችን መጠበቅ—በሁሉም የሕይወት መደቦች ውስጥ ጽኑ የታማኝነት መርሆዎች መጠበቅ አለባቸው…፡፡ በንግድ ሥራ ውስጥ ከፍጹም ፍትሃዊነት ማፈንገጥ በአንዳንድ ሰዎች ግምት እንደ ትንሽ ነገር ሊታይ ይችላል፣ ነገር ግን አዳኛችን በዚህ አይነት መልኩ አልተመለከተውም። በዚህ ነጥብ ላይ የተናገራቸው ቃላት ግልፅ እና የማያምታቱ ናቸው “ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፡፡” በትንሽ ነገር ባልንጀረውን የሚያሞኝ ሰው ፈተና ወደ እርሱ ቢመጣ በሰፊው ማሞኘቱ አይቀርም፡፡ በትንሽ ነገር መዋሸት በእግዚአብሔር ፊት ልክ በትልቅ ጉዳይም ታማኝትን እንደማጉደል ይቆጠራል፡፡8 ታማኝነት እያንዳንዱን የሕይወት ክዋኔዎቻችንን ማተም አለበት፡፡ የሰማይ መላእክት በእጆቻችን የተሰጠውን ሥራ ይመረምራሉ፤ ከእውነተኛ መርሆዎች ፈቀቅ ማለት ባለበት ሥፍራ ሁሉ፣ “ቀለሃል” የሚል መዝገቡ ላይ ተጽፎ ይገኛል፡፡274 CGAmh 146.2