የልጅ አመራር

30/85

ምዕራፍ 28—ሐቀኛነት

ወላጆች የሐቀኛነት አርአያ ይሁኑ—ወላጆች እና መምህራን፣ ለእግዚአብሔር ታማኞች ይሁኑ፡፡ ሕይወታችሁ ከማታለል ልምዶች ነፃ ይሁን። በከንፈሮቻችሁ ተንኮል አይገኝ። ምንም እንኳ በዚያን ጊዜ ለእናነት የማይመች ሊሆን ቢችል፣ መንገዶቻችሁ፣ ቃላቶቻችሁ እና ሥራዎቻችሁ በቅዱስ አምላክ ፊት ቅንነትን የሚያሳይ ይሁን፡፡ በማታለል የመጀመሪያው ትምህርት ያስከተለው ውጤት እንዴት አስከፊ ነው! የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ ለአታላይነት ድርጊቶች እና ውሸቶች ራሳቸውን አሳልፈው ይሰጣሉን? CGAmh 142.1

ልጆቻችሁ እናታችን እውነት አትናገርም ብለው ለመናገር ሰበብ እንዲገኙ በጭራሽ አታድርጉ፡፡ አባታችን እውነቱን አይናገርም፡፡ በሰማያዊው ችሎት ፊት ለፍርድ ምርመራ በምትቀርብበት ጊዜ መዝገብህ አታላይ በሆንከው በስምህ ሊፈርድብህ ይነሳ ይሆን? ልጆችህ በእውነት መንገድ ሊመሩአቸው በሚችሉ ሰዎች ምሳሌ ይመለሱ ይሆን? ከዚህ ይልቅ የእግዚአብሔር የመለወጥ ኃይል ወደ እናቶች እና አባቶች ልብ ውስጥ አይገባምን? የእግዚአብሔር መንፈስ በልጆቻቸው ላይ ምልክት እንዲያደርግ አይፈቀድለትምን? CGAmh 142.2

ልጆች በአጠቃላይ ቅን ይሆናሉ ብለው መጠበቅ አይቻልም። ግን ጥበብ በጎደለው አያያዝ ወላጆች የልጆችን ተሞክሮ ሊገልጽ የሚገባውን ግልጽነት ያጠፋሉ የሚል ስጋት አለ። ማስመሰል የሌለበት ቀላል የአኗናር ዘይቤን ጠብቆ ለማቆየት ወላጆች በቃላት እና በድርጊት በአቅማቸው ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ መሥራት አለባቸው። ልጆች በዕድሜ እያደጉ ሲሄዱ፣ ወላጆች ወደ ማታለል እና ወደ ውሸት የሚያድግ እና ወደ አለመታመን ልምዶች የሚጎመራ ዘር ለመዝራት ቀንጣት ያህል አጋጣሚ መስጠት የለባቸውም፡፡ 264 CGAmh 142.3

በጭራሽ አትዋሹ—ወላጆች የሐቀኛነት አርአያ መሆን አለባቸው፣ ምክንያቱም ይህ በልጅ ልብ ውስጥ መቀረጽ ያለበት ዕለታዊ ትምህርት ነው፡፡ በሕይወት ጉዳዮች ሁሉ ወላጆችን የማያወላውል መርኾ ሊገዛቸው ይገባል፣ በተለይም በልጆቻቸው ትምህርትና ስልጠና ላይ ይህ ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ “ሕጻን ቅንና ንጹህ መሆኑ በሚያደርገው ሥራ ይታወቃል።” 265 CGAmh 142.4

ማስተዋል የጎደላት እና የጌታን መመሪያ የማትከተል እናት ልጆቿ አታላዮች እና ግብዞች እንዲሆኑ ሊታስተምራቸው ትችላለች። በዚህ መንገድ ከፍተኛ ዋጋ የተሰጠው ባሕርይ በጣም ጽኑ ሊሆን ስለሚችል መዋሸት እንደ መተንፈስ ተፈጥሯዊ ይሆናል፡፡ ማስመሰል የታማኝነት እና የሐቀኝነትን ሥፍራ ይወሰዳል፡፡ 266 CGAmh 143.1

ወላጆች፣ በፍፁም አትዋሹ፤ በመመሪያ ወይም በአርአያነት በጭራሽ ሐሰት አትናገሩ። ልጅዎ እውነተኛ እንዲሆን ከፈለጉ እራስዎ እውነተኛ ይሁኑ፡፡ ታማኝ እና ጽኑ ይሁኑ፡፡ አንዲት ትንሽ ውሸት እንኳ ፈቃድ ማግኘት የለበትም። እናቶች የመዋሸት እና ታማኝ ያለመሆን ልማድ ስላላቸው ልጅም የእሷን ምሳሌ ይከተላል፡፡ 267 CGAmh 143.2

ሐሰተኛነት በማመናጨቅ ቃላት ይበረታታል—ልጆችዎ በሚሳሳቱበት ጊዜ ትዕግስት አይጡ። እነርሱን ሲያርሙ በችኮላ እና በማመናጨቅ አይናገሩ፡፡ ይህ እውነቱን ለመናገር እንዲፈሩ በማድረግ ግራ ያጋባቸዋል፡፡5 CGAmh 143.3