የልጅ አመራር

20/85

ምዕራፍ 18—- ንጽሕና፣ ሥርዓት፣ እና መደበኛነት

ሥርዓታዊነትን እና አመራረጥን ማሳደግ—ሥርዓታዊነትን እና አመራረጥን ማሳደግ የልጆች ትምህርት አንዱ አካል ነው…፡፡ CGAmh 104.1

እንደ ልጆችዎ አሳዳጊና መምህር፣ ቤት ውስጥ የሚተገበሩ እያንዳንዱን ጥቃቅን ነገር በጥሩ ሁኔታ እና በሥርዓት የመሥራት ኃላፊነት ተጥሎብዎታል፡፡ ልጆችዎ ልብሳቸውን ጽዱእ አድርገው እንዲይዙ የማድረግ ተወዳዳሪ የሌለውን ትምህርት ያስተምሯቸው፡፡ ልብስዎን ንጹሕ፣ ያማረ እና የተከበረ አድርገው ይያዙ፡፡ CGAmh 104.2

ቤታችሁ ውስጥ ለእግዚአብሔር ሁልጊዜ በጨዋነት ምሳሌ የመሆን ግዴታ ሥር ናችሁ…፡፡ በሰማይ ስርዓት አልበኝነት እንደሌለ ያስታውሱ፣ እንዲሁ ቤታችሁ እዚህ ታች ያለ ሰማይ መሆን አለበት፡፡ በየቀኑ ቤት ውስጥ መሰራት ያለባቸውን ጥቃቅን ነገሮችን በታማኝነት በመስራት፣ የክርስቲያንን ባህሪይ ፍጹም የምታደርጉ ከእግዚአብሔር ጋር አብራችሁ ሰራተኞች እንደሆናችሁ አስታውሱ፡፡ 183 CGAmh 104.3

ወላጆች ለልጆቻችሁ ድነት እየሰራችሁ እንደሆነ አስተውሉ፡፡ ልማዶቻችሁ ትክክለኛ ከሆነ፣ ንጽሕናን፣ ሥርዓትን፣ ጥሩነትና ጽድቅን፣ የነፍስ፣ የአካል እና የመንፈስ ቅድስና ካሳያችሁ “እናንት የዓለም ብርሃን ናችሁ” ለሚለው ለአዳኙ ቃል ምላሽ ሰጥታችኋል፡፡ 184 CGAmh 104.4

የንጽሕናን ልማድ ያሰልጥኗቸው—እያንዳንዱ ቤተሰብ ስለ ንጽሕና እና ጥንቁቅነት ልማዶች መሰልጠን ይጠበቅበታል፡፡ እኛ እውነትን እናምናለን የምንል የእውነት እና ጽድቅ መርኾዎች ሰዎችን ሻካራ፣ እንደነገሩ የሆነ፣ ቆሻሻ እና የተመሰቃቀለ እንደማያደርጋቸው ለዓለም ማሳየት አለብን….፡፡ CGAmh 104.5

ቤተሰብ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚገለጠው ለልጆቻችን ባለን ፍቅር ነው፡፡ ከልብ የመነጨ ፍቅር ልል እና ቆሻሻ እንዲሆኑ አይተዋቸውም፣ ምክንያቱም ይህ ቀላሉ መንገድ ነው፤ ነገር ግን ወላጆቻቸው በሚያሳዩአቸው የንጽሕና ተምሳሌታዊነት፣ በፍቅር ነገር ግን አምራችነትን በውስጣቸው በሚያሳድግ የማያወላውል ጽናት፣ ልጆቻቸውን በተመሳሳይ ስርዓታዊነት ያስተምሯቸዋል፡፡ 185 CGAmh 104.6

ልጆች ለልብስ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያስተምሯቸው—ልጆች ለልብሶቻቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ገና ከልጅነታቸው ጀምራችሁ አስተምሯቸው፡፡ ዕቃዎቻቸውን የሚያስቀምጡበት ሥፍራ ይኑራቸው፣ እያንዳንዱንም ነገር በጥንቃቄ እንዲያጥፉና በሥፍራው እንዲያስቀምጡ ይማሩ፡፡ ውድ ቢሮ ማዘጋጀት ባትችሉ እንኳ፣ አንድ ጥሩ ደረቅ ሳጥን ከሼልፍ ጋር በመግጠምና በአንድ ደማቅ የሚያምር ስዕል ባለው ጨርቅ በመሸፈን ይጠቀሙ፡፡ ይህ ጥንቃቄና ሥርዓታዊነትን የማስታመር ሥራ በእያንዳንዱ ቀን ጥቂት ጊዜ የሚወስድ ሲሆን፣ ነገር ግን ለወደፊት ለልጆችዎ ወሮታን የሚከፍል፣ እና በመጨረሻም ብዙ ጊዜዎንና ሥራዎን የሚቆጥብ ይሆናል፡፡ 186 CGAmh 105.1

የራስን ክፍል ጽዱዕ አድርገው መያዝ—ልጆች ራሳቸው የኔ ነው ብለው የሚያውቁት ክፍል ያላቸው እና እርሱንም ጽዱዕ እና አስደሳች አድርገው መያዝን የተማሩ እንደሆነ የባለቤትነት ስሜት ይኖራቸዋል— ይህም ማለት፣ ቤት ውስጥ ያለ ያራሳቸው ቤት እንዳላቸው ይሰማቸዋል፣ ንፁህና ጥሩ አድርገው በማያዛቸውም እርካታ ይኖራቸዋል፡፡ እናት የግድ ሥራቸውን መቆጣጠር እና አስተያየቶችን እና መመሪያዎችን መስጠት አለባት፡፡ ይህ የእናት ተግባር ነው፡፡ 187 CGAmh 105.2

መደበኛ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑራቸው—ቀንን ወደ ሌሊት እና ሌሊትን ወደ ቀን የመቀየር ልማድ እንዴት ተስፋፍቶ ይገኛል፡፡ አያሌ ወጣቶች ጠዋት ወፎች ቀደም ብለው በሚዘምሩበት ጊዜ መነሳት እና ፍጥረታት ሁሉ ሲነቁ መንቀሳቀስ ሲኖርባቸው ደህና አድረገው ይተኛሉ፡፡ 6 CGAmh 105.3

አንዳንድ ወጣቶች ከሥርዓት እና ሥነ ምግባር እጅግ የራቁ ናቸው፡፡ በመደበኛ ሰዓት በመንቃት የቤቱን ደንብ አያከብሩም፡፡ ነግቶ እያንዳንዱ ሰው መንቀሳቀስ ባለበት ጊዜ ለተወሰነ ሰዓት አልጋ ላይ ይጋደማሉ፡፡ ተፈጥሮ በጊዜዋ ከምትሰጠው ብርሃን ፈንታ ሰው ሰራሽ ብርሃን ላይ ጥገኛ በመሆን፣ የእኩለ ሌሊቱን ዘይት ያቃጥላሉ፡፡ እንዲህ በማድረግም ውድ አጋጣሚዎቻቸውን ማባከን ብቻ ሳይሆን፣ ለተጨማሪ ወጪ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን በእያንዳንዱ ሁኔታ “ሥራዬን መሥራት አልቻልኩም፤ አንድ ሥራ አለብኝ፤ በጊዜ መተኛት አልችልም” የሚሉ ምክንያቶች ይቀርባሉ፡፡ ውድ የሥርዓት ልማዶች ተበላሽተዋል፣ እናም ገና በጠዋት በዚህ ሁኔታ የጠፋው ጊዜ ሙሉ ቀን ነገሮች ከዕቅድ ውጭ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ CGAmh 106.1

አምላካችን የሥርዓት አምላክ ነው፣ ልጆቹም በሥርዓትና ሥነ-ምግባር ሥር ራሳቸውን ለማድረግ ፈቃደኞች ይሆኑ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህ ሌሊትን ወደ ቀን እና አዲስ የማለዳ ሰዓታትን ወደ ሌሊት የመቀየር ልማድ ቢቀር አይሻልም? ወጣቶች የመደበኛነትን እና የሥርዓታዊት ልማድ ቢኖራቸው፣ በጤና፣ በመንፈስ፣ በማስታወስ እና በባህሪይ የተሻሻሉ ይሆኑ ነበር፡፡ CGAmh 106.2

በሕይወት ልማዶች ውስጥ ጥብቅ ደንቦችን የመጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ነው፡፡ ውድ ወጣቶች ሆይ፣ ለአካልም ሆነ ለግብረ-ገብ ይህ ለራችሁ ጥቅም ነው፡፡ ጠዋት ስትነሱ፣ በተቻላችሁ መጠን በቀኑ ሰዓታት ውስጥ ማከናወን ያለባችሁን ሥራዎች ከግምት ውስጥ አስገቡ፡፡ ከተቻለም፣ መሰራት ያላባቸው ተግባራት የሚመዘገብበት ትንሽ መጽሐፍ ይኑራችሁ፣ ሥራችሁንም የምትሰሩበትን ጊዜ መድቡ፡፡ 188 CGAmh 106.3