የልጅ አመራር
ምዕራፍ 17—ንጽሕና
እግዚአብሔር ጥንቁቅ ነው —በመካከላቸው በሚያልፍበት ጊዜ ርኩሰትን እንዳያይ ልብሶቻቸውን እንዲያጥቡና ርኩሰትን ሁሉ ከሰፈራቸው እንዲያስወግዱ ጌታ የእስራኤል ልጆችን አዘዘ፡፡ እግዚአብሔር ዛሬ በሰፈራችን እያለፈ ነው፣ እናም የቤተሰብ የንጽህና ጉድለትና ግድየለሽ ልማዶችን ይመለከታል፡፡ ሳንዘገይ የተሻለ ተኃድሶ ማድረግ የለብንምን? CGAmh 100.1
ወላጆች፣ በልጆቻችሁ አዕምሮ ውስጥ ትክክለኛ መርኾዎችን ታሳድጉ ዘንድ እግዚአብሔር ወኪል አድርጓችኋል፡፡ የጌታ ትናንሽ ልጆች አደራ አለባችሁ፣ የእስራኤል ልጆች በንጽህና ልማድ ማደግ እንዳለባቸው ያስጠነቀቃቸው እግዚአብሔር በዛሬ ቤት ውስጥም መቆሸሽን አይደግፍም፡፡ ልጆቻችሁን በዚህ መስመር የማስተማር ሥራን እግዚአብሔር ሰጥቷችኋል፣ ስለ ንጽህና ልማዶችም ልጆቻችሁን ስታስተምሯቸው፣ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እያስተማራችኋቸው ነው፡፡ በልባቸውና በአካለቸውም ጭምር ንጹህ መሆን እንዳለባቸው እግዚአብሔር እንደሚፈልግ ይመለከታሉ፣ እግዚአብሔር የወጠናቸው የንጽሕና መርኾዎችም የመላ ሕይወታቸው ተግባራት ቀስቃሽ መሆናቸውን ወደ መረዳት ይመራሉ፡፡ 174 CGAmh 100.2
እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ ከቤት ውጭ አየር ውስጥ ያሳለፉ፣ በበረኻ ሲጓዙ ከነበሩ ሰዎች ንጽህና እንዲኖራቸው ከፈለገ፣ ቆሻሻዎች ይበልጥ የሚታዩብን እና ይበልጥ ጤናማ ያልሆነ ተጽዕኖ ያለን፣ በጣሪያ በተሸፈነ ቤት ውስጥ ከምንኖር፣ ያልተናነሰ ነገር ይጠብቅብናል፡፡ 2 CGAmh 100.3
ንጽህና ሁለተኛ ፍጥረት መሆን አለበት—ቤት ቆሻሻ መሆኑ ትልቅ ስህተት ነው፣ ምክንያቱም ውጤቱ ትምህርት ሰጭ እና ከቤት ውጭም ተጽዕኖ የሚጥል ነው፡፡ በልጅነታቸውም እንኳ ለልጆች አዕምሮ እና ልማድ ትክክለኛ የሆነ ትምህርት መሰጠት አለበት….፡፡ በአካልም ሆነ በልብስ ንጹሕ አለመሆንን እግዚአብሔር እንደሚጸየፍ አሳዩአቸው፡፡ በንጽህና እንዲመገቡ ያስተምሯቸው፡፡ እነዚህ ልማዶች ለእነርሱ ሁለተኛ ተፈጥሮ ይሆኑ ዘንድ ዘወትር ንቁ መሆን ያስፈልጋል…፡፡ ቆሻሻን እንደሚገባው ይጸየፉት…፡፡ CGAmh 100.4
ኦ፣ እነዚህ ጥቃቅን ተግባራትን ችላ አለማለትን ሁሉም በተረዳ፡፡ መላው መጻኢ ሕይወታቸው በልጅነት ጊዜያቸው ልማዶችና ትግበራዎች ይቀረጻል፡፡ ልጆች በተለይም በቀላሉ የሚማረኩ ናቸው፣ እናም መመሰቃቀልን ባለመፍቀድ የንጽህና ትምህርትን ለእነርሱ መስጠት ይቻላል፡፡ 175 CGAmh 101.1
ንጽህናን እንዲወዱና ቆሻሻን እንዲጠሉ ያስተምሯቸው—ግሩም እና ጥብቅ ንጽህናን መውደድን ያሳድጉ፡፡ 176 CGAmh 101.2
ልጆችዎን ቀላል አድርገው እና ግልጽ በሆነ መልኩ ያልብሷቸው፡፡ ልብሶቻቸው ረጅም ዕድሜ ካለው ዕቃ የተሰራ ይሁን፡፡ አስደሳችና ንፁህ ያድርጓቸው፡፡ ቆሻሻና እድፍ የመሰለው ሁሉ እንዲጸየፉ ያስተምሯቸው፡፡ 177 CGAmh 101.3
ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፣ ምን እንደምትለብሱም፣ አላስፈላጊ ዕቅድ ላይ የዋለው ብርታት አሁን ገላቸውን እና ልብሳቻቸውን ንጹህ ወደ ማድረግ ይዙር፡፡ በዚህ ጉዳይ በተሳሳተ መልኩ እንዳትረዱኝ፡፡ ቤት ውስጥ ልክ እንደ አሻንጉሊት ጠብቋቸው ማለቴ አይደለም፡፡ ንጹህ አሻዋና ደረቅ መሬት ላይ ምንም ቆሻሻ የለም፤ ልብስ እንዲቀየርና ገላ እንዲታጠብ የሚያስገድድ እድፍ ከአካል የሚወጣ ነው፡፡ 178 CGAmh 101.4
አከባቢን በንጽሕና ይጠብቁ—ወላጆች ልጆች የሚሰሩትን አንድ ነገር ቢያገኙላቸው መላው ቤተሰብ ዕርዳታ ያገኛሉ፣ ይባረኩማል፡፡አገልጋዮችና መምህራን ለአካል ጤንነትና መንፈሳዊ ጥንካሬ ትልቅ ትርጉም ባለው በዚህ ርዕስ ላይ ለምን ይበልጥ ግልጽ አይሆኑም? የቤተሰቡ ወንዶችና ሴቶች የቤቱ ድርጅት አካል እንደሆኑ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ ደስተኛ የማያደርጉ ነገሮችን ሁሉ ከአካባቢያቸው ለማጽዳት መትጋት አለባቸው፡፡ በዚህ ረገድ መመሪያ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ 179 CGAmh 101.5
ማንኛውም አይነት የንጽህና ጉድለት የበሽታ አዝማሚያ አለው፡፡ ሞትን የሚያመጡ ሕዋሶች በጨለማ፣ ችላ በተባሉ ጥጎች፣ በተጣሉ ብስባቾች፣ በእርጥበት እና ሻጋታ ላይ ሞልቶ ይገኛል፡፡ ማናቸውም ቆሻሻ አትክልቶች ወይም የረገፉ ቅጠሎች ክምር ቤት አጠገብ በስብሰው አየሩን እንዲበክሉ መተው የለባቸውም፡፡ ቤት ውስጥ አንድም ንጹሕ ያልሆነና የበሰበሰ ነገርን ልትታሱት አይገባም፡፡ፍጹም ንጹህ ናቸው በሚባሉ ከተሞች የትኩሳት ወረርሽኝ የሚመጣው በአንዳንድ ግድየለሽ አባወራዎች መኖሪያ አከባቢ በሚገኙ የበሰበሱ ነገሮች ሳቢያ ነው፡፡ ፍጹም ንጽህና፣ ብዙ የፀሐይ ብርሃን፣ በእያንዳንዱ የቤት ሕይወት ውስጥ ለጽዳት ያለን ጠንቃቃ ትኩረት፣ ከበሽታ ነጻ ለመውጣት እና ለደስታ እና ቤት ውስጥ ለሚኖሩ ብርታት አስፈላጊ ናቸው፡፡ 180 CGAmh 102.1
የግል ንጽሕና ለጤንነት እጅግ አስፈላጊ ነው—ጥንቃቄ የተሞላበት ንጽሕና ለአካልና ለአዕምሮ ጤንነት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ቆሻሻ ዘወትር በቆዳ በኩል ከሰውነታችን ውስጥ ይወጣል፡፡ ዘወትር ካልታጠብን በስተቀር፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ቀዳዳዎቹ ወዲያው ስለሚደፈኑ በቆዳ ውስጥ ማለፍ ያለበት ቆሻሻ ሌሎች ቆሻሻ የሚያስወግዱ የሰውነት ክፍሎች ላይ ተጨማሪ ጫና ይሆናል፡፡ CGAmh 102.2
አብዛኞቹ ሰዎች በየዕለቱ ጧትና ማታ በቀዝቀዛ ወይም ለብ ባለ ውሃ በመታጠብ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ተገቢ በሆነ ሁኔታ መታጠብ ለብርድ ከማገለጥ በተቃራኒ የደም ዝውውርን ስለሚያሻሽል ብርድን ይከላከላል፤ ደም ወደ ላይኛው የቆዳ ገጽታ ስለሚወሰድ ይበልጥ ቀላልና የተስተካከለ ፍሰት ይገኛል፡፡ አዕምሮና አካልም እንዲሁ ብርታትን ያገኛል፡፡ ጡንቻዎች ይበልጥ እጥፍ ዘርጌ ይሆናሉ፣ አዕምሮም ብሩህ ይሆናል፡፡ ገላን መታጠብ ጅማቶችን ያረጋጋል፡፡ ገላን መታጠብ አንጀቶችን፣ ጨጓራን፣ እና ጉበትን በመርዳት ለእያንዳንዳቸው ጤናና ጉልበትን በመስጠት የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል፡፡ CGAmh 102.3
አልባሳት ንጹሕ መሆናቸውም አስፈላጊ ነው፡፡ የምንለብሳቸው አልባሳት በቆዳችን ቀዳዳዎች የሚወገዱ ቆሻሻዎችን ይመጥጣሉ፤ ዘወትር የማንቀይራቸውና የልታጠቡ እንደሆነ፣ ቆሻሻዎቹ እንደገና በቆዳችን ቀዳዳዎች ይመጠጣሉ፡፡ 181 CGAmh 103.1
ንጹሕ አከባቢዎች ለንጽሕና አጋዦች ናቸው—ብዙ ጊዜ ከልጆች አልጋ ላይ የሚነሳ ቆሻሻ፣ መርዛማ ጠረን ለእኔ ዘወትር ልታገሰው የማልችለው ሆኖ አይቻለሁ፡፡ የልጆች አይኖች የሚያርፉባቸውን እና ማታ ወይም ጥዋት ከገላቸው ጋር ንክኪ ያላቸው ነገሮች በሙሉ ንጹሕና ጤናማ ተደርገው ይጠበቁ፡፡ ይህ ንጹሕና እና ጥርት ያለ ነገር እንዲመርጡ አንዱ የማስተማሪያ ዘዴ ነው፡፡ የልጆቻችሁ መኝታ ክፍል ወድ የቤተ ዕቃዎች ባይኖሩትም እንኳ ንጹሕ ይሁን፡፡ 182 CGAmh 103.2
ተገቢ የሆነ ሚዛን መጠበቅ—ንጽሕናና ሥርዓታዊነት የክርስቲያን ተግባራት ናቸው፣ ነገር ግን ሌሎች የላቀ አስፈላጊነት ያላቸው ጉዳዮች ችላ ተብለው እነዚህ ከሚገባቸው መጠን በላይ ሊታዩና ዋናው ጉዳይ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ለእነዚህ ግምት በመስጠት የልጆችን ፍላጎቶች ወደ ጎን የሚተው፣ የሕጉን ዋናኛውን ነገር— ፍትሕ፣ ምህረት እና የእግዚአብሔርን ፍቅር ወደ ጎን ትተው ከአዝሙድና ከካሙን አሥራት እየከፈሉ ናቸው፡፡ 11 CGAmh 103.3