የልጅ አመራር
ምዕራፍ 19—ንጽሕና
ስለ ንጽሕና መርኾዎች መመሪያ ይስጡ—ክርስቲያን እናቶች፣ ያረፈባችሁን ኃላፊነት ለመረዳት በአንዲት እናት ተለመኑ፡፡ ልጆቻችሁን ከጨቅላነታቸው ጀምራችሁ ራስን መካድን እና ራስን መቆጣጠርን አስተምሯቸው፡፡ ጤናማ ተክለ-ሰውነትና ጥሩ ግብረ-ገብ እንዲኖራቸው አድረጋችሁ አሳድጓቸው፡፡ የእግዚአብሔር ዕቅድ ለጊዜያዊ እርካታ እንድንኖር ሳይሆን፣ ነገር ግን ለፍጻሜው ጥቅማችን እንደሆነ በለጋ አዕምሮአቸው ላይ ያስርጹ፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ለም መሬት ላይ እንደ ተዘራ ዘር ይሆናሉ፣ ልቦቻችሁንም ደስ የሚያሰኙ ፍሬዎችን ያፈራሉ፡፡ 189 CGAmh 106.4
ወላጆች ልጆቻቸውን ከበካይ ተጽዕኖዎች ለመከለል፣ የንጽሕና መርኾዎችን ማስተማር አለባቸው፡፡ ቤት ውስጥ የታዛዥነትና ራስን የመቆጣጠርን ልማዶችን የሚቀርጹ ልጆች በትምህርት ቤት ሕይወታቸው ውስጥ ጥቂት ችግር የሚገጥማቸው እና ወጣቶችን ዘወትር ከሚያስቸግሯቸው አያሌ ፈተናዎችም የሚያመልጡ ይሆናሉ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው በማናቸውም ሁኔታዎች ውስጥ እና በማናቸውም ሥፍራዎች ለእግዚአብሔር ታማኞች እንዲሆኑ ማሰልጠን አለባቸው፡፡ ባህሪያቸውን የማጎልበት አዝማሚያ ባላቸው ተጽዕኖዎች እንዲከበቡ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከእንደዚህ አይነቱ ስልጠና ጋር ወደ ትምህርት ቤት የሚላኩ ልጆች የረብሻ ወይም የስጋት ሰበብ አይሆኑም፡፡ ለመምህራኖቻቸው ድጋፍ እና ለተማሪ ጓደኞቻቸው ምሳሌና ማደፋፈሪያ ይሆናሉ፡፡ 190 CGAmh 107.1
የማያቋርጥ ንቁነትን መለማመድ አለባቸው—ወላጆችና አሳዳጊዎች ልጆቻቸው ንፁህ እንዲሆኑ የሚሹ እንደሆነ፣ ራሳቸውም የልብና የሕይወት ንጽህናቸውን መጠበቅ አለባቸው፡፡ ተገቢውን መመሪያ መስጠት አለባቸው፣ ከዚህም በተጨማሪም የማያቋርጥ ንቁነትን መለማመድ አለባቸው፡፡ በእያንዳንዱ ቀን በወጣቶች አዕምሮ ውስጥ አዳዲስ ሐሳቦች ይነሳሉ፣ አዳዲስ ግምቶች በልቦቻቸው ውስጥ ይፈጠራሉ፡፡ እነርሱ የሚመሰርቸው ጓደኝነቶች፣ የሚያነቧቸው መጽሐፎች፣ የሚወዷቸው ልማዶች—ሁሉም ጥንቃቄ ያሻቸዋል፡፡ 191 CGAmh 107.2
ቤትን ንጹሕና ማራኪ አድረገው ይያዙ—ቤት ንጹሕና ጽዱ ሆኖ መያዝ አለበት፡፡ ቤት ውስጥ ያልጸዱ፣ ችላ የተባሉ ጥጎች ነፍስ ያልነጻና ችላ የተባለ የማድረግ ዝንባሌ አላቸው፡፡ እናቶች፣ እናንተ የልጆቻችሁ አስተማሪዎች ናችሁ፣ ክፍሎቻቸውን ጽዱ፣ ያማረና ማራኪ በማድረግ ንጹህ አስተሳሰብን ገና በጊዜ ማስረጽ ከጀመራችሁ እጅግ ትልቅ ሥራ መስራት ትችላላችሁ፡፡ 192 CGAmh 107.3
ጓደኝነትን በጥንቃቄ መከታተል— ወላጆች ልጆቻቸው ንጹህ እንዲሆኑ የሚመኙ ከሆነ፣ እግዚአብሔር በሚያጸድቀው አይነት ንጹህ ጓደኝነት ዙሪያቸውን መክበብ አለባቸው፡፡ 193 CGAmh 108.1
ወላጆች ልጆቻቸውን በምን ያህል ጥንቃቄ ከግድየለሽነት፣ ልልነት፣ ግብረ-ገብን ከሚያበለሹ ልማዶች መጠበቅ ይኖርባቸው ይሆን! አባቶችና እናቶች፣ በእናንተ ላይ ያረፈውን የኃላፊት አስፈላጊነት ትረዳላችሁን? ልጆቻችሁ ምን አይነት ትምህርት እየተቀበሉ እንዳሉ ለማወቅ በሥፍራው ሳትገኙ ከሌሎች ልጆች ጋር ጓደኝነት እንዲፈጥሩ ትፈቅዳላችሁን? ከሌሎች ልጆች ጋር ብቻቸውን እንዲሆኑ አትፍቀዱላቸው፡፡ ልዩ እንክብካቤአችሁን ስጡአቸው፡፡ በየምሽቱ የት እንዳሉና ምን እያደረጉ እንዳለ እወቁ፡፡ በልማዶቻቸው ሁሉ ንጹህ ናቸው? እነርሱን በግብረ-ገብ ንፅህና መርኾ ረገድ አስተምራችኋልን? እነርሱን ሥርዓት በሥርዓት፣ ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ጥቂት ከዚህ ጥቂት ከዚያ ማስተማርን ችላ ያሉ እንደሆነ፣ ይህን ከመሥራት ችላ ማለትዎን ንስሃ ሳይገቡ ሌላ ቀን አይለፍ፡፡ ስለዚህ አሁን እንዲሰሩ እግዚአብሔር የሾሞትን ሥራ እየሠሩ እንዳሉ ይንገሯቸው፡፡ በተሃድሶ ውስጥ ከእርሶ ጋር እንዲቆሙ ይጠይቋቸው፡፡ 6 CGAmh 108.2
ጎረቤቶች ልጆቻቸው ከልጆችዎ ጋር ወደ ቤትዎ መጥተው ምሽቱንና ሌሊቱን ከልጆችዎ ጋር እንዲያሰልፉ ሊፈቅዱ ይችላሉ፡፡ ልጆቻቸውን ወደ ቤታቸው በመላክ ጎረቤቶችዎን የማስከፋት አዳጋ መቀበል፣ ወይም እነርሱን በማስደሰት፣ ልጆቻቸው ከልጆችዎ ጋር እንዲያድሩ በመፍቀድ፣ ዕድሜ ልካቸውን እርግማን የሚሆንባቸውን እውቀት ለመቅሰም ተጋላጭ ማድረግ፣ እዚህ ጋር ለእርሶ ፈተናና ምርጫ ነው፡፡ ልጆቼን ከመበላሸት ለማደን፣ ከሌሎች ወንዶች ልጆች ጋር አንድ አልጋ ላይ ወይም አንድ ክፍል እንዲተኙ ፈቅጄ አላውቅም፣ እናም በምጓዝበት ጊዜ፣ እንደ ወቅቱ አስፈላጊነት፣ ከሌሎች ልጆች ጋር ከሚያድሩ ይልቅ ወለል ላይ ትንሽ አልጋ አሰራላቸው ነበር፡፡ ሥርዓት አልባና ባለጌ ከሆኑ ወንዶች ልጆች ጓደኝነት እንዲጠበቁ እና ተግባራቸውን ቤት ውስጥ ደስተኛ በመሆን እንዲያከናውኑ የሚያደፋፍሩ ነገሮችን ለማቅረብ ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ አዕምሮዎቻቸውን እና እጆቻቸውን በሥራ የተያዙ በማድረግ፣ ጎዳና ላይ ከሌሎች ወንዶች ልጆች ጋር መጨወት እና የጎዳናን ትምህርት ለማግኘት ጥቂት ጊዜ ወይም ፍላጎት ብቻ ነበራቸው፡፡ 194 CGAmh 108.3
በስሜታዊነት ላይ ገደብ ያብጁ—በአምሳሉ በተሰሩት የልጆች ነፍሳት እና አካሎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ንብረት ተጠያቂነት ያላቸው ሰዎች በሺዎች የሚቆጠሩትን አካላዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጤንነትን የሚያበላሸው የዘመኑ ልቅ ፍላጎት ላይ ገደብ ማበጀት አለባቸው። ብዙ የዚህ ዘመን ወንጀሎች የእውነተኛ ምክንያቶቻቸው ዱካ ከተፈለገ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ግድየለሾች የሆኑ አባቶች እና እናቶች አላዋቂነት ተጠያቂ ሆኖ ይታያል። ጤና እና ሕይወት እራሱ ለዚህ አሳዛኝ አላዋቂነት መስዋእትነት እየሰጡ ናቸው፡፡ CGAmh 109.1
ወላጆች፣ እግዚአብሔር የእነንተ ኃላፊነት አድረጎ የሰጣችሁን ለልጆቻችሁ ትምህርት መስጠት ካልቻላችሁ፣ ለውጤቱ ለእርሱ መልስ መስጠት አለባችሁ፡፡ እነዚህ ውጤቶች በልጆችዎ ብቻ አይወሰኑም፡፡ አንደኛው እሾህ በሜዳ ውስጥ እንዲያድግ የተፈቀደለት ፍሬ እንደሚያፈራ ሁሉ፣ በቸልታዎ ምክንያት የሚደረጉት ኃጥአቶች ተጽዕኖዎ ክልል ውስጥ ያሉትን ሁሉ ያበላሻል። 195 CGAmh 109.2
አእምሮን በንጹሕ ምስሎች ይሙሉ—የክርስትና ሕይወት የማያቋርጥ ራስን የመግዛት እና ራስን የመቆጣጠር ሕይወት ነው። ልጆች ከሕፃንነታቸው ጀምሮ ሊማሯቸው የሚገባቸው ትምህርቶች እነዚህ ናቸው፡፡ መሻትን መግዛትን፣ በአስተሳሰብ እና በልባቸው እና በድርጊታቸው ንፁህ መሆን እንዳለባቸው፣ የእግዚአብሔር መሆናቸውን ያስተምሯቸው፣ ምክንያቱም በዋጋ ተገዝተዋል፣ ይኸውም በውድ በሆነ በተወዳጁ የልጁ ደም፡፡ 196 CGAmh 109.3
በልጅነት ዕድሜያቸው የልጆች አዕምሮ አስደሳች በሆኑ የእውነት ምስሎች፣ በንጽህና እና በመልካም ምስሎች ተሞልተው ከሆነ ፣ ለንጹህ እና ከፍ ላለው ነገር ልምድ ይመሰረታል፣ አስተሳሰባቸውም በቀላሉ የማይበላሽ ወይም የማይረክስ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተቃራኒውን አካሄድ መከተል ካለ፣ የወላጆች አእምሮ ያለማቋረጥ በዝቅተኛ ትዕይንቶች ላይ ጊዜን የሚያሳልፍ ከሆነ፣ ጭውውታቸው በማያስደስት የባህሪይ ሁኔታዎች ላይ ጊዜን የሚያሳልፍ ከሆነ፣ ሌሎች የሚከተሉትን መንገድ በመቃወም የመናገር ልማድ ካደበሩ፣ ትንንሾቹ ልጆች ከአፀያፊ ቃላቶች እና አገላለጾች በመውሰድ ውጤቱ ጎጂ የሆነውን ምሳሌ ይከተላሉ፡፡ እርኩሱ አሻራ ልክ እንደ ቁምጥና፣ በመጻኢ ሕይወታቸውም ከእነርሱ ጋር የተጣበቀ ይሆናል፡፡ CGAmh 110.1
በጥንቁቅና ፈርሃ-እግዚአብሔር ባለት እናት በጨቅላነት የተዘራው ዘር የሚያብብ እና ፍሬ የሚያፈራ የጽድቅ ዛፎች ይሆናሉ፤ እናም ፈርሀ-እግዚአብሔር ባለው አባት መመሪያ በመስጠት እና በምሳሌ የተስተማረ ትምህርት፣ ልክ በዮሴፍ ሕይወት እንደ ሆነው ሁሉ፣ ዘወትር ብዙ ፍሬ ያፈራል፡፡ 10 CGAmh 110.2