የልጅ አመራር
ምዕራፍ 16—የጤና መርኾዎች
የጤናን ትምህርት ገና ከልጅነታቸው ይጀምሩ—ሰውን የፈጠረው የአካላችንን ሕያው ማሽን አደራጅቷል፡፡ እያንዳንዱ አሠራር በአስደናቂ ሁኔታና በጥበብ ነው የተሰራው፡፡ ሰብአዊ ወኪል ሕግጋቱን የሚጠብቅና ከእግዚአብሔር ጋር የሚተባበር ከሆነ፣ የዚህን ማሽን ጤናኛ አሰራር ለመጠበቅ እግዚአብሔር ቃል ገብቷል…፡፡ የእግዚአብሔርን ሥራ በተፈጥሮ ውስጥ በመመልከት ማድነቅ እንችላለን፣ ነገር ግን የሰብአዊው አካል ግን እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ CGAmh 97.1
ገና ምክንያታዊነት ሲጀምር፣ ከአካል መዋቅር ጋር በተያያዘ የሰዎች አዕምሮ ዕውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ እዚህ ጋር ሰው በእርሱ አምሳል ስለ ተፈጠረ ያሕዌ የራሱን ናሙና ሰጥቷል፡፡ 169 CGAmh 97.2
የወጣቶች የመጀመሪያ ጥናት ራሳቸውን ማወቅ እና አካሎቻቸውን እንዴት በጤንነት መጠበቅ እንዳለባቸው መሆን አለበት፡፡ 170 CGAmh 97.3
በቅድሚያ አስፈላጊ የሆነ ትምህርት—በልጆች የመጀመሪያ ትምህርት ላይ አያሌ ወላጆች እና መምህራን የአካልና የአዕምሮ ጤንነትን ለመጠበቅ የአካል አደረጃጀት ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት መረዳት ያቅታቸዋል፡፡ 3 CGAmh 97.4
የቤተሰብዎ መጻኢ ደስታና የማህረተሰብዎ ደህንነት በእጅጉ የሚወሰነው ልጆችዎ በልጅነታቸው ዕድሜ ላይ በሚቀበሉት የአካልና የግብረ-ገብ ትምህርት ላይ ነው፡፡ 171 CGAmh 97.5
ወላጆች የስነ-አካል ጥናትን መረዳትና ማስተማር አለባቸው—ወላጆች ራሳቸው ዕውቀት ቢያገኙ እና ውድ ልጆቻቸውን በማስተማር ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ቢሰማቸው ኖሮ፣ በወጣቶችና በልጆች መካከል የተለየ ሁኔታን ማየት በቻልን ነበር፡፡ ልጆች ከአካሎቻቸው ጋር በያያዘ ትምህርት ማግኘት አለባቸው፡፡ ስለ ሰብዓዊ ሕይወት ምስጢር ትክክለኛ ዕውቀት ያላቸው ጥቂት ወጣቶች ናቸው፡፡ ስለ ሕያው ማሺን የሚያውቁት ጥቂት ነው፡፡ ዳዊት እንዲህ ይላል፣ “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፡፡” CGAmh 97.6
ልጆች ከመንስኤ እስከ ውጤት ድረስ ያለውን ማጥናት እንደለባቸው አስተምሯቸው፤ የአካላቸውን ሕግጋት ሲተላለፉ፣ ቅጣቱን በበሽታ በመሰቃየት መክፈል እንዳለባቸው አሳዩአቸው፡፡ በጥረትዎ ውስጥ የተለየ መሻሻል ባያዩ፣ ተስፋ አይቁረጡ፤ በትዕግስት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ጥቂት ከዚህ ጥቂት ከዚያ በማድረግ ያስተምሯቸው…፡፡ ድል እስኪገኝ ድረስ ይግፉበት፡፡ ልጆችዎን ስለ አካሎቻቸው እና እነርሱም እንዴት መንከባከብ እንዳለባቸው ማስተማርን ይቀጥሉበት፡፡ 172 CGAmh 98.1
ጤናማ አኗኗር የቤተሰብ ጉዳይ ሊሆን ይገባል—ጤናማ አኗኗር የቤተሰብ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ ወላጆች እግዚአብሔር ለሰጣቸው ኃላፊነቶች መንቃት አለባቸው፡፡ የጤና ተኃድሶ መርኾዎችን ያጥኑና ልጆቻቸውን የራስ-ክህደት ጎዳና ብቻ የደህንነት ጎዳና እንደሆነ ያስተምሯቸው፡፡ በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ብዙዎቹ የአካልን ሕግ ችላ በማለት ራስን የመቆጣጠር ኃይላቸውን ያወድሙና ዘላለማዊ ጋሃዶችን ለማድነቅ ራሳቸውን የማይበቁ ያደርጋሉ፡፡ ስለ አካላቸው አወቃቀር በፈቃደኝነት ችላ በማለት፣ ልጆቻቸውን በራስ ማሞላቀቅ ጎዳና ይመሯቸዋል፣ በእንደዚይ አይነት ሁናቴም የተፈጥሮ ሕግጋትን በመተላለፍ ለሚመጣው ቅጣት የስቃይን መንገድ ለራሳቸው ያዘጋጃሉ፡፡ 6 CGAmh 98.2
የአካል ብቃት ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል—የአካል ብቃት ስልጠና፣ የአካል ዕድገት፣ ከመንፈሳዊ ስልጠና ይልቅ እጅግ በቃላሉ ይሰጣል፡፡ የሕጻናት እንክብካቤ ሥፍራ፣ የመጫወቻ ሥፍራ፣ ቤተ ሙከራ፤ ዘር መዝራት፣ መኸርን መሰብሰብ— እነዚህ በሙሉ የአካል ብቃት ሥልጠና ይሰጣሉ፡፡ በተለመዱ ምቹ ሁኔታዎች ውስጥ አንድ ልጅ በተለምዶ ጤናማ ጥንካሬና የአካል ክፍሎችን ተገቢ ዕድገት ያገኛል፡፡ ነገር ግን በአካል ብቃት አንጻርም ቢሆን ልጅ በጥንቃቄ መሰልጠን ይኖርበታል፡፡ 173 CGAmh 98.3
ለተፈጥሮ ሕግጋት መታዘዝ ጤንነትና ደስታን ያመጣል—ልጆቻችን ስለ አካላቸው ዕውቀት እንዲኖራቸው መማር ይገባቸዋል፡፡ ከሕመምና ከበሽታ ነጻ እንዲሆኑ በሕጻንነታቸው ጊዜ በትዕግስት እነርሱን በማስተማር የአካለቸውን ሕግጋት መታዘዝን እንዲረዱ ማድረግ ይቻላል፡፡ በበሽታ የተጎዱ እንደሆነ ሕይወታቸው ጠቀሜታ እንደማይኖረው መረዳት አለባቸው፡፡ የተፈጥሮ ሕግጋትን ችላ በማለት ሕመምን በራሳቸው ላይ ያመጡ እንደሆነ እግዚአብሔርንም ማስደሰት አይችሉም፡፡ 8 CGAmh 99.1