የልጅ አመራር

14/85

ምዕራፍ 12—መታዘዝ ልማድ መሆን አለበት

በእርጋታ ነገር ግን በጽኑ ጥረት ልጆች ችሎታዎቻቸው ለእግዚአብሔር ክብር ይሆን ዘንድ እንደተሰጣቸው ሊማሩ ይገባል፡፡ ይህን ዓላማ ለማሳካት የታዛዥነትን ትምህርት መማር አለባቸው፡፡… በእርጋታና ጽኑ ጥረት ልማድ መመስረት አለበት፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ በሆነ መጠን የኋላ ኋላ የሚመጡ በወጣቶች አዕምሮ ውስጥ የሚነሳሱ ወላጆችና መምህራንን ባይተዋር የማድረግና ምሬት፣ አብዛኛውን ጊዜ ባለ ሥልጣናት ላይ፣ ሰዎች ላይ እና መለኮት ላይ የሚነሱ ተቃውሞዎችን አስቀድሞ መከላከል ይቻላል፡፡ 130 CGAmh 81.1

ክርክርና ማጭበርበርን አትፈቀዱ—ወላጆች ማድረግ የሚገባቸው የመጀመሪያው ጥንቃቄ መልካም አስተዳደርን በቤተሰብ ውስጥ ማቋቋም ነው፡፡ የወላጆች ቃል ክርክርና ማጭበርበርን የሚከላከል ሕግ መሆን አለበት፡፡ ልጆች ከልጅነታቸው ጀምረው ሳያወላውሉ ወላጆቻቸውን መታዘዝን መማር አለባቸው፡፡ 131 CGAmh 81.2

ጥብቅ ሥርዓታዊነት በአንድ ወቅት አለመርካትን ሊያስከትል ይችላል፣ ልጆችም የራሶቻቸውን መንገድ ይመርጣሉ፤ ነገር ግን ለወላጆቻቸው የመታዘዝን ትምህርት ሲማሩ፣ ለእግዚአብሔር መጠይቆች ለመገዛት በተሻለ ሁኔታ ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ በዚህ አይነት ሁኔታ በልጅነት ጊዜ የተቀበሉት ሥልጠና የኃይማኖት ልምምድ ላይ ተጽዕኖ በመጣል፣ የሰውየውን በህሪይ ይቀርጻል፡፡ 132 CGAmh 81.3

ልዩ ሁኔታዎችን ፈቃድ አያግኙ— ወላጆች እንደ ቤተሰባቸው መምህር ሕገ ደንቦች እንዳይተላለፉ ማየት አለባቸው፡፡… ልጆቻቸው ባለመታዘዝ እንዲቀጥሉ በመፍቀድ፣ ተገቢውን ሥነ-ሥርዓታዊነትን መለማመድ ያቅታቸዋል፡፡ ልጆች ወደ መገዛትና ታዛዥነት መምጣት አለባቸው፡፡ አለመታዘዝ ፍቃድ ማግኘት የለበትም፡፡ የልጆቻቸውን አለመታዘዝ በሚፈቅዱ ወላጆች በር ላይ ኃጢአት ታደባለች፡፡… ልጆች መታዘዝ እንዳለባቸው መረዳት አለባቸው፡፡ 133 CGAmh 81.4

ቅጽበታዊና ፍጹም ታዛዥነትን መስፈርት ያድርጉ—ወላጆች ቅጽበታዊና ፍጹም ታዛዥነትን ከልጆቻቸው እንደ መስፈርት ማስቀመጥ ሲያቅታቸው፣ በትናንሽ ልጆቻቸው ላይ ትክክለኛውን የባህሪይ መሠረት መጣል ያዳግታቸዋል፡፡ ባረጁ ጊዜ እንዳያከብሯቸው ልጆቻቸው ያዘጋጃሉ፣ ወደ መቃብርም ሲቃረቡ ልቦቻቸው ላይ ሐዘንን ያመጣሉ፡፡ 134 CGAmh 82.1

መስፈርቶቹ ምክንያታዊ መሆን አለባቸው—የወላጆች መስፈርቶች ሁልጊዜ ምክንያታዊ መሆን አለባቸው፤ በሞኝነት ማሞላቀቅ ሳይሆን፣ ነገር ግን ጥበብ በተሞላበት መንገድ ርህራሄ መገለጽ አለበት፡፡ ወላጆች ከጥላቻና ስህተት ፈላጊነት በጸዳ ሁኔታ፣ የልጆቻችሁን ልቦች በፍቅር የሀር ገመድ ከራሳቸው ጋር ለማስተሳሰር በመሻት፣ ልጆቻቸውን በደስታ ማስተማር አለባቸው፡፡ አባቶች እና እናቶች፣ መምህራን፣ ታላላቅ ወንድሞች አና እህቶች፣ ሁላቸውም ሕጻናት ልጆች በእንክብካቤ እና በጌታ ግሳጼ ያድጉ ዘንድ እንዲረዳቸው፣ እና በቤትና ትምህርት ቤት ሕይወት ሁለንተናዊ ሁናቴን ለማምጣት፣ እያንዳንዱን መንፈሳዊ ፍላጎት በማበርታት አስተማሪ ኃይል ይሁኑ፡፡ 135 CGAmh 82.2

ልጆቻችንን ስናሰለጥን፣ እና የሌሎች ሰዎች ልጆችን ስናሰለጥን፣ ወላጆችና አሳዳጊዎች ከክፋት ስለሚያግዷቸው የልጆች ፍቅር እንደማይቀንስ አረጋግጠናል፡፡ 7 CGAmh 82.3

የታዛዥነት ምክንያቶች ሊነገራቸው ይገባል—ልጆች በቤተሰባቸው መንግስት ውስጥ ታዛዥነትን መማር አለባቸው፡፡ በቤት ሕይወት ውስጥ ሕግን በመጠበቅ፣ እግዚአብሔር በሚያጸድቀውን ሚዛናዊ ባህሪይ መቀረጽ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸው የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲታዘዙ ማስተማር አለባቸው፡፡…ምን ማድረግ እንዳለባቸው እና ምን ምን ከማድረግ መታቀብ እንዳለባቸው ያውቁ ዘንድ፣ የርሱን ተፈጥሮውን መረዳት በሚጀምሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ሕግ የመታዘዝ እና የማክበር ምክንያት ልጆች ውስጥ መስረጽ አለበት፡፡ 136 CGAmh 82.4

የወላጆች ቃል ሕግ መሆን አለበት—በቁጥጥራችሁ ሥር ያሉ ልጆቻችሁ፣ ሊያስብዎት ይገባል፡፡ ቃልዎ ሕጋቸው መሆን አለበት፡፡ 137 CGAmh 82.5

አያሌ የክርስቲያን ወላጆች ልጆቻቸውን በራሳቸው መንገድ መምራት ያዳግታቸዋል፣ ከዚያም በኋላ ልጆቻቸው ጠማማ፣ የማይታዘዙ፣ አመስጋኞች ያልሆኑ፣ እና ቅዱሳን ያልሆኑ ሲሆኑባቸው ይደንቃቸዋል፡፡ እንደ እነዚህ ያሉ ወላጆች በእግዚአብሔር ግሳጼ ሥር ናቸው፡፡ ልጆቻቸውን በጥንቃቄ እና በጌታ ግሳጼ ማሳደግን ችላ ብለው ነበር፡፡ የክርስትና የመጀመሪያ ትምህርትን እነርሱን ማስተማር አልቻሉም፡ ይህም፡- “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡” “ስንፍና” ይላል ጠቢቡ ሰው፣ “በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፡፡” ከንቱነትን ማፍቀር፣ ክፉ ለማድረግ መመኘት፣ ለቅዱስ ነገሮች ያለ ጥላቻ ወላጆችን በቤት የተልዕኮ ሜዳ የሚገጥሟቸው ችግሮች ናቸው…፡፡ CGAmh 82.6

ወላጆች በእግዚአብሔር ብርታት በመነሳት ቤተሰባቸውን በራሳቸው መንገድ እንዲመሩ ማዘዝ አለባቸው፡፡ ስህተትን በጽኑዕ እጅ መታገድ አለበት፣ ሆኖም ግን በትዕግስት ማጣት ወይም በስሜት መሆን የለበትም፡፡ ልጆቻቸው ስለ ትክክለኛ ነገር ግምታዊ እንዲሆኑ መተው የለባቸውም፣ ነገር ግን በማይሳሳት ቃላት ሊጠቁሟቸው እና በዚያም መንገድ እንዲጓዙ ማስተማር ይገባቸዋል፡፡ 138 CGAmh 82.7

ታዛዥ ያልሆን ልጅ ተጽዕኖ—አንድ ታዛዥ ያልሆነ ልጅ ጓደኞቹ ላይ ትልቅ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፣ ምክንያቱም በራሱ ምሳሌ ሌሎችን ስለሚቀርጽ ነው፡፡ 139 CGAmh 82.8

ኃጢአትን ቀለል አድርጎ ማየት—ልጆቻችሁ እንዲያከብሯችሁ አስተምሯቸው፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሕግ ይህንን ኃላፊነት በልጆቻችሁ ላይ ይጥላል፡፡ ልጆቻችሁ ለመሻታችሁ ቀላል አክብሮት እንዲሰጡ ብትፈቅዱላቸው እና ለቤተሰቡ ሕግጋት ምንም አክብሮት ባይኖራቸው፣ ኃጢአትን ቀለል አደርጋችሁ እያያችሁ ነው፤ ሰይጣን እንደፈለገው እንዲሰራ ፈቃድ እየሰጡት ነው፤ ይህ አለመታዘዝ፣ አክብሮትን መፈለግ እና ራስን መውደድ እስከ የኃይማኖት ሕይወታቸው ድረስ እስከ ቤተ ክርስቲያንም ድረስ ከእነርሱ ጋር ይጓዛል፡፡ የዚህ ክፋት ሁሉ ጅምር በሰማይ መዝገብ ላይ በወላጆች ችላ ባይነት ላይ ይጣላል፡፡ 140 CGAmh 83.1

የታዛዥነት ልማድ በድግግሞሽ ይጸናል፡፡—የታዛዥነት፣ ሥልጣንን የማክበር ትምህርት ብዙ ጊዜ መደጋገም ይኖርበታል፡፡ እንዲህ አይነቱ ተግባር በቤተሰብ ውስጥ ለመልካም የሚሆን ኃይል ይኖረዋል፣ እናም ከክፋት የሚታቀቡት እና እውነት እና ጽድቅን ለመውደድ የሚገደዱት ልጆች ብቻ ሳይሆኑ፣ ወላጆችም እኩል ተጣቀሚዎች ይሆናሉ፡፡ በእርሱ ምሪት እነርሱን ይመሯቸው ዘንድ፣ ጌታ የሚፈልገው እንዲህ አይነቱ ሥራ በእነርሱ በኩል ያለ ጥብቅ ማሰላሰል፣ የእግዚአብሔርን ቃል አብዝተው ባለማጥናት የሚሆን አይደለም፡፡ 13 CGAmh 83.2