የልጅ አመራር

13/85

ምዕራፍ 11mdash;ከሕጻንነት ጀምሮ መማር

ማስተማርን ከልጅነት ይጀምሩ —ለወላጆች ሥልጣን መታዘዝን በሕጻንነት ማስረጽ እና በወጣነት ማሳደግ ተገቢ ነው፡፡ 122 CGAmh 78.1

አንዳንድ ወላጆች ትናንሽ ልጆቻቸው የራሶቻቸውን መንገድ መከተል ይችላሉ ፣ ካደጉም በኋላ እንወቅሳቸዋለን ብለው ያስባሉ፣ ነገር ግን ይህ ስህተት ነው፡፡ ታዛዥነትን በሕጻንነት ሕይወት ማስተማርን ጀምር፡፡… በቤት ትምህርታችሁ ቤት ውስጥ ታዛዥነትን እሹ፡፡ 123 CGAmh 78.2

ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ ወላጆቻቸውን መታዘዝን፣ ቃላቸውን ማክበርን፣ እና ሥልጣናቸውን ማክበርን መማር አለባቸው፡፡ 124 CGAmh 78.3

የማሰብ ችሎታ ከማደጉ በፊት—ልጅ መማር ያለበት የመጀመሪያው ትምህርት የታዛዥነት ትምህርት ነው፡፡ የማሰብ ችሎታው ከማደጉ በፊት ታዛዝነትን መማር አለበት፡፡ 125 CGAmh 78.4

የእናቶች ሥራ ሕጻኑ በጨቅላ ዕድሜ ሳለ መጀመር አለበት፡፡ ፍቃዱንና ስሜቱን ማስገዛት እና ጸባዩን በቁጥጥር ሥር ማድረግ አለባት፡፡ ታዛዝነትን አስተመሪው፣ ሕጻኑም እያደገ ሲሄድ፣ እጅሽን ከእርሱ አትመልሺ፡፡ 126 CGAmh 78.5

የራስ ፍቃድ ከመጎልበቱ በፊት—ታዛዥነትን ገና በጊዜው ልጆችን ማስተማር የሚጀምሩ ጥቂት ወላጆች ናቸው፡፡ በተለምዶ ልጅ ታዛዥነትን ለመማር ገና ልጅ ነው በሚል እሳቤ ወላጆች ልጅን ሥርዓት ማስተማር በመተው ሁለት ወይም ሦስት ዓመት እስኪሞላው ድረስ ይጠበቃል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ ጊዜያት በሙሉ ራስ ወዳድነት በሕጻኑ ውስጥ እየጎለበተ ይሄዳል፣ እናም ወላጆች በየዕለቱ ልጁን ለመቆጣጠር ከባድ ሥራ ይሆንባቸዋል፡፡ CGAmh 78.6

ሕፃናት በልጅነታቸው ዕድሜ በግልጽና በቃላሉ የተነገራቸውን ነገሮች መረዳት ይችላሉ፣ እናም፣ በርህራሄና ሕጋዊ አያያዝ፣ ታዛዥነትን ሊማሩ ይችላሉ፡፡… ልጇ ለቅጽበትም እንኳ የአሸናፊነት አጋጠሚ እንዲያገኝባት እናት መፍቀድ የለባትም፣ ይህን ሥልጣን ዘላቂ ለማድረግም፣ መጥፎ እርምጃ መወሰድ የለበትም፤ ጽኑ፣ ጥብቅ እጅ እና ልጁን ስለ መውደድሽ ሊያሰምነው የሚችል ርህራሄ ዓለማውን ተፈጻሚ ያደርጋዋል፡፡ ነገር ግን ራስ ወዳድነት፣ ቁጣ፣ የራስ ፈቃድ በልጁ ሕይወት የመጀመሪያ ሦስት ዓመታት ውስጥ ሥራቸውን እንዲሰሩ ይፍቀዱና ከዚያም ለሁለንተናዊ ሥነ-ሥርዓት እርሱን ማስገዛት ከባድ ይሆናል፡፡ ጸባዩ ተበላሽቷል፤ የራሱን መንገድ በመያዙ ደስተኛ ይሆናል፤ የቤተሰብ ቁጥጥር ለእርሱ አስደሳች አይሆንም፡፡ እነዚህ ክፉ ዝንባሌዎች ልጁ ሲያድግ ከእርሱ ጋር ያድግና ለአካለ-መጠን ሲደርስ የገነነው ራስ ወዳድነት እና ራስን መቆጣጠር አለመቻል በምድራችን አመጽን የሚያስፋፋ ክፋት ሥር ይጥለዋል፡፡ 127 CGAmh 79.1

እነርሱ [ልጆች] በፍጹም ለወላጆቻቸው አክብሮት ማጉደልን ማሳየት የለባቸውም፡፡ የራስ ፈቃድ ሳይገሰጽ መታለፍ የለበትም፡፡ የልጁ መጻኢ ደህንነት ርህራሄ፣ ፍቅር ቢፈልግም፣ ጽኑ ሥነ-ሥርዓታዊነት ግን ያስፈልጋል፡፡ 128 CGAmh 79.2

ለወላጆች መታዘዝ ለእግዚአብሔር ወደ መታዘዝ ያመራል—የሚጸልዩ ወላጆች ያሏቸው ወጣቶች እና ልጆች ዕድለኞች ናቸው፣ ምክንያቱም እንደ እነዚህ አይነት ልጆች እግዚአብሔርን ለማወቅና ለመውደድ አጋጣሚ ይኖራቸዋል፡፡ ወላጆቻቸውን በማክበር እና በመታዘዝ፣ የሰማዩ አባታቸውን ማክበርና መታዘዝን ይማራሉ፡፡ እንደ ብርሃን ልጆች ሲራመዱ፣ ለሚያዩአቸው ወላጆቻቸው ሩህሩህና መልካም ጸባይ ያለው ሰው፣ አፍቃሪና ሰው አክባሪ ሲሆኑ ያላዩትን እግዚአብሔርን ለመውደድ ይበልጥ ብቁ ይሆናሉ፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው እርዳታ እውነትን በመለማመድ ለወላጆቻቸው ተማኝ ወኪሎች ሲሆኑ፣ ከዚያም በመርህና በምሳሌ የእግዚአብሔርን ባለቤትነት እውቅና በመስጠት እና ሥርዓታዊነት ባለው ሕይወት እና መልካም ንግግር እርሱን ያከብሩታል፡፡ 8 CGAmh 79.3

ታዛዦች ብቻ ሰማይ ይገባሉ—ጌታ በፍቅርና አክብሮት ይታዘዙት እንደሆነ ለማየት በምድራዊ ሕይወታቸው እነርሱን እየፈተነ እንደሆነ ወላጆችና መምህራን በልጆች አዕምሮ ያስርጹ፡፡ እዚህ ለክርስቶስ ታዛዥ የማይሆኑ በዘላለሙ ዓለም ውስጥ ታዛዥ መሆን አይችሉም፡፡ 129 CGAmh 80.1

ወላጆች ወይም ልጆች በላይኛው ቤት ተቀባይነት የሚያገኙ ከሆነ፣ በዚህ ምድር ላይ የእግዚአብሔርን ሕግጋት መታዘዝን የተማሩ ስለሆነ ነው፡፡ 10 CGAmh 80.2