የልጅ አመራር

70/85

ክፍል 16—የግብረ ገብ ሐቀኝነትን ጠብቆ ማቆየት

ምዕራፍ 68—የምግባረ-ብልሹነት መስፋፋት

አመጽ የበዛበት ዘመን— የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት አደጋዎች ውስጥ ነው። ከዓመፃ ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች። “ብዙዎች” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቲያን ነን ባዮችን ነው፡፡ እነርሱ በተስፋፋው አመጽ እና ከእግዚአብሔር ወደ ኋላ ማፈግፈግ ተጽዕኖ ይደርስባቸዋል፣ ነገር ግን በተጽዕኖ ሥር መውደቅ ለእነርሱ ግዴታ አይደለም፡፡ የዚህ ማሽቆልቆል ምክንያትም ከዚህ ክፋት ነጻ ሆነው አለመገኘታቸው ነው፡፡ ከአመጽ የተነሳ ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር የመቀዝቀዙ ገሃድ እነርሱም በተወሰነ ሁኔታ የዚህ ክፋት ተካፋይ መሆናቸውን ያሳያል፣ ይህ ባይሆን ኖሮ ግን ለእግዚአብሔር ያላቸው ፍቅር እና በዚህ ሥራ ውስጥ ያላቸው ጉጉት እና ቅንዓት ተጽዕኖር ሥር ባልወደቀ ነበር፡፡ 877 CGAmh 417.1

የብልሹ መጽሐፍት እና ሥዕሎች ተጽዕኖ— አያሌ ወጣቶች ለመጽሐፎች ጉጉት አላቸው። ሊያገኙት የሚችሏቸውን ሁሉ ያነባሉ፡፡ ስሜት ቀስቃሽ የፍቅር ታሪኮች እና ብልሹ ስዕሎች ብልሹ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ ልብ ወለዶች በብዙዎች በጉጉት ይነበባሉ፤ በዚህም ሳቢያ አስተሳሰባቸው ይረክሳል። እርቃናቸውን ያሉ የሴቶች ፎቶዎች አዘውትረው ለሽያጭ ይሰራጫሉ። እነዚህ አስጸያፊ ሥዕሎች እንዲሁ በፎቶ ሳሎኖች [ፎቶ ቤቶች] ውስጥ የሚገኙ እና ቅርጻ ቅርጾችን በሚሸጡ ሰዎች ግድግዳ ላይ የሚንጠለጠሉ ናቸው፡፡ ይህ ብልሹነት በየትኛውም ቦታ ተስፋፍቶ የሚገኝበት ዘመን ነው። የዓይን ምኞት እና ብልሹ ስሜቶች በማየት እና በማንበብ ይነሳሳሉ፡፡ ልብ በልብ ወለድ ሐሳብ ይረክሳል፡፡ ወራዳ እና ጸያፍ ስሜቶችን የሚቀሰቅስ ትዕይንቶችን በማሰላሰል አእምሮ ደስታን ያገኛል፡፡ በረከሰ አስተሳሳብ የሚታዩ እነዚህ ብልሹ ምስሎች ግብረ ገብን ያረክሱ እና የተታለሉ፣ የነሆለሉ ሰዎች የፍትወተ-ሥጋ ልጓም እንዲላላ ያዘጋጃሉ፡፡ ከዚያም በአምሳሉ የተፈጠሩ ሰዎችን ወደ እንስሳነት ደረጃ ዝቅ በማድረግ በመጨራሻም ወደ ጥፋት እንዲሰጥሙ የሚያደረጉ ኃጢአቶች እና ወንጀሎች ተከትለው ይመጣሉ፡፡ 878 CGAmh 417.2

ፍትወት ልዩ ኃጢአት— የዓለም አስፈሪ ሁኔታ ምስል በፊቴ ቀርቦ ነበር። የግብረ ገብ ጉድለት በሁሉም ቦታ ተስፋፍቷል። ፍትወት የዘመኑ ልዩ ኃጢአት ነው። ክፋት አሰቀያሚ ራሱን እንደአሁኑ በአይናውጣነት በጭራሽ ቀና አድርጎ አያውቅም፡፡ ህዝቡ የደነዘዘ ይመስላል፣ ደግሞም በጎነትን እና እውነተኛውን መልካምነትን የሚያፈቅሩ ሰዎች በአይናውጣነቱ፣ በጥንካሬው እና በመስፋፋቱ ተስፋ ቆርጠዋል፡፡ 879 CGAmh 418.1

ክርስቶስ ዳግም ከመገለጡ በፊት የሚሆነውን የዓለም ሁኔታ እውነተኛ መግለጫ ይሆን ዘንድ ወደ ሮሜ 1፡18-32 ተመራሁ፡፡ 880 CGAmh 418.2

እግዚአብሔርን ከህዝቡ የሚለየውና ነፍስ መደሰትና እርሱን ማክበር እንዳትችል የሚያደርግ ኃጢአት ነው እንጂ ፈተናና ስቃይ አይደለም፡፡ ነፍሳትን የሚያጠፋው ኃጢአት ነው፡፡ በሰንበት ጠባቂ ቤተሰቦች ውስጥም ኃጢአት እና ክፋት አለ፡፡ 881 CGAmh 418.3

ሰይጣን ወጣቶች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት— በዚህ የመጨረሻ ዘመን የወጣቶችን አእምሮ መያዝ፣ አስተሳሰቦችን ማበላሸት እና ስሜቶችን ማጋጋል የሰይጣን ልዩ ስራ ነው፤ ምክንያቱም እንዲህ በማድረጉ ወደ ርኩሰት ድርጊቶች ሊያመራቸው እንደሚችል እና በዚሁም ሳቢያ የተከበሩ የአእምሮ ችሎታዎች ሁሉ እንደሚዋረዱ እና ለራሱ ዓላማዎች ገጣሚዎች እንዲሆኑ ሊቆጣጠራቸው እንደሚችል ስለሚያውቅ ነው። 882 CGAmh 418.4

የመጻኢ ሕብረተሰብ አመላካች— የዛሬዎቹ ወጣቶች የመጻኢው ህብረተሰብ እርግጠኛ አመላካች ናቸው፤ ደግሞም እነርሱን ስንመለከት ለወደፊቱ ምን ተስፋ አለን? ብዙዎች መዝናናትን እና ስራ ጠልነትን የሚወዱ ናቸው ...፡፡ እነርሱ በጥቂቱ ብቻ ራሳቸውን የሚቆጣጠሩ እና በቀላሉ የሚደሰቱ እና የሚበሳጩ ናቸው። በእያንዳንዱ እድሜ እና የሕይወት መደብ ውስጥ እጅግ አያሌ ሰዎች መሰረታዊ መርህ ወይም ህሊና የሌላቸው ናቸው፤ እንዲሁም ዓለማችን ሁለተኛ ሰዶም እስከምትሆን ድረስ ከሥራ ፈትነት እና የብኩንነት ልምዶች ጋር ወደ ምግባረ ብልሹነት በመፍጠን ሕብረተሰቡን እየበከሉ ናቸው፡፡ የምግብ አምሮት እና ስሜቶች በምክንያታዊነት እና በሃይማኖት ቁጥጥር ስር ቢሆኑ ኖሮ ህብረተሰቡ እጅግ የተለየ ገፅታን ያሳይ ነበር፡፡ አሁን ያለው አስከፊ ሁኔታ እንዲኖር የእግዚአብሔር ዕቅድ አልነበረም፤ ይህም የተፈጥሮ ህጎችን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የመጣ ነው። 883 CGAmh 418.5

ራስን በራስ የመጉዳት ችግሮች— አንዳንድ የላቀ እምነት አላን ባዮች ራስን በራስ የመጉዳትን ኃጢያትና አይቀሬ ውጤቱን አይረዱም፡፡ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ልማድ መረዳታቸውን አሳውሮታል። እነርሱ የዚህ አዋራጅ ኃጢአት ታላቅ ኃጢአት መሆንን አይገነዘቡም፡፡ 884 CGAmh 419.1

የሁለቱም ጾታዎች ወጣቶች እና ልጆች በሥነ ምግባር ብልሹነት ውስጥ በመሳታፍ ይህን አስጸያፊ፣ ነፍስ-እና-አካልን አውዳሚ ድርጊት ይለማመዳሉ። ብዙ ክርስቲያን ነን ባዮች በተመሳሳይ ልምዶች ከመደንዘዛቸው የተነሳ ግብረ ገባዊ ስሜቶቻቸው ይህ ኃጢአት መሆኑን ለመገንዘብ አይነሳሱም፣ እናም በዚያው የሚቀጥል እንደ ሆነ የአካልና የአዕምሮ ውድቀት አይቀሬ ውጤት ይሆናል፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው፣ እጅግ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ እራሱን ወደ አውሬነት ይለውጣል! ራሱን ቅጥ ያጣ እና ብልሹ ያደርጋል፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን ስሜቶቹን መግታት እና በመርህ ቁጥጥር ሥር መሆንን መማር አለበት። ይህንን ካላደረገ በስተቀር ለክርስቲያን ስም ብቁ አይሆንም፡፡ 885 CGAmh 419.2

ከማንኛውም ክፋት ይልቅ ምግበረ ብልሹነት የሰው ዘር እንዲያሽቆለቁል አድርጓል፡፡ ይህ አስደንጋጭ በሆነ መጠን የተተገበረ እና እያንዳንዱን አይነት በሽታ ያመጣ ነው ማለት ይቻላል። በጣም ትናንሽ ልጆች፣ ሕፃናት፣ በወሲባዊ አካላት ተፈጥሯዊ መቆጣት ጋር በመወለድ፣ በመነካካት ጊዜያዊ እፎይታን ያገኛሉ፣ ይህም ከዕድገታቸው ጋር እያደገ የሚመጣ መቆጣትን ብቻ የሚጨምር እና ድርጊቱን ወደ መደጋገም የሚያመራ ይሆናል፡፡ 886 CGAmh 419.3

የፍትወት ተፈጥሮአዊ ዝንባሌዎች ይወረሳሉ— በጥቅሉ ወላጆች ልጆቻቸው ስለዚህ መጥፎ ምግባር አንዳች ነገር እንደሚያውቁ አይጠረጥሩም። በብዙ ሁኔታዎች አንጻር ወላጆች በትክክል ኃጢአተኞች ናቸው፡፡ የጋብቻ መብቶቻቸውን አላግባብ በመጠቀም አግባብነት የሌላቸውን ስሜቶችን በማርካት የእንስሳነትን ምኞት አጎልብተዋል፡፡ እነዚህም ሲጠናከሩ ግብረ ገባዊ እና አዕምሯዊ ችሎታዎች ደካማ ይሆናሉ፡፡ መንፈሳዊው በአውሬው ቁጥጥር ሥር ሆኗል፡፡ ልጆች የወላጆች ባህሪይ ማህተም የሆነውን እጅግ የጎለበቱ የእንስሳነት ዝንባሌዎችን ይዘው ይወላዳሉ…፡፡ ለእነዚህ ወላጆች የተወለዱላቸው ልጆች ዘወትር በተፈጥሮ የዚህን ምስጢራዊ መጥፎ ምግባር ልማዶችን ይዘው ይወለዳሉ...፡፡ ወላጆች የራሳቸውን የፍትወት ተፈጥሮአዊ ዝንባሌዎች ማህተም ስለሚሰጡአቸው የወላጆች ኃጢአቶች ልጆቻቸው ላይ ይደርሳል፡፡ 887 CGAmh 420.1

አፍዛዥ ባርነት— ተራ ያልሆነ አዕምሮ እና ችሎታ ያላቸውን ወንዶች እና ሴቶችን የሚቆጣጠር የእንስሳነት ስሜት ኃይለኛ ተጽዕኖ ስመለከት በጥልቅ ይሰማኛል። በርካሽ ስሜቶች ባርያ ባይሆኑ ኖሮ ኃይለኛ ተጽዕኖም ለማሳደር መልካም ሥራ ላይ የመሳተፍ አቅም ይኖራቸዋል፡፡ በሰው ልጆች ላይ ያለኝ እምነት በሚያስፈራ ሁኔታ ተናወጠ፡፡ CGAmh 420.2

በግልጽ መልካም ጸባይ ያላቸው፣ ከሌሎች ጾታዎች ጋር አግባብነት የሌላቸውን ግንኙነቶች የሌላቸው ሰዎች በህይወታቸው በሙሉ ማለት በሚቻልበት ሁኔታ በየቀኑ ምስጢራዊ መጥፎ ተግባሮችን በመፈፀም ጥፋተኛ እንደሆኑ ተመልክቻለሁ፡፡ እጅግ የተከበሩ ስብሰባዎች በሚካሄዱበት ጊዜ እንኳ ከዚህ አስፈሪ ኃጢአት አልታቀቡም፡፡ በእግዚአብሔር ፍርድ ችሎት ፊት እንደሚቀርቡ፣ እንዲፈሩ እና እንዲንቀጠቀጡ የሚያደርጋቸውን እጅግ የተከበረ፣ አስገራሚ ንግግሮችን ሰምተዋል፤ ዳሩ ግን የሚወዱትና አፍዛዥ የሆነ ኃጢአት ሳይፈጽሙ እና የገዛ አካሎቻቸውን ሳያረክሱ አንድ ሰዓት እንኳ ማሳለፍ አይችሉም፡፡ እነርሱ ለዚህ አሰቃቂ ወንጀል እንደዚህ ዓይነት ባሪያዎች ስለነበሩ ምኞቶቻቸውን የመቆጣጠር አቅም አጥተዋል፡፡ ለአንዳንዶቹ በትጋት ሰርተንናል፣ ተማጽነናል፣ ስለ እነርሱ አንብተናል ጸልየንማል፤ ነገር ግን እርግጥ ከሆነው ልፋታችን እና ጭንቀታችን ሁሉ አልፎ ተርፎ፣ የኃጢያት ልማድ ኃይል የበላይ ሆኖ አግኝተነዋል፣ እነዚህም ኃጢያቶች ተፈጽመዋል። 888 CGAmh 420.3

የክፉ ምግባር እውቀት በሰለባዎቹ በመስፋፋት ላይ ይገኛል— በዚህ ነፍስ-እና-አካል አውዳሚ ክፉ ምግባርን ሙሉ በሙሉ የሚተገብሩ ሰዎች እነዚያ የምስጢራዊ ክፋት ሸክማቸውን ለጓደኞቻቸው እስኪያካፍሉ ድረስ እምብዛም አያርፉም። የማወቅ ጉጉት በአንድ ጊዜ ይነሳሳ እና የዚህን አዋራጅ ኃጥአት የማያውቅ አንድም ሰው እስኪጠፋ ድረስ የክፉ ተግባር እውቀት ከወጣት ወደ ወጣት፣ ከልጅ ወደ ልጅ እየተላለፈ ይሄዳል፡፡ 889 CGAmh 421.1

አንድ ብልሹ አዕምሮ ብዙዎች ዕድሜ ልካቸውን መንቀል የማይችሉትን የክፋት ፍሬ በአጭር ጊዜ መዝራት ይችላል፡፡ 890 CGAmh 421.2