የልጅ አመራር

71/85

ምዕራፍ 69—የጎጂ ልማዶች ውጤቶች

ወሳኝ ጉልበት ተደምስሷል— የምስጢር ተግባር ልምምድ የአካል ስርዓትን ወሳኝ ኃይሎችን ያጠፋል። እያንዳንዱ አላስፈላጊ ትልቅ ድርጊት ተጓዳኝ ድባቴን ያስከትላል፡፡ በወጣቶች መካከል ዋና ርዕሰ አምድ የሆነው አዕምሮ የአካል ሥርዓትን ለተለያዩ በሽታዎች የሚያጋልጥ እጥረት እና ከፍተኛ ድካም እስኪፈጠር ድረስ ገና በልጅነት በአደገኛ ሀኔታ ይጠመዳል፡፡ 891 CGAmh 422.1

በኋለኛው ዕድሜ ለሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎች መሰረት ይጣላል— ልምምዱ ከአስራ አምስት እና ከዚያ በላይ ለሚሆን ዕድሜ የቀጠለ እንደሆነ ተፈጥሮዋ የደረሰበትን በደል እና እየደረሰባት ያለውን ጉዳት በመቃወም በተለይም ከሰላሳ እስከ አርባ አምስት ዕድሜ መካከል፣ በጉበት እና በሳንባ በሽታ፣ በነርቭ በሽታ፣ በአንጀት በሽታ፣ በአከርካሪ በሽታ፣ በሽተኛ ኩላሊቶች እና በካንሰር እብጠቶች የተፈጸመባትን ሕግ የመተላለፍን ቅጣት በአካል ሥርዓት ላይ በሚከሰቱ በርካታ በሽታዎች እና የተለያዩ ሕመሞች ታስከፍላለች፡፡ የተወሰኑት የተፈጥሮ ረቂቅ ማሽኖች በሌሎች አካላት ላይ ከባድ ሥራን በመተው ዘወር ይላሉ፣ ይህም የተፈጥሮን ረቂቅ ቅንጅትን የሚረብሽ ነው፤ ደግሞም ብዙውን ጊዜ ድንገተኛ የአካል ሁከት እና ሞት የዚህ ውጤቱ ይሆናል። 892 CGAmh 422.2

ስድስተኛው ትእዛዝ በጭካኔ ተጥሷል— የአንድን ሰው ሕይወት በቅጽበት መንጠቅ በመንግሥተ ሰማይ ቀስ በቀስ፣ ነገር ግን በእርግጠኝነት ከማጥፋት የባሰ ታላቅ ኃጢያት አይደለም፡፡ ስህተት በመስራት በእርግጥ መበስበስን በራሳቸው ላይ የሚያመጡ ሰዎች እዚህ ቅጣቱን የሚቀበሉ እና በአግባቡ ንስሃ ካልገቡ በስተቀር ሕይወትን በቅጽበት ከሚያጠፋው ሰው በተሻለ ወደ ሰማይ የሚገቡ አይደሉም። የእግዚአብሔር ፈቃድ በመንስኤ እና በውጤቶቹ መካከል ያለውን ትስስር ያጠናክራል፡፡ 893 CGAmh 422.3

ንፁህ-አእምሮም የላቸውም ሰዎች እንዲሁ በበሽታ ይጠቃሉ— ደካማ የሆኑ ወጣቶችን በሙሉ በተሳሳተ ልማድ ጥፋተኝነት ውስጥ አናካትታቸውም። ከእነርሱ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ምክንያቶች የሚሰቃዩ ንጹህ አዕምሮ ያላቸው እና አሳቢ ወጣቶች አሉ፡፡ 894 CGAmh 423.1

የአእምሮ ሀይሎች ተዳክሟል— ሞኝ እና የሚያሞላቅቁ ወላጆች ልጆቻቸው ትምህርታቸውን በጣም የሚወዱ ስለሆኑ እና ጥናታቸውን በጥብቅ በማከናወናቸው ጤናቸውን እየጎዱ ስለሆነ ያዝናሉ፡፡ እውነት ነው፣ እጅግ ብዙ እና በጣም ከባድ በሆኑ ጥናቶች የወጣቶችን አእምሮ ማጨናነቅ አይመከርም፡፡ ነገር ግን፣ ወላጆች፣ ልጆቻችሁ የሚያቀርቡትን ሀሳብ ከመቀበል ይልቅ ጉዳዩን በጥልቀት አልተመለከቱትምን? ግልጽ ለሆነ ጤናን የማጣት ምክንያት በችኮላ እውቅና አልሰጣችሁምን? ወላጆች እና አሳዳጊዎች መንስኤውን ለማዋቅ ጠለቅ አድርገው መመልከት አለባቸው፡፡ 895 CGAmh 423.2

የእነዚህ ልጆች አእምሮ በጣም የተዳከመ ከመሆኑ የተነሳ መልካም ምግባረ እና ንፁህ ቢሆኑ ኖሮ ሊኖራቸው ይችል ከነበረው የአዕምሮ ብልህነት አንድ ግማሽ ወይም አንድ ሦስተኛ ብቻ ይኖራቸዋል፡፡እርሱንም እራሳቸውን በራሳቸው በመበደል ነው ያጡት፡፡6 CGAmh 423.3

ከፍተኛ ውሳኔ እና መንፈሳዊ ሕይወት ተደምስሷል— ምስጢራዊ ብልግና ከፍተኛ ውሳኔ፣ ልባዊ ጥረት እና ጥሩ ሃይማኖትን ለመመስረት ያለውን የፈቃድ ጥንካሬ ደምሳሽ ነው፡፡ ክርስቲያን መሆን ምን ምን እንደሚይዝ እውነተኛ ስሜት ያላቸው ሁሉ፣ ልክ እንደ ደቀ መዛሙርት የክርስቶስ ተከታዮች ፍላጎቶቻቸውን፣ አካላዊ ኃይሎቻቸውን እና የአእምሮ ችሎታቸውን በፍጹም ለእርሱ ፈቃድ የማስገዛት ግዴታ ሥር እንዳሉ ያውቃሉ። ስሜቶቻቸው የሚገዛቸው ሰዎች የክርስቶስ ተከታዮች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ እነርሱ ብልሹ ልምዶቻቸውን ትተው የክርስቶስን አገልግሎት እንዳይመርጡ የሁሉ ክፋት ጠንሳሽ ለሆነው ጌታቸው አገልግሎት በጣም የተጉ ናቸው፡፡ 896 CGAmh 423.4

ሃይማኖት ሥርዓታዊ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ጎደሎ ነው— የክርስቶስ ተከታዮች ነን የሚሉ አንዳንድ ሰዎች በአምላክ ላይ ኃጢአት እየሠሩና ጤንነታቸውን እያጠፉ እንደሆነ ያውቃሉ፣ ሆኖም ግን እነርሱ ለሚሰሩት ብልሹ ምኞቶቻቸው ባሮች ናቸው። እነርሱ የጥፋተኝነት ሕሊና ይሰማቸዋል እናም በስውር ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ ያነሰ ዝንባሌ አላቸው፡፡ እነርሱ የሃይማኖትን መልክ ይዘው ሊቀጥሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን በልባቸው ውስጥ የእግዚአብሔር ጸጋ የጎደላቸው ናቸው፡፡ ለአገልግሎቱ ምንም ዓይነት ፍቅር የላቸውም፣ በእርሱም ላይ እምነታቸውን አይጥሉም ፣ ለእርሱ ክብር አይኖሩም፣ በሥርዓቶቹም ደስ አይሰኙም፣ በእርሱም ደስ አይሰኙም፡፡ 897 CGAmh 424.1

ራስን የመግዛት ኃይል የጠፋ ይመስላል— አንዳንዶች የኃጢያት ፍላጎቶችን የማርካትን ክፋት አምነው ይቀበላሉ፣ ሆኖም ፍላጎቶቻቸውን ማሸነፍ እንደማይችሉ ያስተባብላሉ፡፡ የክርስቶስን ስም ለሚጠራ ማንኛውም ሰው ይህ አስፈሪ ቅበላ ነው፡፡ “የክርስቶስን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ።” ይህ ድክመት ለምን ተፈጠረ? ምክንያቱም የእንስሳነት ተፈጥሮአዊ ዝንባሌዎች በከፍተኛ ኃይሎች ላይ የበላይነት እስኪያገኙ ድረስ በልምምድ ስለ በረቱ ነው፡፡ ወንዶች እና ሴቶች መሠረታዊ መርኾ የላቸውም፡፡ ራስን የመግዛት ኃይላቸው የጠፋ እስኪመስል ድረስ የተፈጥሮ አምሮታቸውን ረዘም ላለ ጊዜ ልቅ ስላደረጉ በመንፈሳዊነት እየሞቱ ናቸው፡፡ የተፈጥሮአቸው ወራዳ ስሜቶች ልጓማቸውን ስለወሰዱ፣ ገዢ ኃይል መሆን የነበረበት ለስሜት አገልጋይ ሆኗል፡፡ ነፍስ በወራዳ እስራት ተይዛለች፡፡ ስሜታዊነት የቅድስናን ምኞት አጥፍቷል፣ መንፈሳዊ ብልጽግናንም እንዲጠወልግ አድርጓል። 898 CGAmh 424.2

ከሰማይ ጋር የሚደረግ ግንኙነት አደጋ ላይ ወድቋል— ከሰማይ የሆኑ ክቡር መልዕክቶች በዚህ ወራዳ ብልግና ያልተመሸጉ ሰዎችን ልብ በኃይል መንካት አይችሉም። የአዕምሮ ስስ ነርቮች በክፉ ነገሮች ፍቅር ጡፈት ኢተፈጥሮአዊ ስሜታዊ ፍላጎትን ለማርካት ጤናማ ለዛቸውን አጥተዋል፡፡ ከመላው የአካል ስርዓት ጋር የሚገናኙት የአንጎል ነርቮች ሰማይ ከሰው ጋር የሚገናኝበት እና በውስጠኛው ህይወቱ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር የሚችልበት ብቸኛው መንገድ ነው። በነርቭ ሥርዓቱ ውስጥ የኤሌክትሪክ ሞገድን ስርጭት የሚረብሽ ነገር ሁሉ የአብይ ኃይል ጥንካሬን በመቀነስ የአእምሮ ስሜት ኃይሎችን ሞት ያስከትላል፡፡ ከእነዚህ እውነታዎች አንፃር፣ እግዚአብሔርን እንመስላለን የሚሉ አገልጋዮች እና ሕዝብ ከዚህ ነፍሰን ከሚያረክስ ብልግና ንጹህ ሆኖ መገኘታቸው ምንኛ አስፈላጊ ነው! 899 CGAmh 424.3

አንዳንዶች ይጸጸታሉ፣ ዳሩ ግን ለራሳቸው ያላቸውን አክብሮት ያጣሉ— እነዚህ ወራዳ ልማዶች የሚያስከትሉት ውጤት በሁሉም አዕምሮዎች ላይ አንድ አይደለም። የግብረ ገብ ኃይሎቻቸው እጅግ የጎለበተ፣ ይህን ራስን የመጉዳት ድርጊትን ከሚፈጽሙ ልጆች ጋር ጓደኝነት ሲፈጥሩ ብልግናውን የሚጀምሩ አንዳንድ ልጆች አሉ፡፡ በእነዚያ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ብዙውን ጊዜ ጥልቅ ሐዘን፣ ግልፍተኛ እና የቅናት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰዎች ለኃይማኖታዊ አምልኮ ያላቸውን አክብሮት እጦት እና ለመንፈሳዊ ነገሮች ልዩ አለመታመንን ላያሳዩ ይችላሉ። አንዳንድ ጊዜ በጸጸት ስሜቶች በጥልቅ ይሰቃያሉ፣ በገዛ ራሳቸው ፊት ዝቅተኝነት ይሰማቸዋል፣ ለራሳቸውም ያላቸውን አክብሮትም ያጣሉ። 900 CGAmh 425.1

አእምሮን ለፈተና እንዲቋቋም መመሸግ ይቻላል— የሥነ ምግባር ኃይሎች ከሰረጹ ልማዶች ጋር በሚዋጋበት ጊዜ እጅግ በጣም ደካማ ይሆናል፡፡ ርኩስ ሀሳቦች ምናብን በሚቆጣጠሩበት ጊዜ ፈተና ሊቋቋሙት የማይችል ይሆናል። አዕምሮ የከበሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ማሰላሰል የለመደ ከሆነ፣ አዕምሮ ንጹህ እና ቅዱስ ነገሮችን እንዲመለከት የሰለጠነ ከሆነ ፈተናን ለመቋቋም የተመሸገ ይሆናል፡፡ እርሱ በሰማያዊው፣ ንጹህ፣ በቅዱስ ነገሮች ላይ ጊዜውን የሚያሳልፍ ሲሆን ወደ ርካሽ፣ ብልሹ እና ብልግና ሊስብ አይችልም። 901 CGAmh 425.2

በእነዚህ ነገሮች ላይ ጠንቃቆች ሁኑ— ርካሽ ስሜቶችን ማርካት ብዙዎች ብርሃኑን ከማያት አይኖቻቸውን አንዲጨፍኑ ይመራቸዋል፣ ምክንያቱም ለመተው ፈቃደኞች የማይሆኑ ኃጢአቶችን ማየት ስለሚፈሩ ነው፡፡ ፈቃደኞች ቢሆኑ ሁሉም መየት ይችሉ ነበር፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ቢመርጡ ወንጀለኛነታቸው ያነሰ አይሆንም፡፡ አካላዊ፣ አዕምሮአዊ እና ግብረ ገባዊ ጥንካሬአቸውን በሚነካው በእነዚህ ነገሮች ወንዶች እና ሴቶች በማንበብ ለምን ብልሆች አይሆኑም? ይህን መኖሪያ እግዚአብሄር ሰጠን ለአገልግሎቱ እና ክብሩ በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ እና ጠበቆ ማቆየት እንድንችል ነው፡፡ ሰውነትህ የራስህ አይደለም ፡፡ “ወይሰ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናነተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ፡፡” “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፍርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፣ ያውም እናንተ ናችሁ፡፡” 9 CGAmh 425.3