የልጅ አመራር

69/85

ምዕራፍ 67—የፋሽን አስደናቂ ኃይል

ፋሽን ጨቋኝ ገዥ ናት— ፋሽን ዓለምን ትገዛለች፤ እናም ብዙውን ጊዜ አምላኪዎቿን ወደ የባሰ ችግር እና ምቾት ማጣት እንዲገቡ የምታስገድድ ጨቋኝ እመቤት ነች። የፋሽን ያለምክንያት ትቀርጣለች፣ ያለ ምሕረትም ትሰበስባለች። እሷ አስደናቂ ኃይል ያላት እና የእሷን ጎዳና የማይከተሉትን ሁሉ ለመንቀፍ እና በእነርሱ ላይ ለማፌዝ ዝግጁ ናት፡፡ 866 CGAmh 411.1

ሀብታሞች ዘወትር ከሚለዋወጡት የተለያዩ ዘይቤዎቿ ጋር ተስማምተው በመኖር አንዳቸው ከሌላኛው የተሻለ የመሆን ጉጉት አላቸው፡፡ የመካከለኞጭ እና የድሃው መደብ ክፍሎች ከእነርሱ በላይ እንደሆኑ የሚታሰቡት የመደቡት ደረጃ ላይ ለመድረስ ይጥራሉ፡፡ ገንዘብ ወይም አቅም ውስን ሆኖ ሲገኝ፣ እና የቁንጮነት ምኞት ታላቅ ሲሆን ሸክሙ ሊደገፍ የማይችል ይሆናል። ለብዙዎች የሚለብሱት ልብስ ተስማሚ ወይም የሚያምር ቢሆንም እንኳ፣ ምንም ችግር የለውም፣ ፋሽን በሚቀየርበት ጊዜ እንደገና መታደስ ወይም መጣል አለበት።2 CGAmh 411.2

ያለማቋረጥ በመለወጥ ላይ ባለ፣ ጭራሽ እርካታ በሌላው የፋሽን አዋጅ መሪ እና ዋና አንቀሳቃሽ የሆነው ሰይጣን በአካላዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጤንነት ላይ ጉዳት የሚያደርስ አዲስ ነገር በማዘጋጀት ዘወትር በትጋት ይሠራል፤ ዕቅዶቹም በጥሩ ሁኔታ ስለሚሳኩለት ድል ያደርጋል፡፡ በፋሽን መስገጃ ሥፍራዎች የሚሰግዱ አምላኪዎች ጤናን ጉዳት ላይ የሚያደርስ ጅልነት እና እውር ጉጉት በእርሱ ሥር እንዲመጡ ስለሚያደርግ ሞት ይስቃል፡፡ ደስታ እና በእግዚአብሔር ፊት ያላቸው ሞገስ በመሠዊያዋ ላይ ተሰቅለዋል። 867 CGAmh 411.3

የአለባበስ ጣኦት አምላኪነት የግብረ ገብ በሽታ ነው፡፡ እርሱ ወደ አዲስ ሕይወት መምጣት የለበትም፡፡ ለወንጌል መስፈርቶች መገዛት በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች በአለባበስ ረገድ ፍጹም ለውጥ ይፈልጋል፡፡4 CGAmh 412.1

አንዳንዶች የሚከፍሉት ዋጋ— ብዙዎቹ ፋሽን የምታስተላልፋቸው የአለባበስ ስልቶች ትዕዛዛት በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ከተሰጡት መርኾዎች ጋር እንዴት የሚቃረን ነው! ላለፉት ጥቂት መቶ ዓመታት ወይም ላለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት ያህል ሞልተው የነበሩ የልብስ ሞዶችን አስቡ። ንጽህት፣ እግዚአብሔርን ለምትፈራ፣ እራሷን ለምታከብር ሴት ተገቢ እንዳልሆነ የሚነገርለት ስንቱ ነው…፡፡ አያሌ ምስኪን ልጃገረዶች ለቄንጠኛ አለባበሷ ስትል ሙቀትን ከሚሰጥ የውስጥ ልብስ እራሷን በመከልከል በሕይወቷ ውስጥ የቅጣትዋን ዋጋ ትከፍላለች፡፡ ሌሎች ብዙ ሰዎች የሀብታሞችን ታይታ እና ግርማ ሞገስ በመመኘት ተማኝነትን ወደ ማጣት እና እፍረት መንገድ ተስበዋል። ብዙ ቤቶች ምቾትን አጥተዋል፣ ብዙዎች ሰዎች የሚስቶቻቸውን ወይም የልጆቻቸውን ቅጥ ያጣ ፍላጎቶችን ለማርካት ወደ ማጭበርበር ወይም ኪሳራ እንዲሳቡ ተደርገዋል፡፡ 868 CGAmh 412.2

ድነት በአለባበስ የጣኦት አምልኮ ሳቢያ አደጋ ላይ ይወድቃል— ኩራት እና ከንቱነት በሁሉም ቦታ ይታያሉ፤ ነገር ግን እራሳቸውን ለማድነቅ መስታወትን መመልከት የሚፈልጉ ሰዎች ታላቅ የግብረ ገብ መስታወት ወደ ሆነው የእግዚአብሔርን ህግ የመመልከት ጥቂት ዝንባሌ ብቻ ይኖራቸዋል። ይህ የአለባበስ የጣኦት አምልኮ ትህትናን፣ የዋህነትን ፣ እና መልካም ባህሪይን ሁሉ ያጠፋል። በማሰላሰል፣ ልብን በመመርመር፣ እና የእግዚአብሔርን ቃል በጸሎት በማጥናት ላይ መዋል የነበረባቸውን ውድ ሰዓታትን ይበላል…፡፡ አንድም ክርስቲያን የነፍሱን ድነት ለአደጋ ሳያጋልጥ ግብረ ገብ ከጎደለው ዓለም ፋሽን ጋር መመሳሰል አይችልም፡፡ 869 CGAmh 412.3

የታይታ ፍቅር ቤትን ግብረ ገብ የጎደለው ያደርጋል— ሴቶች በክርስቶስ ጸጋ በመደገፍ፣ ታላቅ እና የተከበረ ስራ የመሥራት ችሎታ አላቸው። በዚህም ምክንያት በዚህ ዘመን ውስጥ ባሉ ክርስቲያን ነን ባዮች እናቶች እንኳ የታይታ ፍቅር አዕምሮ፣ ልብ እና ስሜትን እንዲይዝ፣ ልጆቻቸውን ለማስተማር እና ለማሰልጠን ጊዜ እንዳይኖራቸው ወይም ለልጆቻቸው ምሳሌ ለመልካም ሥራ ሞዴል መሆን ይችሉ ዘንድ፣ የራሳቸውን አዕምሮ እና ባህሪያትን እንዳያሳድጉ፣ ሰይጣን ፋሽንን ለመፍጠር ከሚጠቀምባቸው መሳሪያዎቹ ጋር ይሠራል፡፡ ሰይጣን የእናትን ጊዜ እና ስሜት ሲቆጣጠር ምን ያህል እንደሚያተርፍ በሚገባ ያውቃል፡፡ ከአስር እጅ በዘጠኙ የመላውን ቤተሰብ ፍቅር ለአለባበስ እና ለከንቱ ታይታ አድርጓል፡፡ እናትን ስለ ማረከ ልጆችን እንደ ምርኮው ይቆጥራቸዋል፡፡ 870 CGAmh 413.1

እናት ከአዳኟ ይልቅ ከፋሽን ጋር የተላመደች ስለሆነ…ትናንሽ ልጆች ከድነታቸው ይልቅ ስለ አለባበሳቸው ይበልጥ ይሰማሉ... ። 871 CGAmh 413.2

ወላጆች እና ልጆች በሕይወት ውስጥ ምርጥ፣ ጣፋጭ እና እውነት የሆነውን ነገር አጥተዋል፡፡ ለፋሽን ሲሉ ለመጻኢው ሕይወት ዝግጅት እንዳያደርጉ ተታልለዋል፡፡ 872 CGAmh 413.3

ማዕበልን ለማስቆም ደፋሮች አይደሉም— የአያሌ እናቶች ሸክም ከፋሽን ጋር እኩል ለማራመድ የሚደረግ ጥረት ውጤት ነው፡፡ እነዚህ ፋሽኖች በአካላዊ፣ በአዕምሮአዊ እና በሥነ-ምግባራዊ ጤና ላይ የሚያስከትሉት ውጤቶች በጣም አስከፊ ናቸው፡፡ ሴቶች በጽናት ከእውነት ጎን ለመቆም ድፍረቱ ስለሌላቸው ዝነኛ ስሜት አዝማሚያ በተነሳ ቁጥር ወደ ራሱ እንዲሳባቸው ይፈቅዳሉ…፡፡ ብዙውን ጊዜ ክርስቲያን ነን የሚሉ እናቶች ፋሽንን አምላካቸው ያደረጉ አያሌ ሰዎችን ለመከተል ባላቸው ምኞት መርኾን መስዋዕት ያደርጋሉ፡፡ ሕሊና ተቃውሞ ያቀርባል፣ ነገር ግን እነርሱ ከስህተት በተቃራኒ ለመቆም ቆራጥ አቋም ለመያዝ ድፍረቱ የላቸውም፡፡ 873 CGAmh 413.4

ወላጆች — ተጠንቀቁ— ወላጆች ብዙውን ጊዜ ከመጠን በላይ ውድ የሆነ ልበስ፣ ብዙ የታይታ ጌጣ ጌጦች ያለውን ልብስ ልጆቻቸውን ያለብሳሉ፣ ከዚያም የአለባበሳቸውን ውጤት በግልጽ ያደንቃሉ፣ በመልካቸውም ላይ ያላቸውን ፍቅር ይገልጻሉ። እነዚህ ሞኝ ወላጆች ሰይጣን ጥረቶቻቸው ላይ እንዴት እንደሚያክል እና ወደ ባሰ ጅልነት እንዴት እንደሚወስዳቸው ቢመለከቱ ኖሮ በድንጋጤ ይሞሉ ነበር፡፡11 CGAmh 414.1

ብዙ እናቶች የሚያጋጥሟቸው ችግሮች— ሴቶች ልጆቻችሁ እነርሱ ካላቸው የተለየ ልብስ ካዩ ከዚያ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ልብስ ወደ መልበስ ያዘነብላሉ፡፡ ወይም ደግሞ እናንተ ለእነርሱ ለመስጠት ከእምነታችሁ ጋር የሚጣጣም እንዳልሆ የሚሰማችሁን ምናልባት ሌሎች እንዳላቸው ያዩትን ሌላ ነገር ይፈልጉ ይሆናል፡፡ በወንጌል መሰረታዊ መርሆዎች ረገድ እነርሱን ከመቅረጽ ይልቅ እነርሱ እንዲቀርጿችሁ በማድረግ ይህ ነገር ከተጽዕኖአችሁ ውጭ እንዲሆኑ ትፈቅዳላችሁን? ልጆቻችን በእግዚአብሔር ፊት በጣም ውድ ናቸው። የእግዚአብሔርን ቃል እናስተምራቸውና በእርሱም መንገዶቹም እናሠለጥናቸው፡፡ በሰማይ ተቀባይነት እንዲኖራቸው በሚያደርግ መልኩ እንዲኖሩ ልጆችቻችሁን ማስተማር ልዩ መብታችሁ ነው…፡፡ CGAmh 414.2

ልጆቻችን የዓለምን ፋሽን እንዲከተሉ አናበረታታቸው፤ እናም ለእነርሱ ትክክለኛውን ሥልጠና በመስጠት ረገድ ታማኞች ከሆንን፣ ይህንን አያደርጉም…፡፡ የዓለም ፋሽን ብዙውን ጊዜ አስነዋሪ ቅርጽ ይኖረዋል፣ በመሆኑም እርሱን ለመቃወም ጽኑህ አቋም ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ 874 CGAmh 414.3

የታይታ ፍቅር ፍሬ — የአለባበስ እና የተድላ ፍቅር በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ደስታ እያጎዳ ነው። ደግሞም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እንደሚወድዱ እና እንደሚጠብቁት ከሚናገሩ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ በተቻላቸው መጠን ሁሉ ከዚህ የሕብረተሰብ መደብ ጋር ለመመሳሰል እየኮረጁ የክርስቲያንን ስም ይይዛሉ፡፡ አንዳንድ ወጣቶች የልብስ ከንቱነት እና የተድላ ፍቅር ዝንባሌአቸውን ብቻ መከተል ከቻሉ፣ ለታይታ ከፍተኛ ጉጉት ስላላቸው የክርስትናን ስም ለመተው እንኳ ፈቃደኞ ናቸው፡፡ 875 CGAmh 414.4

ለታይታ በመልበስ አብዛኛውን ጊዜያቸውን የሚያጠፉ ቤተሰቦች የሱስ ከሩቅ በተመለከታት የበለስ ዛፍ ሊመሰሉ ይችላሉ፡፡ ይህች የበለስ ዛፍ በፍርድ ፊት የበለጸጉ ቅርንጫፎቿን ለይስሙላ አሳይታለች፤ ነገር ግን ክርስቶስ ፍሬን ለመፈለግ በመጣ ጊዜ ከላይኛው ቀንበጦጥ እስከ ታችኛው ቅርንጫፎች ድረስ ፈልጎ ከቅጠሎች ሌላ ምንም አላገኘም፡፡ እርሱ የተራበው ፍሬ ነው፤ እርሱ ፍሬ ማግኘት ይፈልጋል፡፡14 CGAmh 415.1

ለእግዚአብሔር ሴቶች ልጆች የማያረካ ነው— ችግር እና ስቃይ ባለበት በዚህ ዓለም ውስጥ ውድ ጊዜን በጌጣ ጌጥ እና ታይታ ከማሰለፍ ይልቅ አስፈላጊ እና ወሳኝ የሆነ በቂ ሥራ አለ፡፡ የንጉስ ቤተሰብ አባል የሆኑ፣ የሰማዩ ንጉስ ሴቶች ልጆች፣ ከሰማይ ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲኖራቸው እና ከዓለም ቤዛ ጋር በአብሮነት በመስራት ከፍ ወዳለው ሕይወት ለመደረስ የኃላፊነት ሸክም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ በዚህ ሥራ የተጠመዱ ሰዎች በእነዚህ የመጨረሻ ጊዜያት አዕምሮአቸውን እና አፍቅሮታቸውን በሚይዝ ፋሽን እና ጅልነት አይረኩም፡፡ እነርሱ በእርግጥም የእግዚአብሔር ሴቶች ልጆች ከሆኑ፣ የመለኮት ባህሪይ ተካፋዮች ናቸው፡፡ በሕብረተሰቡ ውስጥ ያሉ ብልሹ ተጽዕኖዎችን ሲመለከቱ ልክ እንደ መለኮታዊ ቤዛቸው፣ ጥልቅ በሆነ የሐዘን ስሜት ይታወካሉ፡፡ ክርስቶስ ከፍ ባለው ስፍራው ለሰው ልጆች ጥቅም እንደሠራ ሁሉ እነርሱም ችሎታ እና አጋጣሚ እንደማግኘታቸው መጠን ከክርስቶስ ጋር ያላቸውን ርኅራሄ ያሳያሉ፡፡ 876 CGAmh 415.2