የልጅ አመራር

68/85

ምዕራፍ 66—የአለባበስ መሰረታዊ መርኾዎችን ማስተማር

አስፈላጊው የትምህርት ክፍል— በአለባበስ ረገድ ትክክለኛ መሠረታዊ ሥርዓቶችን የማያስተምር ትምህርት የተሟላ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትምህርት ከሌለ የትምህርት ሥራ ብዙውን ጊዜ ወደኋላ ይመለሳል፣ መንገዱንም ይስታል፡፡ የአለባበስ ፍቅር እና ፋሽንን መውደድ የአስተማሪው ዋና ተቀናቃኞች እና እጅግ ውጤታማ እንቅፋቶች መካከል ናቸው፡፡827 CGAmh 398.1

ምንም ዓይነት አቅጩን የሚናገር ዘይቤ አልተሰጠም— አለባበሳቸውን ሁሉ የሚመራ አንድ ዓይነት ትክክለኛ የዘይቤ መመሪያ አልተሰጠኝም፡፡ 828 CGAmh 398.2

ግሩም፣ ማራኪ፣ ንጹህ— ወጣቶች ገጽታቸው ግሩም እና ማራኪ እንዲሆን በአለባበስ ረገድ ትክክለኛው ልማዶችን እንዲመሰርቱ ሊበረታቱ ይገባል፤ ልብሶቻቸው በንጽህና እና በጥንቃቄ እንደተጠገነ እንዲጠብቁ መማር አለባቸው፡፡ ልማዶቻቸው በሙሉ ለሌሎች እርዳታ እና መጽናኛ የሚያደርጋቸው አይነት መሆን አለበት፡፡829 CGAmh 398.3

አለባበስ ተገቢ እና ማራኪ ይሁን። ምንም እንኳን የአስር ሳንቲም ካሊኮ ቢሆንም ግሩም እና ንጹህ መሆን አለበት። 830 CGAmh 398.4

ሥርዓት ያለው እና ትክክለኛ ምርጫ— በአለባበሳቸው [ክርስቲያኖች] ከልክ በላይ እና ታይታን ያስወግዳሉ፣ ነገር ግን አለባበሳቸው ግሩም፣ ብልጭልጭ ያልሆነ፣ ዝግ ያለ እና በለባሹ ሰው ላይ በሥርዓት እና በምርጫ የተቀናጀ መሆን አለበት።5 CGAmh 398.5

ትክክለኛ ምርጫ መናቅ ወይም መወገዝ የለበትም። ልዩ እንደ ሆኑ ሰዎች እንድንቆጠር፣ እምነታችን ተግባር ላይ ከዋለ በአለባበሳችን በጣም ግልፅ እንድንሆን እና ለመልካም ሥራዎች የቀናን እንድንሆን ይመራናል። በአለባበሳችን ሥርዓታዊነት እና ግሩምነትን ስናጣ ግን እውነትን ለመተው ምንም ያህል ያልቀራቸው እንሆናለን፤ ምክንያቱም እውነት ከፍ የሚያደርግ እንጂ የሚያዋርድ አይደለም፡፡ 831 CGAmh 399.1

እህቶቼ፣ አለባበሳችሁ ስለ ክርስቶስ እና ስለ ቅዱስ እውነት ወይም ስለ አለም እያወራ ነው፡፡ የትኛው ይሆን? 832 CGAmh 399.2

በቀለም እና በቅርጽ ጥሩ ምርጫ — ቀለም ላይ ምርጫ መተያት አለበት፡፡ በዚህ ረገድ ያለ ወጥነት ልክ እንደ ምቾት ሁሉ አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ቀለም ከግምት ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ዝግ ያሉ ቀለሞችን መፈለግ ተገቢ ነው። ቅርጻ ቅርጽ ያለው ቁሳቁስ ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ፣ ፣ እሱን በሚመርጡት ላይ ከንቱነትን እና ጥራዝ ነጠቅ ትዕቢትን የሚያሳይ ትልቅ እና ቀይ ቀለም ያለው ቅርጽ መወገድ አለበት፡፡ የተለያዩ ቀለሞችን በመልበስ ረገድ እንግዳ የሆነ ምርጫ መጥፎ ነው፡፡ 833 CGAmh 399.3

ረጅም ዕድሜ መቆየት መቻሉና አገልግሎቱ ይታይ— ልብሳችን ዝግ እና ቀለል ያለ ቢሆንም እንኳ ጥሩ ጥራት፣ ማራኪ ቀለም ያለው እና ለአገልግሎት ምቹ መሆን አለበት፡፡ ከታይታ ይልቅ ረጅም ዕድሜ መቆየት በመቻሉ መመረጥ አለበት፡፡ ሙቀት መስጠት እና ተገቢ መከላከልን የሚያደርግ መሆን አለበት፡፡ በምሳሌ መጽሐፍ የተገለጸችው ጥበበኛዋ ሴት “ለቤትዋ ሰዎች ከበረዶ ብርድ የተነሳ አትፈራም፤ የቤትዋ ሰዎች ሁሉ እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና፡፡” [ምሳሌ 31፡21] 834 CGAmh 399.4

ጥሩ ዕቃ መግዛት ቁጠባ ነው— ጥሩ እና በጥንቃቄ የተሰራ ዕቃ መግዛት ትክክል ነው፡፡ ይህ ነው ቁጠባ፡፡ ነገር ግን በጌጣ ጌጥ ማሸብረቅ አስፈላጊ አይደለም፣ እንዲሁም በዚህ ረገድ ተገቢ ያልሆነ ፍላጎትን ማርካት በእግዚአብሔር ሥራ ላይ መዋል የነበረበትን ገንዘብ የራስ ፍላጎትን በማርካት ማጥፋት ማለት ነው፡፡ 835 CGAmh 399.5

የጌታ የወይን ሥፍራ ምን እንደሚፈልግ አስታውስ— ግሩም እና ምርጥ አለባበስ ሊኖረን ይገባል፤ ነገር ግን እህቶቼ ሆይ፣ የራሳችሁን እና የልጆቻችሁን ልብስ በምትገዙበት ጊዜ፣ ገና ለመሰራት እየጠበቀ ስላለው ስለ ጌታ የወይን ሥፍራ አስቡ፡፡11 CGAmh 400.1

አለማውያን ልብስ ላይ ብዙ ያባክናሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡ ከዓለም እንዲወጣ እና እንዲለይ አዟል፡፡ በፍጻሜ ዘመን እየኖርን እንዳለን ለምናምን ሰዎች ማሸብረቅ ወይም ውድ ልብስ መልበስ ተገቢ አይደለም…፡፡ CGAmh 400.2

ለልብስ በሚወጣ ወጪ ቁጠባን ተለማመዱ፡፡ የምትለብሱት ልብስ ከእናንተ ጋር ግንኙነት ባላቸው ሰዎች ላይ ዘወትር ተጽዕኖ እንደሚያሳርፍ አስታውሱ፡፡ ለሌላ ቦታ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በራሳችሁ ላይ አታባክኑ፡፡ የጌታን ገንዘብ ለውድ ልብስ ያላችሁን አላስፈላጊ ፍላጎትን ለማርካት አታባክኑ፡፡ 836 CGAmh 400.3

በአለባበስ ረገድ ቀለል ያለ ዘይቤን መከተል የለባሹን ኃይማኖት ይመሰክራል— ቀለል ያለ የአለባበስ ዘይቤ አስተዋይ ሴትን ብልጫ እንዲኖራት ያደርጋታል፡፡ 837 CGAmh 400.4

ክርስቲያኖች እንደሚለብሱ ልበስ— መልካም እንደምትሰራ፣ እግዚአብሔርን እንደምትፈራ መልካም ሴት ቀለል ባለ እና ጌጣ ጌጥ ባልበዛበት አለባበስ ራሳችሁን አስውቡ፡፡ 838 CGAmh 400.5

ብዙዎች፣ ካልተለመደ ፋሽን ጋር እኩል ለማራመድ ሲሉ ቀላል ያለውን የተፈጥሮ ምርጫ ይተዋሉ፣ በሰው ሰራሽ ውበትም ይደሰታሉ። ጊዜንና ገንዘብን፣ የእውቀት ብርታትን እና የነፍስን እውነኛ ክብር፣ መስዋዕድ በማድረግ እና መላ ሕይወታቸውን ለፋሽን የይገባኛል ጥያቄ የሚያውሉ ናቸው። 839 CGAmh 400.6

ወድ ወጣቶች ሆይ በውስጣችሁ ያለው ከፋሽን ጋር በተጣጣመ መልኩ የመልበስ ፍቅር፣ እና ለታይታ ሀብል፣ ወርቅ እና አርቴፊሻሎችን ማድረግ ኃይማኖታችሁን ወይም እናምናለን የምትሉትን እውነት አይመሰክርም፡፡ አስተዋይ ሰዎች ውጫዊውን ለማስዋብ የምታደርጉትን ሙከራ በመመልከት የደካማ አእምሮዎች እና ትዕቢተኛ ልቦች ማረጋገጫ አድርገው ይወስዳሉ፡፡ 840 CGAmh 401.1

ተገቢ ያልሆነ ታይታ መኖር የለበትም— ለእነርሱ ኃጢአት ሲል አዳኛችን በራሱ ላይ የኃፍረት የእሾህ አክሊል በልበሱን፣ ሰውነታቸውን ለሚያስውቡ እና ኮፍያቸው ላይ ላባ ለሚያደርጉ ወጣቶች ማስታወስ እወዳለሁ፡፡ ልብስህን በማጌጥ ውድ ጊዜህን ስታልፍ፣ የክብር ንጉስ ያላጌጠ እና እንከን የለሽ ልብስ እንደለበሰ አስታውስ፡፡ ሰውነታቸውን ለማስጌጥ የምታደክሙ ሰዎች ሆይ፣ ኢየሱስ በስቃይ እና በችግር ላይ ያሉትን ለመባረክ ብዙውን ጊዜ በማያቋርጥ ልፋት፣ ራስን መካድ እና ራስን መስዋዕት በማድረግ የሚደክም መሆኑን ልብ ይበሉ ...፡፡ በታላቅ ለቅሶ እና እምባ ጸሎቱን ወደ አባቱ ያፈስ የነበረው በእኛ ምክንያት ነው፡፡ እነዚያ እምባዎች የፈሰሱት እና ከማንኛውም የሰው ልጅ በላይ የአዳኛችን ገጽታ በሐዘን እና በጭንቀት የተበላሸው እኛ አሁን ለማርካት የምንፈልገው እና የየሱስን ፍቅርን የሚያስገድደው ከዚህ ትዕቢት፣ የከንቱነት ፍቅር እና ተድላ እኛን ለማዳን ነበር፡፡ 841 CGAmh 401.2

አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦች— አላስፈላጊ ለሆኑ ጌጣ ጌጦች ውጭ መስራትን ልመዱ እና በዚህ መንገድ የተሰበሰበውን ገንዘብ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመስራት አውሉ፡፡ ራስን የመካድን ትምህርት ተማሩ፣ ለልጆቻችሁም አስተምሯቸው፡፡18 CGAmh 401.3

ግልጽ የሆነ ነጥብ— ብዙውን ጊዜ ያላጌጠ ከተልባ እግር የተሰራ ዘለበት መልበስ ስህተት እንደሆነ እንደማምን እጠየቃለሁኝ፡፡ [ማስታወሻ፡- ቴስቲሞኒስ ፎር ዘ ቸርች 1፡135፣ 136፡፡] መልሴ ሁል ጊዜ አይደለም ነበር፡፡ አንዳንዶች እኔ ስለ ዘለበት የጸፍኳቸውን ነገሮች ጽንፍ የያዘ ትርጉም በመውሰድ ከተገለጽት መካከል አንዱንም መልበስ ስህተት እንደሆነም ወስደዋል፡፡ ለታይታ እና ለፋሽን ሲሉ አንዳንድ የሰንበት ጠበቂዎች የሚለብሱት በውድ የተሰራ ዘለበት እና ውድ እና አላስፈላጊ ጥብጣች እና ቀለማትን አሳይተውኝ ነበር፡፡ ስለ ዘለበት በጠቀስኩበት ጊዜ ዘለበት የመሰለ ነገር መለበስ እንደሌለበት ወይም ስለ ጥብጣቦች በጠቀስኩበት ጊዜ የትኛውም ጥብጣብ መለበስ እንደሌለበት እንዲረዱኝ ዕቅዴ አለነበረም፡፡ 842 CGAmh 402.1

ብኩን ወይም ጽንፍ የያዙ ጌጣ ጌጦች— አገልጋዮቻችን እና ሚስቶቻቸው ያለጌጠ ልብስ በመልበስ ምሳሌ መሆን አለባቸው፤ ግሩም፣ ምቹ እና ጥሩ እቃ የሆነ ልብስ መልበስ አለበት፣ ነገር ግን ውድ ባይሆንም እንኳ ብኩንነት እና ጌጣ ጌጦችን መስወገድ አለባቸው፣ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች ጉዳት የሚያመጡ ናቸው፡፡ ቀለል ያለ፣ ያላጌጠ እና ግሩም አለባበስን ዘይቤ ወጣችን ማስማር አለብን፡፡ ዋጋው እምነት ቢሆንም እንኳ ከመጠን በላይ ማጌጥ መቅረት አለበት፡፡ 843 CGAmh 402.2

ለታይታ አይሁን— እውነተኛ ጸጋ ሰውነትን ለታይታ በማስዋብ እርካታን አያገኝም፡፡ 844 CGAmh 402.3

መጽሐፍ ቅዱስ በአለባበስ ረገድ ዝግ ማለትን ያስተምራል፡፡ “ እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፡፡” 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡9፡፡ ይህ በአለባበስ ረገድ ያለውን ታይታ፣ ብልጭልጭ ቀለሞችን እና የቅምጥልና ጌጣ ጌጦችን ይከለክላል፡፡ ትኩረትን ወደ ለባሹ የሚስብ ወይም አድናቆትን ለመቀሰቀስ የተቀደ ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ቃል ከሚያዘው ዝግ ያለ አለባበስ ውስጥ የተገለለ ነው፡፡ 845 CGAmh 402.4

በአለባበስ ረገድ ራስን መካድ የክርስቲያን ተግባር አካል ነው፡፡ ያላጌጠ ልብስ መልበስ እና ከማናቸውም አይነት ጌጣ ጌጥ እና ማስዋቢያዎች መቆጠብ ከእምነታችን ጋር የሚስማማ ነው፡፡ ለልብስ ከመጠን በላይ ወጪ ማድረግ እና ተድላን መውደድን በማርካት የዓለማዊነት ከንቱነትን ከሚመለከቱ ሰዎች መካከል ነን? 846 CGAmh 403.1

የማይጠፋጌጥ እና ወርቅ ወይም ዕንቁ— ፈጽሞ የማይጠፋ፣ በዚህ ዓለም ውስጥ በዙሪያችን ያሉትን ሁሉ ደስ የሚያሰኝ እና በመጻኢው ሕያውነት ውስጥ በማይጠፋ ድምቀት የሚያበራ ጌጥ አለ። እርሱም የየዋህ እና የዝግተኛ መንፈስ ውበት ነው፡፡ እግዚአብሔር እጅግ በጣም የከበረን ልብስ ለነፍሳችን እንድንለብስ አዝዞናል ....፡፡ ለውጫዊው ወርቃማ ጌጣጌጦችን ከመፈለግ ይልቅ ከጥሩ ወርቅ የበለጠ ውድ የሆነውን ጥበብ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ 847 CGAmh 403.2

ከክርስቶስ ፍቅር አንፃር ሲታይ ወርቅ ወይም ዕንቁ ወይም ውድ ልብስ ምንኛ አነስተኛ ዋጋ ያለው ነው፡፡ ሚዛናዊነት የተፈጥሮአዊ ማራኪነት ዋና አካል ነው፣ ወይም አንዱ ከሌለው እርስ በእርስ ስምሙ የሆነ ክፍል ነው፤ ነገር ግን መስማማት ወይም የነፍሳችን ክርስቶስን መመስል የመንፈሳዊ ማራኪነት ዋናው አካል ነው፡፡ ይህ የእነዚህን ባለቤት ከጥሩ ወርቅ ፣ ከኦፊር ወርቅማ ውሻል የበለጠ ውድ ያደርገዋል። የክርስቶስ ጸጋ በእርግጥም በዋጋ ሊተመን የማይችል ውበት ነው። የዚህ ባለቤት የሆነውን ከፍ ከፍ የሚያደርግ እና የሚያስከብር እና በሌሎች ላይ የክብር ጨረሮችን የሚያንጸባርቅ፣ እንዲሁም ወደ ብርሃን እና የበረከት ምንጭ የሚስብ ነው። 848 CGAmh 403.3

የእውነተኛ ውበት መስህብ— ሁሉም ሰው ተግባራዊ ከመሆን ይልቅ ስሜታዊ የመሆን ተፈጥሮአዊ ዝንባሌ አለው። ከዚህ እውነታ አንፃር፣ ወላጆች በልጆቻቸው ትምህርት ረገድ እምሮአቸው እውነትን፣ ተግባርን እና ራስን መካድን እና ክቡር ኢጥገኝነት እንዲኖራቸው፣ አብዛኛው ሰው ስህተትን ሲመርጥ ትክክለኛ መሆንን እንዲመርጡ፣ መምራት እና ማሠልጠን አስፈላጊ ነው…፡፡ CGAmh 403.4

ጤናማ ሰውነት እና ተወዳጅ ስሜት ካለቸው፣ በመለኮታዊ ጸጋ ሊለብሷቸው የሚችሏቸውን እውነተኛ ውበት ያገኛሉ፡፡ ደግሞም እነርሱ በሰው ሠራሽ ቅርፃ ቅርጾች ማጌጥ አያስፈልጋቸውም፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁል ጊዜ የእውነተኛ ግብረ ገብ ውበት እጦት ገላጭ ናቸው፡፡ ቆንጆ ባህሪይ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ያለው ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ውበት ይስባል እንጂ አያሳስትም። እንዲህ አይነቶቹ ክታቦች መቼም የማይጠፉ ጥብቅ ቀለሞች ናቸው፡፡ 849 CGAmh 404.1

የየሱስ ንጹህ ኃይማኖት ከተከታዮቹ ከሰው ሰራሽና ሐሰት ይልቅ የተፈጥሮ ውበት ቀለል ያለ ዘይቤ እና የተፈጥሮ ባህሪይን ለውጥ እና ከፍ ያለ ንጽህናን ይጠይቃል፡፡ 850 CGAmh 404.2

ልጆቹ አስተዋይነት የተሞላበትን አለባበስ ለይተው እንዲያውቁ አስተምሯቸው— ለቤት ህይወት ተግባሮች ታማኝ እንሁን። ልጆች ታዛዥነት እዚያ መንገስ እንዳለበት መገንዘብ አለባቸው፡፡ በአለባበስ ረገድ በአስተዋይነት እና ሞኝነት መካከል እንዲለዩ አስተምሯቸው፣ እንዲሁም በጣም ጥሩና ቀለል ያሉ ልብሶችን አቅርቡላቸው፡፡ በቅርብ ጊዜ ለሚሆነው የክርስቶስ መመለስ እየተዘጋጁ ያሉ ሕዝቦች እንደመሆናችን መጠን ከዘመኑ ፋሽን በተቃራኒ ለአለም ጥሩ የዝግተኝነት ምሳሌ ልንሆን ይገባል፡፡ እነዚህን ነገሮች በዝርዝር ይወያዩ፣ እና ምን እንደሚያደርጉ በጥበብ ያቅዱ፤ ከዚያ እቅዶችዎን በቤተሰብዎ ውስጥ ያከናውኑ። ከልጆችዎ ሐሳቦች እና ምኞቶች በላይ በከፍተኛ መርሆዎች ለመመራት ይወስኑ። 851 CGAmh 404.3

ልባችን ከክርስቶስ ልብ ጋር ከተሳሰረ፣ … በሰው ላይ ትኩረትን ለመሳብ ወይም ተጋድሎ ለመፍጠር ምንም አይደረብም፡፡ 852 CGAmh 404.4

በኑሮ ውስጥ ለእድሜ እና የሥራ ባህሪይ ተስማሚ የሚሆን አመቺ አልባሳትን ማቅረብ— እህቴ ሆይ የልጆችሽን ልብ በፍቅር በልብሽ ላይ እሰሪ፡፡ በሁሉም ነገር ተገቢውን እንክብካቤ እና ትኩረት ስጭያቸው፡፡ ይህ ክብራቸው ላይ ጉዳት የሚያስከትል ስለሆነ በገጽታቸው እንዳይዋረዱ አመቺ የሆነ አልባሳት አቅርቢላቸው …፡፡ በኑሮ ውስጥ ለዕድሜ እና የሥራ ባህሪይ ተስማሚ በሚሆን መልኩ በሥርዓት እና አመቺ በሆነ ሁኔታ መልበስ ሁል ጊዜ ትክክል ነው፡፡853 CGAmh 405.1

ሰውነት መጣበቅ የለበትም— ልብስ የደም ዝውውር እንዳይሰራጭ ወይም ነፃ፣ ሙሉ እና ተፈጥሯዊ አተነፋፈስን የማያግድ በቀላሉ የሚገጥም መሆን አለበት። እግሮች በተገቢ ሁኔታ ከብርድ እና ከእርጥበት መጠበቅ አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ ከለበስን፣ ማለዳ ወይም ማታ ጠል፣ ወይም ዝናብ ከዘነበ ወይም በረዶ ከወረደ በኋላ እንኳ፣ ብርድ ሳንፈራ ከቤት ውጭ አየር ማግኘት በሚቻልበት ሥፍራ ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት እንችላለን። 854 CGAmh 405.2

የትናንሽ ልጆች አለባበስ— የልጅ ልብስ ሙቀትን፣ መከላከል እና ምቾት አጣምሮ ከያዘ፣ የመበሳጨት እና የመቁነጥነጥ ዋና ዋና መንስኤዎች አንዱ ተወግዷል፡፡ ትንሹ ልጅ የተሻለ ጤና ይኖረዋል፣ እናትም የልጇ እንክብካቤ በጥንካሬዋ እና በጊዜዋ ላይ ከባድ ተግባር ሆኖ አታገኘውም። CGAmh 405.3

ጠባብ ማሰሪያ ወይም መቀነት የልብ እና ሳንባዎችን ተግባር የሚያደናቅፍ በመሆኑ መወገድ አለበት፡፡ አንዱም የሰውነት ክፍል በማንኛውም ጊዜ የአካል ክፍልን በሚያምቅ ወይም የመንቀሳቀስ ነፃነቱን በሚገድብ ልብስ ምቾት ማጣት የለበትም፡፡ የሁሉም ልጆች አልባሳት ነጻ እና ሙሉ አተነፋፈስን ለማስገባት እጅግ ለቀቅ ያለ እና ትከሻዎች ክብደቱን እንዲሸከሙ ሆኖ መሰራት አለባቸው። 855 CGAmh 405.4

እጆች እና እግሮች በአግባቡ መልበስ አለባቸው— ከፍተኛ ሙቀት ባለበት እንደ ደረት እና የልብ ክልል ሁሉ እጅ እና እግር በጥሩ ሁኔታ እንዲለብሱ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እጅ እና እግርን እርቃናቸውን በመተው ወይም ከዚያ ባልተናነሰ ሁኔታ ልጆቻቸውን የሚያለብሱ ወላጆች የልጆቻቸውን ጤና እና ሕይወት ለፋሽን ሲሉ መስዋዕት እያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚህ አካላት እንደ ሌሎቹ የሰውነት ክፍሎች የማይሞቁ ከሆነ የደም ዝውውሩ እኩል አይሆንም፡፡ ከዋና ዋና አካላት ርቀው የሚገኙት እጆች እና እግሮች በትክክል ካልለበሱ ደም ወደ ጭንቅላት ይዛወራል፣ ይህም የራስ ምታት ወይም የአፍንጫ ነስርን ያስከትላል፤ ወይም በዚያ አካባቢ ብዙ ደም በመኖሩ ሳቢያ ደረት አከባቢ የመመላት ስሜት ይኖራል፣ ይህም በዚያ አካባቢ ላይ እጅግ ብዙ ደም ስለሚኖር ሳል የልብ ምት መጨመር የሚያስከትል ወይም ጨጓራ በጣም ብዙ ደም ስለሚኖረው የሆድ ድርቀት ያስከትላል። CGAmh 405.5

እናቶች ፋሽንን ለመከተል ሲሉ የልጆቻቸውን እጆች እና እግሮች እርቃን ከመሆን ባልተናነሰ መልኩ ያለብሷቸዋል፤ ደም በመቀዝቀዝ ዝውውሩን ያቋርጥ እና በሽታን በመፍጠር ከተፈጥሮ መንገዱ ተመልሶ ወደ ውስጣዊ የሰውነት የአካል ክፍሎች ይመለሳል፡፡ በፈጣሪያችን እጆች እና እግሮች እንደ ፊት ተጋላጭነትን እንዲቋቋሙ ተደርገው አልተፈጠሩም። ለሰው ሕይወት አስፈላጊ የሆነውን እጅግ ብዙ ደም ማግኘት እንዲችሉ፣ እጆች እና እግሮች ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ጋር በተመሳሳይ መልኩ ሙቀት እንዲያገኙ፣ ጌታ ለእጆች እና ለእግሮችም ጭምር ትላልቅ የደም ሥሮች እና ነርቮችን ሰጥቷል፡፡ እነርሱ ደምን ወደ እጆች እና እግሮች መሳብ በሚችል መልኩ መልበስ አለባቸው፡፡ CGAmh 406.1

ሰይጣን ለሕይወት አስፈላጊ የሆነው ደም ቀዝቅዞ ከዋናው መንገድ ወደ ኋላ በመመለስ እጆች እና እግሮች እንዲጋለጡ የሚያደርግ ፋሽንን ፈጠሯል፡፡ ወላጆችም በፋሽን መስገጃ ሥፍራ ይሰግዳሉ፣ እንዲሁ ነርቮች እና ደም መላሽ ቧንቧዎች እንዲኮማተሩ በሚያደርግ እና እግዚአብሔር ላቀደው ዓላማ መልስ መስጠት በማያችላቸው ሁኔታ ልጆቻቸውን ያለብሳሉ፡፡ ውጤቱም በተለምዶ ቀዝቃዛ እግሮች እና እጆች ናቸው፡፡ ከሕሊና ፍርድ ይልቅ ፋሽንን የሚከተሉ ወላጆች የልጆቻቸውን ጤንነት በዚህ መልኩ በመዝረፋቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡ ሕይወትም እንኳን ዘወትር ለፋሽን አምላክ ይሰዋል፡፡ 856 CGAmh 406.2

የወንዶች እና የሴቶች አለባበስ ልዩነት— ሴቶች በአለባበሳቸው እና በገጽታቸው ልክ እንደሌላው ጾታ ለመሆን ምንም ያለቀረው እና አለባበሳቸውን በተቻላቸው መጠን ሁሉ እንደ የወንዶች የመለበስ አዝማሚያ እያደገ መጥቷል፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህ አስጸያፊ እንደ ሆነ በግልጽ ተናግሯል፡፡ “እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፡፡” 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፡9...፡፡ CGAmh 407.1

የእግዚአብሔር ዕቅድ በወንድ እና በሴቶች አለባበስ መካከል ግልፅ የሆነ ልዩነት እንዲኖር ነበር፣ በዚህም ረገድ ግልጽ መመሪያዎችን መስጠት እጅግ አስፈላጊ እንደሆነም ተመልክቷል፤ በሁለቱም ጾታዎች የሚለበሰው ተመሳሳይ አለባበስ ግራ መጋባትን እና የወንጀል መጨመርን ያስከትላል፡፡ 857 CGAmh 407.2

ለቤተክርስቲያን የሚሆን አለባበስ— ማንም ሰው በታይታ አለባበስ የእግዚአብሔርን መቅደስ ክብር እንዳያዋርድ።35 CGAmh 407.3

ሁሉም በአለባበሳቸው ግሩም፣ ንፁህ እና ሥርዓታዊ መሆንን መማር አለባቸው እንጂ ለቤተ መቅደስ ሙሉ በሙሉ አግባብነት በሌለው ውጫዊ የጌጥ ውበት መርካት የለባቸውም፡፡ አክብሮት ማጣትን ስለሚያበረታታ ለታይታ መልበስ መኖር የለበትም። የሰዎች ትኩረት ብዙውን ጊዜ በዚህኛው ወይም በዚያኛው መልካም የአለባበስ አይነት ይሳባል፣ እናም በዚህ መንገድ በአሚላኪዎች ልብ ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው የማይገባቸው ሀሳቦች ሰርገው ይገባሉ። እግዚአብሄር የሃሳብ ርዕሰ ጉዳይ፣ የአምልኮ ግብ መሆን አለበት፤ እንዲሁ አእምሮን ከክቡር እና ከቅዱስ አገልግሎቱ በተቃራኒ አቅጣጫ የሚስብ ማንኛውም ነገር በእርሱ ላይ ጥቃት የሚፈጽም ነው፡፡ አልቦ፣ ሪቫን፣ የልብስ ጌጣ ጌጦች እና ላባ እንዲሁም የወርቅ እና የብር ጌጣጌጦች የጣኦት አምልኮ ዝርያ ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ ለአምላክ ቅዱስ አገልግሎት ተገቢ የማይሆኑ ናቸው፡፡ 858 CGAmh 407.4

አንዳንዶች ከዓለም መለየትን ተግባራዊ ለማድረግ ስለ አለባበሳቸው ችላ ማለት እንዳለባቸው የእግዚአብሔር ቃል ይጠይቀናል የሚል ሐሳብ ይቀበላሉ፡፡ ከዓለም ጋር ያለመመሳሰል መርኾዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሲሉ በሰንበት ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ በቅዱሳን ጉባኤ መካከል በሚታዩበት ጊዜ ተራ የጸሃይ ባርኔጣ እና በሳምንቱ ውስጥ የለበሱትን ልብስ ይለብሳሉ፡፡ አንዳንድ ክርስቲያን ነን ባዮችም የአለባበስን ጉዳይ በዚሁ ብርሃን ይመለከታሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች በሰውነታቸው ላይ ባለ ዝርክርክ ሁኔታ አቧራማ እና ቆሻሻ እንዲሁም በልብሶቻቸው ላይ ካሉ ሰፋፊ ቀዳዳዎች ጋር በሰንበት ቀን ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሰበሰባሉ፡፡ CGAmh 408.1

ይህ ቡድን በተለይም በእርሱ ፊት ሞገስ ለማግኘት የሚመኙ በዓለም የተከበረ ጓደኛ ለማግኘት ቀጠሮ ቢኖራቸው በተቻላቸው መጠን ማግኘት በሚችሉት ልብስ በእርሱ ፊት ለመቅረብ ይጥራሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ባልተበጠረ ጸጉራቸው እና ንጹህ እና ስርዓታዊነት በሌለው አለባበሳቸው ቢቀርቡ ይህ ጓደኛ እንደ ተናቀ ይሰማዋል፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ሰዎች ታላቅ አምላክን ለማምለክ በሰንበት ቀን ሲገናኙ በማንኛውም አለባበስ ቢታዩ ወይም የሰውነታቸው ሁኔታ ምንም ቢሆን ምንም ችግር የለውም ብለው ያስባሉ፡፡ 859 CGAmh 408.2

አለባበስ የክርክር ርዕሰ ጉዳይ መሆን የለበትም— የአለባባስን ጥያቄ የኃይማኖታችሁ ዋና ነጥብ ማደረግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ መነጋገርን የሚፈለግ የላቀ ነገር አለ፡፡ ስለ ክርስቶስ ተናጋገሩ፤ ልብ በሚለወጥ ጊዜ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የማይስማማ ነገር ሁሉ ይወድቃል፡፡ 860 CGAmh 408.3

በእግዚአብሔር እይታ ዋጋ እንዲኖርህ የሚያደርገህ አለባበስህ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ዋጋ የሚሰጣቸው የውስጥ ውበት፣ የመንፈስ ጸጋዎች፣ የርህራሄ ቃላት እና ለሌሎች ማሰብን ነው፡፡ 861 CGAmh 409.1

ማንም ለሌላ ሰው ሕሊና መሆን የለበትም፣ ነገር ግን ጥሩ ምሳሌን መሆን ይችላል—አለባበሱን የኃይማኖቱ ማዕከል የሚያደርገውን ክፍል አታበረታቱ። በአለባበስ ረገድ ቀለል ያለ ዘይቤን መከተል እና ያላጌጠ መሆን እንዳለበት መጸሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ግልጽ አስተምህሮ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ የሚያጠና እና ለእነዚያ ትምህርቶች በታማኝነት በመታዘዝ ለዓለም እና ለአዲስ አማኞች ጥሩ ምሳሌ ይሁን፡፡ እግዚአብሄር ማንም ሰው ለሌላው ህሊና እንዲሆን አይፈልግም፡፡ CGAmh 409.2

ስለ የሱስ ፍቅር እና ትህትና ተናገሩ እንጂ አንዳቸው ከሌላው አለባበስ ወይም ገጽታ ላይ ጉድለቶችን በማንሳት ጊዜያቸውን የሚያሳልፉ ወንድሞች እና እህቶችን አታበረታቱ። አንዳንዶች በዚህ ሥራ ይደሰታሉ፤ እናም አእምሯቸው ወደዚህ አቅጣጫ ሲዞር፣ የቤተክርስቲያን አዳሾች መሆን አለብን የሚል ስሜት ሊሰማቸው ይጀምራል፡፡ በፍርድ ወንበር ላይ በመቀመጥ ከወንድሞቻቸውና ከእህቶቻቸው አንዳቸውን በተመለከቱበት ቅጽበት፣ የሚተቹበት ነገር ለማግኘት ይፈልጋሉ፡፡ ይህ የአስተሳሰበ-ጠባብ እና በመንፈሳዊ ዕድገት የቀጨጨ ለመሆን አንዱ ውጤታማ መንገድ ነው፡፡ እግዚአብሔር በፍርድ ወንበር ላይ ስላላስቀመጣቸው ከዚያ ላይ እንዲወርዱ ይፈልጋል፡፡ 862 CGAmh 409.3

ልብ የቀና መሆን አለበት— ክርስቲያን ከሆንን ምንም እንኳን የምንጓዝበት መንገድ የተፈጥሮ ዝንባሌያችንን ቢያደናቅፍብንም ክርስቶስን እንከተላለን፡፡ ይህንን ወይም ያንን መልበስ የለብህም ብሎ ለአንተ መናገር ምንም ፋይዳ የለውም፣ ምክንያቱም የእነዚህ ከንቱ ነገሮች ፍቅር በልብህ ውስጥ ከሆነ፣ ማስዋቢያዎችህን መተው ልክ የዛፍ ቅጠሎችን እንደ መቁረጥ ብቻ ይሆናል። የተፈጥሮ ልብ ዝንባሌዎች እንደገና ራሳቸውን ይገልጣሉ፡፡ የራስህ ህሊና ሊኖርህ ይገባል።. 863 CGAmh 409.4

በርካታ ኃይማኖቶች ኃይላቸውን ያጡበት ነጥብ— የሰው ልጅ አስተሳሰብ ቀላል እና ቀጥተኛ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል መደበቅ ወይም ገሸሽ ማድረግን ሲሻ ከርሟል፡፡ በየዘመናቱ አብዛኛዎቹ የክርስቶስ ተከታዮች ነን ባዮች ራስን መካድ እና ራስን ዝቅ ማድረግን የሚጠይቀውን ዝግ ማለትን፣ ቀለል ያለ ንግግር፣ ጸባይ እና አለባበስን የሚያዙትን እነዚያን ሕጎችን ችላ ይላሉ፡፡ ውጤቱም አንድ ተመሳሳይ ነው— ከወንጌል አስተምህሮ ማፈንገጥ ወደ ፋሽሽኖች፣ ልምዶች እና የአለም መርሆዎች ወደ መቀበል ያመራል። በጣም ወሳኝ የሆነው እግዚአብሔርን መምሰል ለሙት ሕጋዊነት ሥፍራውን ይለቃል፡፡ ከእነዚህ ዓለም-አፍቃሪ ክበቦች የተለየው የእግዚአብሔር መገኘት እና ኃይል የሚገኘው የቅዱስ ቃሉን ትምህርቶች ለመታዘዝ ፈቃደኛ ከሆኑ ትሑት አምላኪዎች ጋር ይገኛል፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ውስጥ ይህ ተግባራዊ ሲሆን ቆይቷል፡፡ የተለያዩ ቤተ እምነቶች አንዱ ሌላውን ተከትሎ በመነሳት ቀለል ያለ ዘይቤን ትተዋል፣ የቀድሞ ኃይላቸውንም በእጅጉ አጥተዋል፡፡ 864 CGAmh 410.1

የእግዚአብሔር ቃል መመዘኛ ይሁን— የአለባበስ ጉዳዮች ሁሉ የመጽሐፍ ቅዱስን ህግ በጥብቅ በመከተል በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት፡፡ ፋሽን የውጭውን ዓለም የምትገዛ አምላክ ናት፣ እንዲሁ ብዙውን ጊዜ ወደ ቤተ-ክርስቲያን ሾልካ ትገባለች። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል መመዘኛዋ ማድረግ ይኖርባታል፣ ወላጆችም በዚህ ጉዳይ ላይ በጥበብ ማሰብ አለባቸው፡፡ ልጆቻቸው ዓለማዊ ፋሽኖችን የመከተል አዝማሚያ ሲያዩ፣ ልክ እንደ አብርሃም፣ ቤተሰቦቻቸውን ከኋላቸው ያለማወላወል ማዘዝ አለባቸው፡፡ ከዓለም ጋር አንድ ከመሆን ይልቅ ከእግዚአብሔር ጋር አንድ አድርጓቸው፡፡ 865 CGAmh 410.2